Posts

Hardywood Bourbon Sidamo

Image
Beer style:  Imperial Coffee Stout aged in Bourbon Barrels An assertive Imperial Stout aged 12 weeks in bourbon barrels and conditioned on custom roasted Sidamo coffee from Lamplighter Roasting Company, Bourbon Sidamo showcases the signature flavors of whiskey, roasted malt and Ethiopian coffee. This robust stout displays a midnight hue with a caramel head and offers a dark chocolate character laced with hints of blueberry from this unique coffee bean, rounded out by charred White Oak infused by an angel’s share of Kentucky goodness. Best with:  Pairs beautifully with rich, soft cheeses, gamey meats in savory sauce, cream-based and dark fruit desserts. Original Gravity (O.G.):  1.092 Strength (ABV):  10.3 % ABV Color (SRM):  45 °L Bitterness (IBU):  55 IBUs Next release date:  Sat, 03/02/2013 - 2:00pm Package:  Draft 1/6 bbl (5.1 gal) keg Bottles 12 x 750 ml bottles Category:  Barrel Series beer

አዲሱ የኢትዮጵያ የቋንቋ ፖሊሲ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው

Image
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 13 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተዘጋጀው የቋንቋ ፖሊሲ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው። ረቂቅ ፖሊሲው ላለፉት ሁለት ዓመታት ሀገራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ ጋር በመተባበር በባለድርሻ አካላት ሲገመገም ነው የቆየው። ትላንትና ከትናንት ወዲያ  በተካሄደው የመጨረሻ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ፥ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ሌሎችም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት የተውጣጡ 230 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። በሚኒስቴሩ የቋንቋና የባህል ልማት ዳይሬክተር አቶ አውላቸው ሹምነካ እንዳሉት ፖሊሲው የግልና የጋራ የቋንቋ መብቶችን የያዘ ነው። ከፊደል ቀረጻ ጀምሮ እስከ ትግበራ ያለው ሂደት በስርዓት እንዲመራ ፖሊሲው አጋዥ ይሆናል ሲሉ አቶ አውላቸው ለሪፖርተራችን ራሔል አበበ ነግረዋታል። በመድረኩ የቋንቋና የህግ ማዕቀፍ፣ ቋንቋና አፍ መፍቻ ፣ ቋንቋና ከፍተኛ ትምህርት የሚሉና ሌሎችም 10 ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን ፥ በቋንቋ ዙሪያ የህንድና የደቡብ አፍሪካ ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የቋንቋ መብቶች በተገቢው መንገድ ተግባራዊ እንዲሆኑና እንዲደረጉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል የተባለው ፖሊሲ ግብአት ከተሰበሰበት በኋላ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

በለኩ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የሚሸጥ መድሃኒት እየተበራከተ ነው.......ነዋሪዎች

Image
አዋሳ ሚያዚያ 15/2005 በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በሌኩ ከተማ በሀገ ወጥ መንገድ በከተማው የሚሸጡ መድሃኒቶች መበራከት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ በከተማው በገበያ ፣በመንገድ ዳርና ሱቆች በህገ ወጥ መንገድ የሚሸጡ መድሃኒቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መቷል፡፡ ይህም ለነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሪፖርተር አስተያየታቸውን የሰጡ አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ከነዋሪዎቹ መካከል ወይዜሮ ጥሩወርቅ ወልዴ፣ ወይዜሮ አበባው በቀለና ወይዘሮ ምትኬ ጫኒያለው እንዳሉት በተለይ ረቡዕና ቅዳሜ መድሃኒቱ ገበያ ላይ እንደማንኛውም ሸቀጥ ቀርቦ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ መድሃኒቱ የሚሸጠው ምንም ስለመድሃኒቱ ዕውቀት በሌላቸው ግለሰቦች መሆኑ ጉዳዩን እጅግ አሳሳቢ እድሮጎታል፡፡ በተለይ የሰው መድሃኒት ከከብቶች፣ ከበግና ከፍየል በድሃኒቶች ጋር አንድ ላይ ተቀላቅሎ መሸጡ የነገሩን አሳሳቢነት በህብረተሰቡ ዘንድ እንዲጨምር ማድረጉን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቡርሶ ቡላሾ ነዋሪዎች ያነሱት ቅሬታ ትክክል መሆኑን በማመን ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ ከወረዳ አስተዳደር፣ ከፖሊስና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ ህገ ወጥ መድሃኒቶቹ ጎረቤት ወረዳዎችና ዞኖች በማቋረጥ ወደ ከተማ የሚገቡ ስለሆነ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ከአጎራባች ወረዳዎችና ዞኖች ጋር በመሆን እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎችን ከዳር ለማድረስ የህብረተሰቡ የተቀናጀ ትብብርና እገዛ ወሳኝ በመሆኑ በህገ ወጥ መንገድ በመድሃኒት ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦችን በማጋለጥ ህብረተሰቡ እንዲተባበር ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ h

የኢትዮጵያ ምርጫ፤ ሰብአዊ መብትና ዉዝግብ

Image
ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ብራስልስ ላይ እንዳሉት መንግሥታቸዉ ከዓለም አቀፉ ድርጅት ሸላሚዎች ጋር አይግባባም፥ እንዲያዉም ይቃረናል።ከዋሽግተን ዲሲ የደረሰንን ዘገባ ከተከታተላችሁት፥ የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አርብ ማታ ይፋ ያደረገዉ ዓመታዊ ዘገባ ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም መግለጫ ጋር መቃረኑን አስተዉላችኋል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ኀላፊ፥--- ከተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣናት አንዱ፥ --- የፖለቲካ ተንታኝ፥ ---- ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማይርያም ደሳለኝ፥--- የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሹም፥--- አይግባቡም።አይደማመጡም፥ ይቃረናሉም።እንዴት? ለምን? ላፍታ አብረን እንጠይቅ ------ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት፥ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞች ለበርካታ አመታት እንደሚያደርጉ፥ እንደኖሩበት፥ከኖርዌ እስከ ዋሽግተን፥ ከአዳራሽ እስከ አደባባይ እንደተሰለፉ ያለፈዉ ሳምንት-ይሕን ሳምንት ተካ።ጥያቄዉ አንድም ብዙም ነዉ።መፈክሩ ግን ይቀነቀናል።ጥያቄዉ ይዥጎደጎዳል።ቅዳሜ፥-ስታቫንገር-ኖርዌ ተደገመ። ቅዳሜ፥ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምናልባት አዲስ አበባ ይሆኑ ይሆናል።ከአራት ቀን በፊት ሮብ ግን ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ነበሩ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳት ከማርቲን ሹልስ ጋር ባደረጉት ዉይይት ከተነሱ ጉዳዮች የኢትዮጵያ መንግሥት የሠብአዊ መብት፥ የፕሬስ ነፃነት፥ የፍትሕ አያያዝ ዋናዎቹ ነበሩ። ድምፅ ሲሰጥ ርዕሠ-መንበሩን ፓሪስ ፈረንሳይ ያደረገዉ የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፥ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት (UNESCO) የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ወንጀል በይግባኝ አምስት ዓመት እስራት ያስፈረደባትን አምደኛ፥ ፀሐፊ

ኢሳት የተባለው የቴለቪዥን ጣቢያ በወንዶ ገነት ነዋሪ የሆኑትን የሲዳማን እና የኣማራን ብሄሮች ለማጣላት የሚያደርገውን ቅስቀሳ ያቁም

Image
የወንዶ ገነት ኮሌጅ ዲን እና የኮሌጁ የፖሊስ ክፍል አዛዥ ታሰሩ ኢሳት በኣካባቢው መንግስት እና በወንዶ ገነት  የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የከሰተውን ኣለመግባባት ገጽታውን በመቀየር የዘር ግጭት ለመጫር የሚያደርገውን ግፍት የምመለከተው ኣካል ማቆም ኣለበት።  ኣለመግባባቱን በተመለከተ በኢሳት የቀረበው ዜናን ከታች ያንቡ፦ ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዋሳ ዩኒቨርስቲ ስር የሚገኘው የወንዶገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ጸጋየ በቀለ እና የኮሌጁ የፖሊስ ክፍል አዛዥ  ሻምበል አለማየሁ ወረታ የታሰሩት የመንግስት ባለስልጣናት የኮሌጁን መሬት በመቁረጥ ለአካባቢው ተወላጅ ባለሀብት ለመስጠት የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወማቸው ነው። አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ዩኒቨርስቲው ባለስልጣን ለኢሳት እንደገለጹት ሁለቱም ግለሰቦች የታሰሩት የአካባቢው ባለስልጣናትየኮሌጁን መሬት በመውሰድ ለአንድ ባለሀብት ለመስጠት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ሁለቱ ሰዎች አጥብቀው በመቃወማቸው ነው። ሻምበል አለማየሁም ሆኑ ዶ/ር ጸጋየ “መሬቱ የኮሌጁ በመሆኑ ፈርመን አንሰጥም” በማለታቸው ካለፈው አረብ ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆኑ፣ ባለስልጣኑ እንደሚሉት ጉዳዩ ከዘር ጋር የተያያዘ ነው። ሻምበል አለማየሁ የሲዳማን ህዝብ ለመውጋት ጦር አዘጋጅተዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን፣ እሳቸውን ለመያዝ ከ12 በላይ ፖሊሶች ወደ ዩኒቨርስቲው ሲገቡ መጠነኛ ረብሻ ተነስቶ እንደነበርም ለማወቅ ተችሎአል። ሻምበል አለማየሁ በተያዙበት ወቅት ” ወንጀል አልፈጸምኩም ወንጀሌ አማራ መሆኔ ብቻ ነው” በማለት ይናገሩ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወንዶገነት በጉዳዩ ዙሪያ የአካባቢውን ባለስልጣናትን ለማነጋገር አደረግነው