Posts

በሃዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የባህል ፌስቲቫልና የኢንዱስትሪ ሳምንት ተጠናቀቀ

Image
ተፈጥሮአዊ መስህቦችና ባህላዊ ቅርሶች ለሀገሪቱና ለዓለም ህዝቦች በማሳወቅ ለገፅታ ግንባታው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው  እየሰራ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሃዋሳ ከተማ ለአምስት ቀናት   ሲካሄድ የቆየው የባህል ፌስቲቫልና የኢንዱስትሪ ሳምንት መጋቢት 30/2005 ተጠናቋል፡፡ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ የልማትና የትብብር ዳይሬክቶሬት ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ ተስፋዮ ኦታንጎ በፌስትቫሉ መዝጊያ ላይ እንደገለጹት የብዝሃ ባህል፣ የቅርስና የተፈጥሮ መስህቦችን ቀጣይነት ባለው መልኩ በመጠበቅና በማልማት የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት እየተሰራ ነው፡፡ የሀገሪቱን ዕምቅ የባህል፣ የተፈጥሮ ቅርሶችና ዕሴቶችን በተገቢው መንገድ በማልማት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ጉልህ ድርሻ እንዲኖራቸው ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ ለሁለተኛ ጊዜ ከመጋብት 25   እስከ መጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ በተካሄደው የባህል ፌትቫልና የኢንዱስትሪ ሳምንት ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ ከዘጠኙም ክልሎች የመጡ የባህል ቡድኖች የየአከባቢያቸውን ባህልና እሴቶችን በአደባባይ በማሳየት ባህል ለአንድነት፣ ለሰላም፣ ለልማት፣ ለዕውቀትና ለመልካም ገፅታ ግንባታ ያለውን ጠቀሜታ አጉልተው ያሳዩበት መድረክ ነበር ብለዋል፡፡ ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአማራና ከአዲስ አባባ የመጡ አንዳንድ የባህል ልዑካን ቡድን አባላት በሰጡት አስተያየት ፌስትቫሉ የእርስ በርስ ግንኙነትን የሚያጠናክር፣ ለዕውቀት ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ከመሆኑም ባሻገር ክልሎች የየራሳቸውን ዕምቅ የባህል ሃብቶቻቸውን ለማስተዋወቅና መልካም ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እንደረዳቸው ተ

በኢትዮጽያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ አዳማ ከነማናሲዳማ ቡና አንድ አቻ ተለያዩ

Image
በአዳማ ከተማ እየተካየደ ያለው የኢትዮጽያ  ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ  ውድድር ዛሬ ሚያዝያ 2/2005ዓ.ም  አዳማ ከነማናሲዳማ ቡና ተጫውተው አንድ አቻ ተለያዩ።  ዛሬ  በ10 ሰአት ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ከመከላከያ ነገ ማያዝያ 3/2005ዓ/ም ደግሞ ድሬዳዋ ከነማ ከደደቢት፤ ሃዋሳ ከነማከኢትዮጽያ መድህን ይጫወታሉ።

‹‹በሕዝብ የተመረጥኩ ነኝ›› ብሎ የሚያምን መንግሥት ‹‹ሕዝብ አለቃዬ ነው›› ብሎ ማመንም አለበት

Image
ሕገ መንግሥታችን ሥልጣን የሚይዝ መንግሥት በሕዝብ ድምፅ ብልጫ የተመረጠ መሆን አለበት ይላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ጉድለት አለው እንዲህ መሰል ችግር ነበረው ቢባልም፣ በተግባር ምርጫ የሚካሄድበት አገርና ሕዝብ ሆነናል፡፡ ምርጫ በማካሄድ መንግሥትን ሥልጣን ላይ ማስቀመጥ ማለትና ለገዥው ፓርቲ ሕዝባዊ ድምፅ ሰጥቶ በአመራር ላይ ማስቀመጥ ማለት ግን በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ኃላፊነት የማኖር ተግባር ነው፡፡ ኃላፊነቱም ሕዝብን በግዴታም በውዴታም የማገልገል ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕዝብ መንግሥትን የሚመርጠው፣ አመራርን የሚመርጠው፣ አስተዳደርን የሚመርጠው ‹‹አገልግለኝ›› ብሎ ነው፡፡ ስለሆነም በሕዝብ ተመርጦ ሥልጣን ላይ የተቀመጥኩ መንግሥት ነኝ የሚል ገዥ ፓርቲ አለቃዬ የመረጠኝ ሕዝብ ነው በማለት ማመን አለበት፡፡ በሕዝብ መመረጥ መብቴ ነው የሚል ገዥ ፓርቲ ሕዝብን ማገልገል ግዴታዬ ነው ብሎም ማመን አለበት፡፡ ሕገ መንግሥታችንም ያስገድደዋል፡፡ ሕዝብ አለቃዬ ነው፣ ሕዝብን ማገልገል ግዴታዬ ነው ብሎ የሚያምን መንግሥት ደግሞ የሕዝብን ጥያቄ ይመልሳል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኢሕአዴግ እንደ ገዥ ፓርቲ ራሱን መጠየቅ፣ መፈተሽና መገምገም ያለበት በእውነት የሕዝብን ጥያቄ እየመለስኩ ነው ወይ? ብሎ ነው፡፡ ሕዝብ መልካም አስተዳደር እንዲኖር እየጠየቀ ነው፡፡ ሕዝብ እንደ አለቃ መንግሥትን ሥልጣን ላይ ያስቀመጥኩህ መልካም አስተዳደር እንድታመጣልኝ ነው፡፡ የት አለ መልካም አስተዳደሩ እያለ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ደፈር ብሎ አዎን ሕዝብ ሆይ የሚገባኝን መልካም አስተዳደር ስላልሰጠሁህ ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ አሁን ግን አሟላለሁ ማለት አለበት፡፡ የት አቤት እንደሚባል እየጠፋ ነው፡፡ መልስ ሰጪ እየታጣ ነው፡፡ እንባ ሲፈስ እንጂ ሲታበስ አይ

የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን መሥራች ጉባዔ በተደበላለቀ ስሜት ተካሄደ

Image
-    ፋውንዴሽኑ የሚገነባበት ቦታ ቢለይም ዲዛይኑ አልተጠናቀቀም -    ፋውንዴሽኑ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ስጦታ አግኝቷል -    ለቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ቤት ለመገንባት ዲዛይኑ እስከሚፀድቅ እየተጠበቀ ነው ከሰባት ወራት በፊት በሞት የተለዩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታሰቢያ “መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን” መሥራች ጉባዔ መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተደበላለቀ ስሜት ተካሄደ፡፡ ፋውንዴሽኑ የአቶ መለስ ዜናዊ እሴቶችና መርሆዎች፣ በቀጣይነት ከትውልድ ትውልድ ይሰርፁ ዘንድና ቀጣይነት እንዲኖራቸው፣ ሐሳቦችና ፕሮግራሞች የሚፈልቁበት ህያው ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል “መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን” በሚል ስያሜ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ጥር 17 ቀን 2005 ዓ.ም. በአዋጅ እንዲቋቋም መደረጉ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም ፋውንዴሽኑን በአዋጅ ለማቋቋም ላለፉት ሰባት ወራት ሒደቱን የሚመራና የሚያስተባብር የሌጋሲ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተደርጎ፣ የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት፣ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ መሥራች ጉባዔውን ለማካሄድ መቻሉን የገለጹት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔና የሌጋሲው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ካሣ ተክለብርሃን ናቸው፡፡ በአጭር ጊዜና ዝግጅት፣ በአገር ውስጥ ከአርሶ አደር እስከ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ እንዲሁም ከአፍሪካ እስከ ዓለም ድረስ ላሉ የአቶ መለስ ወዳጆችና አድናቂዎች፣ የተደረገላቸውን ጥሪ አክብረው በፋውንዴሽኑ መሥራች ጉባዔ ላይ በመገኘታቸው ምሥጋናቸውን የገለጹት አቶ ካሣ፣ አቶ መለስ በሥራቸው በአኅጉር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታወሱ እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡ በእሳቸው የሕይወት ዘመን በአመራር ቦታ ላይ ለመድረስ የቻሉ ሰዎች ልብ ሊሉት የሚገባው ነገር እሳቸው በዘፈ

በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ሃዋሳ ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን ኣሸነፉ

Image
አዳማ ላይ እየተካሄደ ያለው የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በደማቅ ሁኔታ በብርቱ ፉክክር ታጅቦ መከናወኑን ቀጥሎ መጋቢት 29/2005 ሶስት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ በውድድሩ ስኬታማ ይሆናሉ ተብለው ቀዳሚ ግምት ከተሰጣቸው መሐል አንዱ የሆነው መከላከያ በሲዳማ ቡና ሳይጠበቅ 3ለ1 ተሸንፏል፡፡ ትብለጥ ሁለቱን ተራማጅ ቀሪዋን ጎል ለሲዳማ ቡና አስቆጥረዋል፡፡ የአዲስ አበባዎቹ ደደቢትና መድህን ባደረጉት ጨዋታም ደደቢት 3ለ0 አሸንፏል፡፡ ሰናይት ባሩዳ ሁለቱን ብርቱካን ገ/ክርስቶስ ደግሞ አንዷን ጎል ከመረብ አገናኝተዋል፡፡ በሌላው ጨዋታ ሐዋሳ ከነማ ድሬዳዋ ከነማን 3ለ1 ረቷል፡፡ እስከዳር አብዲ፣ ሮዛ ከድርና ዝናሽ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ መርሃ ግብር ሐሙስ ሲቀጥል ጠዋት 3፡00 ሰዓት አዳማ ከነማ ከሲዳማ ቡና ከሰዓት 10፡00 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመከላከያ ይጫወታሉ፡፡ http://www.ertagov.com/amharic/index.php/2013-03-11-06-12-23/item/402-%E1%8B%A8%E1%88%B4%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8D%95%E1%88%AA%E1%88%9A%E1%8B%A8%E1%88%AD-%E1%88%8A%E1%8C%8D-%E1%89%A0%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%89%B1-%E1%8D%89%E1%8A%AD%E1%8A%AD%E1%88%AD-%E1%89%B3%E1%8C%85%E1%89%A6-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B0%E1%89%80%E1%8C%A0%E1%88%88-%E1%8A%90%E1%8B%8D