Posts

Hawassa constructing 184 mln. Birr worth safe water project

Image
Hawassa March 14/2013 More than 184 million Birr worth safe water project is being carried out in Hawassa Town, South Ethiopia Peoples' State, the town administration water and sewerage department said Department Head, Letta Yetamo told ENA that upon going fully operational within a year, the project will benefit more than 450,000 residents. He said the budget for construction of the project is secured from the regional government, the town administration, international donor organizations and NGOs. Safe water service coverage will grow to 100 per cent from the present 76 per cent when the project goes operational. http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=6315&K=0

ደኢህዴን በአለታ ወንዶ ወረዳ ከ5ሺ800 በላይ ዕጩዎችን ለዉድድር አቀረበ

Image
ሃዋሳ መጋቢት 6/2005 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያ ንቅናቄ/ደኢህዴን/ በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የከተሞችና የአካባቢ ምርጫ በአለታ ወንዶ ወረዳ ከ5ሺህ 800 በላይ ዕጩዎችን ለዉድድር ማቅረቡን አስታወቀ ። በወረዳው የንቅናቄዉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሀላፊ አቶ ከበደ ቱሚቻ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በምርጫው ንቅናቄውን ወክለው ለመወዳደር ከተዘጋጁት መካከል ግማሽ ያህሉ ሴቶች ናቸዉ ። ንቅናቄዉ እጩ ተወዳደሪዎችን ለምርጫ ያቀረበዉ በህዝብ ካስገመገምና ብቁነታቸዉን በይሁንታ ካረጋገጠ በኋላ መሆኑን አስታዉቀዋል ። ድርጅቱ ካዘጋጃቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎች መካከል አምስቱ ለዞን ምክር ቤት፣ 87 ለወረዳ ምክር ቤቶች ቀሪዎቹ ደግሞ ለቀበሌ ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ መሆናቸዉን ገልጠዋል ። ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ ግልጽና በህዝብ ዘንድ አመኔታ አግኝቶ እንዲጠናቀቅ በንቅናቄው ደረጃ ሰፊ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን አቶ ከበደ ጠቁመው በቀጣይነትም ሀዝቡ በመብቱ ተጠቅሞ የመሰለውንና ይበጀኛል የሚለዉን እንዲመርጥ አሳስበዋል ። ንቅናቄዉ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር የጋራ ምክር ቤት አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን አመልከተው እስካሁን በምርጫው ለመሳተፍ የሚንቀሳቀስው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን/ ቢሆንም በምርጫው ከማይሳተፈው ከኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/ ጭምር በጋራ ምክር ቤቱ አብረዉ እየሰሩ መሆናቸዉን ገልጠዋል ። በሌላ በኩል ደግሞ በወረዳው ለሚካሄደው ለዚሁ ምርጫ 58ሺህ 854 ህዝብ ተመዝግቦ ለመራጭነት የሚበቃውን ካርድ መውሰዱን የወረዳው ምርጫ ጽህፈት ቤት አስተባበሪ አቶ ወርቁ አኔቦ አመልከተዋል፡፡ ለመራጭነት ከተመዘገበው ህዝብ ውስጥ ከ27 ሺህ የሚበልጡት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመው በዕጩ ተወዳደሪነትም ከደቡብ ኢትዮጵያ ህ

በሴቶች ጥሎ ማለፍ ሲዳማ ቡና ለግማሽ ፍፃሜ አለፈ

Image
በኢትዮጵያ ሴቶች ጥሎ ማለፍ ሲዳማ ቡና መብራት ሃይልን በመል ስ  ጨዋታ በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላል፡፡ መጋቢት5/2005 ይርጋለም ላይ በዝናባማው የአየር ሁኔታ ሲዳማ ቡና እና መብራት ሃይል ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡በጨዋታው ሲዳማ ቡና 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ በመጀመሪያ ጨዋታቸው መብራት ሃይል 1 ለ 0 ያሸነፈ ቢሆንም በደርሶ መልስ ሲዳማ ቡና 2 ለ1 በሆነ አጠቃላይ ውጤት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ከነማን ፣ደደቢት መከላከያን ፣ኢትዮጵያ መድህን ደግሞ ድሬዳዋ ከነማን በማሸነፍ ያለፉ ክለቦች ናቸው፡፡ በግማሽ ፍፃሜው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ መድህን ደደቢት ከሲዳማ ቡና ይገናኛሉ፡፡ ጨዋታዎቹ በሚቀጥለው ሃሙስ መጋቢት 13/2005 እንደሚካሄዱም ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል፡፡

SEPDM’s 8th regular session to review GTP implementation

Image
Addis Ababa, March 14 (WIC)  - The 8th regular session of the Southern Ethiopian People's Democratic Movement (SEPDM) will be held in Hawassa tow from March 17-20, 2013.  The conference would evaluate the two and half year performance of the Growth and Transformation Plan (GTP), according to organizing committee of the conference. Moreover, it will review efforts made to alleviate problems related to rent seeking mentality and good governance as well as put forth directions, it said.    �  The conference will also deliberate on ways of strengthening the public drive created to attain the vision of the late Prime Minister Meles Zenawi. The conference is expected to elect central and executive committee as well as pass various decisions. http://www.waltainfo.com/index.php?option=com_content&view=article&id=7608:sepdms-8th-regular-session-to-review-gtp-implementation-&catid=52:national-news&Itemid=291

የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከአለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገለጸ

Image
አዋሳ መጋቢት 05/2005 በምርምር፣ በመማር ማስተማርና በህብረተሰብ አገልግሎት በአለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን ከተለያዩ አለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በአሜሪካ ከሚገኘው ኬንታኪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለው የጋራ መግባቢያ ሰነድ ትናንት ተፈራርሟል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንና ማርከቲንግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር አቶ መልሰው ደጀነ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ጥራቱና ብቃቱ የተረጋገጠ ፍትሃዊና ተገቢነት ያለው የትምህርት፣ የምርምርና የህብረተሰብ አገልግሎት በመስጠት በአገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡ በዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን ትምህርት በጥናትና በፈጠራ ስራ በማስደገፍ፣ህብረተሰቡን በባለቤትነት በማሳተፍና አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር የተገኘውን ውጤት በአግባቡ ለመጠቀም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው ትምህርት ከኢኮኖሚ ፖሊሲው ጋር በማናበብ በኢኮኖሚ መዋቅር ውስጥ ገብተው በንቃት በመሳተፍ የተጀመረውን ዕድገት ማስቀጠል የሚችል ዜጋ ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዛሬውን ጨምሮ ከ30 በላይ በአፍሪካ ፣በአውሮፓና አሜሪካ ከሚገኙ አለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጥናትና ምርምር፣ በትምህርትና ስልጠና፣ በህብረተሰብ አገልግሎና በመምህራን ልማት ተባብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙን ጠቁመዋል፡፡ በዚሁም በርካታ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተለይ መምህራን የአጭር ፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስልጠና መውሰዳቸውንና የተወሰኑም አሁንም በመከታተል ላይ ናቸው ብለዋል፡፡ የዛሬው ስምምነት የዚሁ መርሀ ግብር አንዱ አካል መሆኑን የገለጹት አቶ መልሰው ኬንታኪ ስቴ