አነጋጋሪው የኢትዮጳያ የሰብአዊ መብቶች መርሃ ግብር
አቶ እንዳልካቸው የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ሰብአዊ መብትን ከ 23 ባላነሱ አንቀፆች አካቶ መያዙን አስታውሰው በተግባር ግን በተዘዋዋሪ መንገድ በህገ መንግሥት የተጠቀሱትን መብቶች የሚዳፈሩ ና የሚሸረሽሩ ሌሎች ህጎች መውጣታቸውን ይዘረዝራሉ ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች መርኀ ግብር አስፈላጊ ቢሆንም ተግባራዊ ይሆናል ብለው እንደማይጠብቁ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በምህፃሩ ሰመጉ ሃላፊና የአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባል አስታወቁ ። የሰመጉ ሃላፊ ና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ የአመራር አባል ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ከልምድ እንደተገነዘቡት ኢትዮጵያ ውስጥ ችግሩ ህግ ማውጣት ሳይሆን በህገ መንግሥቱ የተደነገጉት ሰብአዊ መብቶች ተግባራዊ አለመሆናቸውና ይህንንም ተከታተሎ ማስፈፀም አለመቻሉ መሆኑን ተናግረዋል ። በተለያየ ደረጃ ውይይት የተካሄደበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች መርሃ ግብር በቅርቡ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያፀድቀው ይቀርብለታል ተብሎ ይጠበቃል ። ሰነዱም ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበትና በሚኒስትሮች ምክርቤት ደረጃም እንደፀደቀ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት አስታውቀዋል ። ምንም እንኳን መንግሥት ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት በመርሃ ግብሩ ላይ ማወያየቱን ቢገልፅም የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በምህፃሩ ሰመጉ ግን ለውይይት አለመጠራቱንና የተባለው ሰነድም እንዳልደረሰው የሰመጉ ሃላፊ አቶ እንዳልካቸው ሞላ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ የሥራ አስፈፃሚ አባልና የትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ ጌታቸው ባያፈርስ ድርጅታቸው የመርሃግብሩን ሂደት በመከታተል ላይ መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። አቶ ጌታቸው ሌላው ቢቀር ሰመጉ ቢቻ