Posts

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት አራተኛ ዙር ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤ በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነዉ

Image
ሃዋሳ የካቲት 12/2005 በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በዘንድሮ ግማሽ በጀት ዓመት በየዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት የተመዘገበባቸው መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ ። የክልሉ ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት አራተኛ ዙር ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤ በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነዉ ። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የክልሉን የግማሽ በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ካለፈዉ ዓመት ክንውን በየስራ ዘርፉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመውሰድና በማስፋት እስትራተጂ በመጠቀም ውጤታማ ተግባራት ተከናወነዋል ። በመንግስትና በህብረተሰቡ የተሟላ ተሳትፎ የኪራይ ሰብሳቢነትን ችግሮች ለመቅረፍ በሚያሰችል መልኩ በገጠርና በከተማ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ለውጥ ማምጣት የተቻለ መሆኑን አስታዉቀዋል ። ባለፉት ስድስት ወራት በግብርና ልማት፣ በመንገድ ግንባታና በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ስራዎች የገጠር ቀበሌዎችን ዕርስ በዕርስና ከዋና መንገድ ጋር በማገናኘት 705 ኪሎ ሜትር መንገድ ተገንብቶ መጠናቀቁን አርሶና አርብቶ አደሩ ምርቱን ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል ። መንገዶቹ በሚገነቡባቸው አካባቢዎች በማህበር ለተደራጁና በጉልበት ሰራ ለተሰማሩ ከ106 ሺህ በላይ ሰዎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ጠቁመው ከ668 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ለመንገዱ ግንባታ ከ65 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነጻ የጉልበት አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። የትምህርት ጥራት ፍትሀዊነትና ተደራሽነት በማረጋገጥ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ለማስቻል እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በሚሰጡ ስልጠናዎች ጥራትና ተፈላጊነት ዙሪያ የታቀዱ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመዋል። በህዝብ ንቅናቄ የታጀበው

ከሲዳማ እና ቤንች ማጂ ዞኖች 106 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ተመርቶ ብሄራዊ ባንክ ቀረበ

Image
ሃዋሳ የካቲት 12/2005በደቡብ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት በባህላዊ መንገድ የተመረተ 106 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ መቅረቡን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ ገለጸ ፡፡ በቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ወርቁ ተሰብስቦ ለባንኩ የቀረበው ከቤንች ማጂና ሲዳማ ዞኖች ነዉ ። በባህላዊ መንገድ የተመረተዉ ወርቅ በህጋዊነት ተደራጅተው በሚንቀሳቀሱ 18 የወርቅ አምራቾችና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ለባንኩ መቅረቡን አስረድተዋል ። የዘንድሮዉ የግማሽ በጀት አመት ክንውን ከእቅዱ አኳያ ዝቅተኛ ቢሆንም ከ2001 ሙሉ በጀት አመት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ከሁለት ዕጥፍ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል ። በየዞኖቹ በባህላዊ መንገድ የሚመረተው ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ እንዳይባክን የግብይት ጣቢያዎችን ከማጠናከር ባሻገር የግብይት ስርዓት ህጋዊ መልክ በማስያዝና አቅርቦቱን በቀጣይ ለማሻሻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቢሮዉ ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን አቶ መላኩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=5642&K=1

አደናጋሪው የሕግ ቋንቋ ጉዳይ…

በውብሸት ሙላት የሕግ ቋንቋ በብዙ መልኩ የተቀዣበረ ነው፡፡ ቀዥባራነቱን አንዳንዶች እንደ ውበት ይወስዱታል፡፡ ሌሎች ደግሞ የሕግ ባለሙያዎች ብቻ እንደሚያውቁት የአስማት/የመተት ቋንቋ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ሌላም ሌላም ይሉታል፡፡ ለማንኛውም በእንግሊዝኛ ተናጋሪ አገሮች ዘንድ የግልጽ ቋንቋ ተሟጋቾች እየተበራከቱ በመምጣታቸው የሕግ ማኅበረሰቡ ግልጽ ቋንቋ ይጠቀሙ ዘንድ የሚያበረታቱ፣ እንዲጠቀሙ የሚሞግቱ የቋንቋና የሕግ ባለሙያዎች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በአገራችን ግን ስለዚህ ጉዳይ ስለመነሳቱ ይህ ጸሐፊ አያውቅም፡፡ በመሆኑም ስለሕግ ቋንቋ አንዳንድ ነገሮችን አንስተን እንወያያለን፡፡ መነሻ ወግ አንድ በዕድሜ ገፋ ካሉ የእግሊዝኛ ቋንቋ መምህርና ደራሲ ጋር እያወጋን ነው፡፡ በሕይወታቸው ሦስት ጊዜ የእንግሊዝኛ አንድ ጊዜ የአማርኛ የፍትሐ ብሔር ሕግ ኮድ (መጽሐፍ) ገዝተዋል፡፡ አራቱንም መጻሕፍት ለሕግ ባለሙያዎች ሰጥተዋቸዋል፡፡ የስጦታቸው ምክንያት በልገስና ስሜት ሳይሆን ከገዟቸው በኋላ ሲያነቧቸው ሊገቧቸው ስላልቻሉ በብስጭት ነው፡፡ በእልህ ገዟቸው በብስጭት ሰጧቸው፡፡ እስካሁን ለምን ያነበቧቸው እደማይገቧቸው ግልጽ አልሆነላቸውም፡፡ አንድ የጓደኛዬ ጓደኛ ከሚንስትር መለስ ባለ ደረጃ ቱባ ባለሥልጣን ነው፡፡ ከቱባ ባለሥልጣን ሚስቱ ጋር በመጣላቱ በፍች ትዳራቸውን ሊያፈርሱ ሆኖ በሚስቲቱ አመልካችነት ጉዳዩ ተጀምሮ የፍችው አቤቱታ መጥሪያ ይደርሰዋል፡፡ በአቤቱታው የመጀመሪያ ገጽ የክሱ መግለጫ በሚለው ክፍል ላይ እንዲህ የሚሉ ዓረፍተ ነገሮች ተቀምጠዋል፡፡ “1. በሕግ ችሎታ የለሽም አልተባልኩም፡፡ 2. ጉዳዩ በይርጋ አልታገደም፤” የሚሉ ዓረፍተ ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ ሁለተኛ ዲግሪ ያለው ቱባ ባለሥልጣን ሚስቱ እንፋታ ብላ ባቀረበችው አቤቱታ ላይ ከላይ የ

የግብርና ሚኒስቴር የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በድጋሚ ሊሰጥ ነው

ግብርና ሚኒስቴር ለሁለተኛ ጊዜ በአራት ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ 50 ሚሊዮን ማሳዎች በካዳስተር ካርታ የተደገፈ የገጠር መሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሊሰጥ ነው፡፡ የካዳስተር ካርታ ሥራውን የሚያካሂዱት የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ናቸው፡፡ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ጌታሁን፣ የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሡልጣን መሐመድና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ ነገር ግን የግብርና ሚኒስቴር ለዚህ ፕሮጀክት የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በእጁ ባለማስገባቱ ሥራው እንዳልተጀመረ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ግብርና ሚኒስቴር የሚያስፈልገውን ገንዘብ የዓለም ባንክ እንዲያቀርብለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ የዓለም ባንክ ገንዘቡን በቅርቡ እንደሚለቅ ምንጮችም ገልጸዋል፡፡ ገንዘቡ እንደተለቀቀ ደኅንነት ኤጀንሲ ማሳዎቹን የአየር ፎቶ ያነሳል፡፡ ያነሳውንም ፎቶ ለካርታ ሥራ ኤጀንሲ ያስረክባል፡፡ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ የማሳዎቹን ካርታ እንደሚሠራና ለሚኒስቴሩ እንደሚያስረክብ ታውቋል፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት መንግሥት በየክልሉ በባህላዊ የአሠራር ዘዴ በመጀመርያ ደረጃ የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በማዘጋጀት 90 በመቶ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ማደሉ ታውቋል፡፡ ነገር ግን ቀደም ሲል የቀረበው ካርታ የተጠናከረ መረጃ የማይሰጥ በመሆኑና በመጀመርያ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ላይ የነበሩበትን ክፍተቶች በማስተካከል እንደ አዲስ መረጃ የሚሰጥ ካርታ መስጠት እንደሚገባ ታምኖበታል፡፡ የገጠር መሬት አስተዳደር ሥርዓቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የካዳስተር የመሬት መረጃ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተኝቷል ተብሏል፡፡ አዲ

ለከተማ ኣስተዳደር ምክር ቤት ለሚካሄደው ምርጫ ሲኣን150 እጩዎችን ኣስመዘጋበ

Image
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ሚያዝያ ወር ለሚካሄደው ምርጫ የሚወዳደሩትን እጩዎች ይፋ አደረገ። ዛሬ ማምሻውን ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባገኘነው ጊዜያዊ መረጃ መሰረት  ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለመወዳደር 11 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል። በዚህም መሰረት ኢህአዴግ 138 ፣ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ  87፣ የመላው ኢትዮጵያውያን ብሄራዊ ንቅናቄ መኢብን 85 እንዲሁም የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ኢራፓም 14 እጩዎችን አስመዝግበዋል። የመላው ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መኦህዴፓ 14፣ የኢትዮጵያ የፍትህና የዶሞክረሲ ኃይሎች ግንባር ኢፍዴሃግ 9 ፣ የኢትዮጵያ ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢሰዴፓ 6፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ ኢዴአን 3፣ የገዳ ስርዓት አራማጅ ፓርቲ ገስአፓ 2 ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ 1 እጩዎችን ሲያመዘግቡ በድምሩም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 393 እጩዎች ተመዝግበዋል። አዲስ አበባ ላይ ለክፍለ ከተማ ምክር ቤት ኢህአዴግ 3ሺ 480 እጩዎቹን ሲያስመዘግብ ለወረዳ ምክር ቤትም እንዲሁ 34ሺ 794 እጩዎችን ነው ያስመዘገበው። ኦሮሚያ ክልል ላይም ለከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ ኢህአዴግ ፥ 2 ሺህ 205 እጩዎችን ሲያስመዘግብ ፤ መኦህዴፓ 5፣ እንዲሁም ገስአፓ 1 እንዲሁም አምስት የግል ተወዳዳሪዎችም እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል። ደቡብ ከልል ላይ ለከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለሚካሄደው ምርጫ ኢህአዴግ 1ሺህ 160 ፣ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ሲአን 150 ፣ ኢዴፓ፣ ኢፍዲሃግና ኢራፓም በድምሩ 12 እጩዎችን  ፣ የወላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ዎህዴግ 1 እንዲሁም ሁለት እጩዎችም በግ