በኢትዮጵያ የከተሞች በዓል ላይ የሃዋሳ ከተማ ተሳትፎ
ከተሞች ተሞክሯቸውን እየተለዋወጡ ናቸው ዜና ሐተታ አዳማ እንግዶቿን ማስተናገድ ከጀመረች ቀናትን አስቆጥራለች። ማዕዷን እያቋደሰች የምትገኘዋ አዳማ ገፅታዋን ለማስተዋወቅ የአራተኛው የከተሞች ሣምንት ኤግዚቢሽን ተሣታፊ ነች። ለሰባት ተከታታይ ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ የቆየው ኤግዚቢሽን 136 ያህል ከተሞች ወደ አዳማ ያመጣቸውን መገለጫዎቻቸውን በድንኳን በድንኳን ሆነው ራሳቸውን እያስተዋወቁ ናቸው። የአዳማና ዙሪያዋ ከተሞች በርካታ ነዋሪዎች ኢግዜቢሽኑን ይጐበኛሉ። ነዋሪዎቹ አዳማ በዘንድሮው የከተሞች ውድድር አንደኛ እንደምትወጣ ይገልፃሉ። የከተማዋን ገፅታ በኤግዚቢሽኑ እያስጎበኙ የሚገኙ አካላትም ይህንኑ ያጠናክራሉ። አቶ ዘላለም አስራት የአዳማ ከተማን ገፅታ ለማሳየት በተዘጋጀው ድንኳን ውስጥ ስለቀረቡት የተለያዩ ዝግጅቶች ሲያብራሩ «የአዳማ ከተማን ማስተዋወቅ ያስፈለገው ከከተሞች ሁሉ በመሪነት ቦታ ላይ እንድትቀመጥ ታስቦ ነው» ይላሉ። እንደ አቶ ዘላለም ማብራሪያ፤ የአዳማ ከተማ ከ63 ሺ በላይ አባላትን ያቀፉ ከ4ሺ 73 በላይ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አሏት። ከ280 ኪሎ ሜትር በላይ መንገዷ በአስፋልትና በኮብልስቶን ተሸፍኗል። ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል የሚያንቀሳቀሱ ከ700 በላይ ባለሀብቶች ይገኙባታል። አዳማ በቀን 45 ሺ የሚሆኑ ሕዝብ ገብቶ የሚወጣበት 7ሺ ያህል ሰዎች ደግሞ የሚያድሩባት ናት። 8ሺና ከዛ በላይ እንግዶችን ሊያስተናግዱ የሚችሉ የተለያዩ የስብሰባ ማዕከላት ያሏት ስትሆን። ይህም ከተማዋን የኮንፈረንስ ከተማ አሰኝቷታል። ለኢንዱስትሪ፣ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ለሪልስቴት፣ ለጤና፣ ለትምህርትና ለተለያዩ ዘርፎች የሚውል 128ነጥብ 70 ሔክታር መሬት ለልማት ማዘጋጀቷንም አቶ ዘላለም ይጠቁማሉ። የ