Posts

በሀዋሳ ከተማ ከ113 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ግብር ተሰበሰበ

Image
አዋሳ ጥቅምት 24/2005 በሀዋሳ ከተማ ባለፉት ሶስት ወራት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከ113 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ገቢ በመሰብሰብ ከእቅድ በላይ ማከናወኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ገለጸ፡፡ ከከተማው የሚሰበሰበው ገቢ አጠቃላይ ወጪን በሚሸፈንበት ደረጃ ላይ መድረሱም ተመልከቷል፡፡ የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ፈቃዱ ፍሰሃ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የተሰበሰበው ገቢ ቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች፣ ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች፣ ከማዘጋጃ ቤትና ሌሎች የግብር ዘርፎች ነው፡፡ ገቢው ከእቅዱ ጋር ሲነፃፀር በ13 ነጥብ 5 ሚልዮን ብርና ከዓምናው ተመሳሳይ ጊዜም እጥፍ ያህል ብልጫ እንዳለው ገልጸው ከተሰበሰበው ገቢ የተጨማሪ እሴት ታክስ 54 ነጥብ 5 ሚልዮን ብር እንደሚገኝበት አስታውቀዋል፡፡ ብልጫ ያለው ገቢ የተሰበሰበው ከዚህ በፊት በአስፈፃሚ ሰራተኞችና አመራሩ ላይ የሚታየው የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር በዲሲፕሊን እርምጃ ስርዓት እንዲይዝና ለግብር ከፋዩ ህብረተሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት ሁሉም ግዴታውን እንዲወጣ ጠንካራ የአሰራር አደረጃጀት በመዘርጋቱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በከተማው በተለያየደረጃ ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ቁጥር ከ10ሺህ 800 በላይ መድረሱን ጠቁመው በግብር ከፋዩ የሚቀርቡ ቅሬታዎች በአግባቡ የሚስተናገዱበት ግልፅ አሰራር መመቻቸቱን ገልጸዋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ሰፊ የኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚካሄድበትና ከዚህ የሚመነጨው የገቢ አቅም ከኪራይ ሰብሳቢነት በፀዳ አሰራር አሟጦ ለመጠቀም በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ገቢው በየዓመቱ ጨምሮ ባለፈው ዓመት ብቻ 250 ሚልዮን ብር መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡ መደበኛና ካፒታልን ጨምሮ 220 ሚልዮን ብር ወጪ በመሸፈን የተረፈው ለመንግስት ፈሰስ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ክልል ከ320 ሚልዮን ብር በሚበልጥ በጀት የድንጋይ ንጣፍ መንገድ ስራ ይካሄዳል ተባለ

Image
አዋሳ ጥቅምት 24/2005 በደቡብ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ320 ሚልዮን ብር በሚበልጥ ወጪ 123 ኪሎ ሜትር የድንጋይ ንጣፍ መንገድ ግንባታ እንደሚካሄድ የክልሉ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡ ግንባታው ከ36ሺህ ለሚበልጡ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጠር ተጠቁሟል፡፡ የቢሮው የመሰረተ ልማት አቅርቦትና አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ አምሩላህ ጠለሀ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የድንጋይ ንጣፍ መንገድ ግንባታ ስራው የሚከናወነው በክልሉ 14 ዞኖችና 4 ልዩ ወረዳዎች በሚገኙ 22 ከተሞች ነው፡፡ በበጀት ዓመቱ በሚገነባው የድንጋይ ንጣፍ መንገድ በሚፈጠረው የስራ ዕድል ከ36ሺህ በላይ ስራ አጥ ወጣቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በመጠቆም ከእነዚህም መካከል ወደ 13ሺህ የሚሆኑት ሴቶች ይሆናሉ ብለዋል፡፡ በከተሞች የሚሰራው መንገድ በአማካይ 8 ሜትር ስፋትና 123 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው እንደሚሆን ገልጸው የዚሁ ግንባታ ወጪ 140 ሚልዮን ብር በክልሉ መንግስት ቀሪው በከተሞች ማዘጋጃ ቤቶች፣ከአለም ባንክና ከጀርመን መንግስት ድጋፍ ነው ብለዋል፡፡ የድንጋይ ንጣፍ መንገድ ከአስፓልት የማይተናነስና በዝቅተኛ ወጪ ለረጅም ዓመታት ያለብልሽት የሚያገለግል ከመሆኑም ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ነባር መንገዶች፣ ጥርጊያና ጥገና፣ የጎርፍ መውረጃ ቦዮች ግንባታና ማሻሻያ፣ የቱቦ ቀበራ፣ የእግረኛ መተላለፊያ ፣ የመንገድ መብራትና የውሃ መስመር ዝርጋታን ጨምሮ ከ2ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የመሰረተ ልማት ስራዎች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡ በደቡብ ክልል ባለፈው በጀት ከ146 ሚልዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ከ59 ኪሎ ሜትር በላይ የድንጋይ ንጣፍ መገንባቱንና ከ26ሺህ ለሚበልጡ ወጣቶ

ሀዋሳ መንገድ ላይ ትልቅ ኣየር ማረፊያ ልገነባ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ለሚገነባው አውሮፕላን ማረፊያ ድጋፋቸውን ሰጡ -     የቦሌ መንገደኞች ተርሚናል ማስፋፊያ ሥራ ሊካሄድ ነው በቃለየሱስ በቀለ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በሞጆ አካባቢ ለመገንባት ላቀደው ግዙፍ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ድጋፋቸውን ገለጹ፡፡ የኤርፖርቶች ድርጅት አንድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢንተርፕራይዙን በኤርፖርት ግንባታው ዕቅድ ላይ ቀጣይ ሥራ እንዲሠራ መመርያ ሰጥተውታል፡፡ አዲስ ስለሚገነባው ኤርፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ በቅርቡ የሰጡት የትራንስፖርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ናቸው፡፡ የአዲሱ ኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት ዕቅድ በቅርቡ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ የሚፀድቅ ሲሆን፣ በመቀጠል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል፡፡ ለፕሮጀክቱ የሚሆን ገንዘብ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ እንደሚጠየቅ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መገንባት ያስፈለገበት ምክንያት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እየተጨናነቀ በመሆኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፍጥነት በማደጉና በርካታ አውሮፕላኖች በመግዛት ላይ በመሆኑ፣ የተለያዩ አገሮች አየር መንገዶች ወደ አዲስ አበባ በረራ መጀመራቸው ለኤርፖርቱ መጨናነቅ እንደ ምክንያት ተቆጥሯል፡፡ በተጨማሪም መደበኛ የበረራ አገልግሎት፣ ጄነራል አቪዬሽን (መደበኛ ያልሆነ የቻርተር በረራ አገልግሎት) እንዲሁም የ‹‹ቪአይፒ›› በረራዎች በአጠቃላይ በአንድ ኤርፖርት መስተናገዳቸው የሥራ ጫና ፈጥሯል፡፡ በተለይ እንደ ሴስና ያሉ ትናንሽ አውሮፕላኖችንና እንደ ቦይንግና ኤርባስ ዓይነት ትላልቅ አውሮፕላኖችን በአንድ ኤርፖርት

ከአሥር ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ 15 ቢሊዮን ዶላር መውጣቱ ተረጋገጠ

•    ካቻምና ብቻ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ታጥቷል በአስራት ሥዩም እ.ኤ.አ. ከ2001 እስከ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ሕጋዊ በሆነና ባልሆነ መንገድ ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ተደርጎ ወደ ውጭ ገበያዎች ማምራቱን በቅርቡ ይፋ የሆነ ሪፖርት አመለከተ፡፡ ይህ ችግር በመላ አፍሪካ ትኩረት እየሳበ እንደመጣ ታውቋል፡፡ የፋይናንስ ምንጭ በእጅጉ ከሚያስፈልጉዋቸው ታዳጊ አገሮች ወደ ሌሎች አገሮች ገንዘብን በማዘዋወርና በሕገወጥ የፋይናንስ ግብይት እየወጣ ያለውን ሀብት በተመለከተ እ.ኤ.አ. ከ2009 ጀምሮ ሲወጡ የነበሩ ሪፖርቶች የሚያረጋግጡት፣ ክስተቱ ትኩረት እየሳበ መምጣቱን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ያላትን ውስን የውጭ ምንዛሪ መጠን ይኼው ከፍተኛ የካፒታል ማዛወር ወይም ማሸሽ ተግባር በእጅጉ እየታየባት በመምጣቱ፣ የመነጋገርያ አጀንዳ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ ተሻሽለው የወጡ አኀዞች እንደሚያመለክቱት፣ እ.ኤ.አ. ከ1970 እስከ 2010 በነበሩት ሰላሳ ዓመታት 24 ቢሊዮን ዶላር ከኢትዮጵያ እንዲሸሽ ተደርጓል፡፡ ገንዘብ በከፍተኛ መጠን እየሸሸ መሆኑ ከተመዘገበባቸው ጊዜያት ትልቁን ድርሻ መያዝ የጀመረው እ.ኤ.አ ከ2000 በኋላ ያለው ሲሆን፣ በተለይ እ.ኤ.አ. በ2010 ብቻ 3.5 ቢሊዮን ዶላር በአገሪቱ ኢንቨስት ያደረጉ የውጭ ባለሀብቶች ያሸሹት ገንዘብ (ካለፈው ዓመት ኅዳር ወር አኳያ ከአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በላይ ሆኖ ተመዝግቧል) በከፍተኛነቱ ሲጠቀስ፣ ከዚህ መጠን ቀጥሎ የተመዘገበው ከፍተኛ የገንዘብ ማሸሽ እ.ኤ.አ. በ2002 የታየው የ3.1 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ በሪፖርቱ የቀረቡት መረጃዎች ሲፈተሹ፣ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የካፒታል ማሸሽ የተመዘገበባቸው ጥቂት ዓመታት ሆነው ይገኛሉ፡፡ ካፒታል የማሸሽ መጠ

‹‹የዳኝነት ሥርዓቱ ራሱን ከመቆጠብ መውጣት ይኖርበታል››

Image
አቶ ጌታሁን ካሣ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብት ማዕከል መምህር አቶ ጌታሁን ካሣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብት ማዕከል መምህር ናቸው፡፡ የትግራይ ብሔራዊ ክልል የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ፣ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ እንዲሁም የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ አባል በመሆንም ለሁለት የሥራ ዘመኖች አገልግለዋል፡፡ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤትም በመምህርነት ሠርተዋል፡፡ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከእንግሊዝ ኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብት ማዕከል በሰብዓዊ መብት ዙሪያ የፒኤችዲ ምርምራቸውን በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡  ሰለሞን ጎሹ  በዳኝነት ነፃነትና በሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ላይ አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያ የፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ዳኞች ምን ዓይነት ሚና ነው ያላቸው? አቶ ጌታሁን ፡- ከ1948 ዓ.ም ጀምሮ ያሉትን ሕገ መንግሥቶች ወይም ከዚያ በፊት የነበሩትን ሁኔታዎች ስንመለከት የዳኝነት ተቋማት ሥራ በዋነኛነት በሚነሱ ጉዳዮች ላይ የሁለት ወገኖችን ክርክርና ማስረጃ በመመልከትና በማገናዘብ ውሳኔ መስጠት ነው፡፡ የመንግሥት አደረጃጀትን በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ በሥልጣን ክፍፍል መርህ ስናይ ግን በሦስት እንከፍላለን፡፡ ሕግ አውጪው፣ ሕግ ተርጓሚውና ሕግ አስፈጻሚው ይኖራሉ፡፡ በአገራችንም እነዚህ የመንግሥት አካላት አሉን፡፡ አንዱ በአንድ ወቅት ከነበረው የሚለይበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ የተለያዩ ገጽታዎችም አሏቸው፡፡ ለምሳሌ የተጻፈ ሕገ መንግሥት ከኖረን ጊዜ ጀምሮ ያለውን ብንመለከት የዳኝነትና የሕግ አስፈጻሚነት ሥልጣን በአንድ አካባቢ ተደራርቦ የምናገኝበት ሁኔታ ነበር፡፡ አሁን ባለው