“ቦተሊካ”ና ነጻ ነገር…
Written by ኤፍሬም እንዳለ እንዴት ሰነበታችሁሳ! ለእስልምና ተከታዮች በሙሉ ኢድ ሙባረክ! ይመቻችሁማ! እኔ የምለው…የእነኚህ፣ አለ አይደል…”ሪሞት ኮንትሮሉን” ይዘውብናል የሚባሉት አሳዳሪዎቻችን የምርጫ ክርክር አሪፍ አይደል! እንደዛ ልክ ልካቸውን “አጠጥተውና ጠጥተው” ሲተቃቀፉ ማየት መአመት ነገር እንድትናፍቁ አያደርጋችሁም! እኛ አገር እኮ…አለ አይደል…አይደለም “ቦተሊከኞች”፣ ኳስ ተጫዋቾች እንኳን የጨዋታው መጨረሻ ፊሽካ ሲነፋ ጀርባቸውን አዙረው ወደ መልበሻ ቤት አይደል እንዴ የሚሄዱት!እናማ…”ቦተሊከኞች” በሆዳቸው “እንዲህ ብለኸኝማ፣ የተወለድክበትን ቀን ባላስረግምህ…” ምናምን አይነት እየዛቱ የሚሄዱ ነው የሚመስለው፡፡ ድሮም እንዲያው ነን…ዘንድሮ ደግሞ ብሶብናል፡፡ ስሙኝማ…የዘንድሮ “ቦተሊከኝነት” ለምን ይናፍቅሃል አትሉኝም…ነፃ “ፉድና ድሪንክ”! ልጄ ቀላል ግብዣ አለ እንዴ! ወላ አሮስቶ ዲቢቴሎ፣ ወላ ስቴክ በያይነቱ፣ ወላ ስቶሊችኒያ…ምን አለፋችሁ የሦስተኛው ዓለም “ቦተሊከኛ” ዝም ብሎ በባዶ ሜዳ ፊቱ የቅቤ ቅል የሚሆን አይምሰላችሁ! በ “ፍሪ ፉድ”ማ እኛም ቅል (የቤውን ለማለት ነው፡፡ ቂ…ቂ…ቂ…) የማንመስልሳ! ኮሚክ እኮ ነው…ዘንድሮ ነፍስ ያለው ምግብ በመጽሔት ማስታወቂያና በአረብ ሳት ጣቢያዎች ላይ ብቻ እያየን…በ’አቋራጭ የሚበላበትን የማንመኝሳ! እናማ…አንዳንዴ የግብዣውን ብዛት ስታዩ…አለ አይደል…አንዳንድ ቦሶች “እሺ፣ ጤፍ ለምን፣ ለምን ያገለግላል?” ተብሎ ይጠይቁ፡፡ ምን አለ በሉኝ፣ አንዳንዶቹ…ለአርባ አራት ደቂቃ ካሰቡ በኋላ ትዝ ብሏቸው…”እሱ ነገር አሁንም አለ እንዳትሉኝ!” ባይሉ ምን አለ በሉኝ፡፡ (“ከምላሴ ፀጉር…” መባባል የቀረው ምላሳችን ፀጉር ባይኖረውም “በመኮሰኮሱ” ነው እንዴ!) ኑሮ እንዲህ የሆረር ፊልም በ