Posts

የሲዳማን እና የወላይታን ባህላዊ ኣስተዳደር ስርኣት ብሎም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የምጫዎቱትን ሚና የሚያወዳድር መጽሃፍ ገበያ ላይ ዋለ

Image
ከኣጸ ሚኒልክ ዘመን በፊት ጀምሮ ያለውን የሲዳማ እና ወላይታ ባህላዊ ኣስተዳደር ስርኣት ብሎም ኣወቃቀር የምገመግመውን ይህን መጽሀፍ ለማንበብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ፦ The Politics of Ethnicity in Ethiopia: Actors, Power and ...

የዲሞክራሲያዊ ልማት ውርስ

Image
በሰለሞን ጎሹ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን በራሳቸው ልዩ ባህሪያትና እንቅስቃሴዎች ላይ ተመሥርቶ ከመፈረጅ ይልቅ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ማነፃፀር እየተዘወተረ ነው፡፡ ለዚህ አንዱ ምክንያት ራሳቸው ኃይለ ማርያም መለስን ከአንደበታቸው አለማራቃቸው ነው፡፡ በኢኮኖሚ ዕውቀታቸው ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸራቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሰፋ ያለ የኢኮኖሚ ትንታኔ የመስጠት ልማድ የነበራቸው ሲሆን፣ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያና ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ባደረጉት ውይይት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ዝርዝር የኢኮኖሚ ትንታኔ ውስጥ ከመግባት ይልቅ አንኳር ጉዳዮች ላይ ብቻ ማተኮር መርጠዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም አካሄድ የኢትዮጵያን ልማታዊ መንግሥት ርዕዮተ ዓለም ከዲሞክራሲ ጋር ካለው ግንኙነት አንፃር የሚነሱትን የተለያዩ ጥያቄዎች እንዴት አድርጎ ያስተናግዳል የሚል ጥያቄም መነሳቱ አልቀረም፡፡ ዲሞክራሲያዊ ልማት ኢትዮጵያ የልማታዊ መንግሥት ጽንሰ ሐሳብን ከምሥራቅ እስያ አገሮች ከመገልበጥ ይልቅ በሒደት ልታረጋግጠው የተነሳችበትን ዲሞክራሲ በመጨመር ‘ዲሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግሥት’ ለመመሥረት መወሰኗ በይፋ የተገለጸው የሚሊኒየምን በዓል ባከበረችበት የ2000 ዓ.ም. መባቻ ላይ ነበር፡፡ ልማታዊ መንግሥታት በመንግሥት ጣልቃ ገብነት፣ ሰፊ ቁጥጥርና ዕቅዶች እየታገዙ የሚጓዙ ሲሆን ነፃ ገበያ፣ ብሔራዊ ስሜት፣ የውጭ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ሰፊ የመንግሥት ቢሮክራሲ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሕዝብ ተቀባይነት፣ ከልሂቃን ጋር አብሮ የመሥራት ባህል፣ ከግል ዘርፉ ጋር ተባብሮ ማደግ፣ ማኅበራዊ ፍትሕ፣ የሕግ የበላይነት፣ የሚዲያና የሲቪል ማኅበራት ተሳትፎና የሙያና የብዙኅን ማኅበራት እንቅስቃሴ ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሁኔ

Hawassa: An African City

Image
By Bridget Boynton This past week, I took a  four-day trip to the southern city of Hawassa. Going by bus, the journey took about 5 and a half hours each way. Before leaving, I can't say I knew much about the city or its environs. To be more precise, I had heard from friends that it offers beautiful countryside scenery, there is a lake, and lots of animals. Sounds nice, but not very telling of the deeper culture that defines the city. I also knew from doing some rudimentary research that the city is part of the homeland of the Sidama people, an indigenous culture of the region. But that pretty much summarizes my knowledge of Hawassa prior to embarking on my journey. Scarce at best; I was in for many surprises. When I reflect at the image I formulated in my head of Hawassa before arriving in the city, I see a picturesque postcard image of a vast lake, sprawling hills, and an abundance of flora and fauna. I also envisioned circular huts, dusty roads, and marketpla

የቴዲ አፍሮ የሐዋሳ ኮንሰርት ለሳምንት ተላለፈ

Image
ስቴዲየሙ ለጨዋታ ተፈልጓል በዛሬው ዕለት በሐዋሳ ከተማ ሊደረግ ታቅዶ የነበረው የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ኮንሰርት ስቴዲየሙ ለኳስ ጨዋታ በመፈለጉ ተሰርዞ ለሚቀጥለው ቅዳሜ ተላለፈ፡፡ የቤለማ ኢንተርቴይመንት የፕሮሞሽን እና ኢቬንት ሐላፊ አቶ ምኞት ኃይሉ (ዲጄ ዊሽ) ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው፤ ቤለማ ኢንተርቴይመንት በዛሬው ዕለት በሐዋሳ ከተማ ትልቅ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ አስቦ ዝግጅቱን ካጠናቀቀ በኋላ ኮንሰርቱ ሊደረግበት የታቀደው ስታዲየም ለኳስ ጨዋታ ይፈለጋል በመባሉ ዝግጅቱ ለጥቅምት 24 ቀን 2005 ዓ.ም ሊተላለፍ ችሏል፡፡ ዝግጅቱ በዕለቱ ሊደረግ ከታቀደ በኋላ ለፕሪሚየር ሊግ ዕጣ ሲወጣ የሐዋሳ ከነማ እና የመድሕን ጨዋታ ጥቅምት 17 ቀን 2004 ዓ.ም በሐዋሳ ስታዲየም ስለወጣላቸው ኮንሰርቱ ሊተላለፍ እንደቻለ ታውቋል፡፡ የዝግጅቱ ቀን በመተላለፉ ለማስታወቂያ ከወጣው 42 ሺህ ብር ውጭ ምንም ዓይነት ኪሣራ አለመድረሱን የገለፀው ዲጄ ዊሽ፤ በቀኑ መተላለፍ ምክንያት ተፈጥሮ የነበረው ትልቅ ስጋት የአርቲስት ቴዲ አፍሮን ፕሮግራም አለማወቃቸው መሆኑን ጠቁሞ፤ ሆኖም አርቲስቱ እና ዛየን ባንድ ትልቅ ትብብር እንዳደረጉላቸው ገልጿል፡፡

ተቃዋሚዎች የምርጫው ሜዳ መስተካከል አለበት አሉ

በመጪው ሚያዚያ ወር በሚደረገው የአካባቢ ምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ላይ ምርጫ ቦርድ ከ75 ፓርቲዎች ጋ ከትላንት በስቲያ የመከረ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከጊዜ ሰሌዳው በፊት መቅደም ያሉባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ገለፁ፡፡የምርጫ አጃቢና አሯሯጭ መሆን ስለማንፈልግ የምርጫው ሜዳ መስተካከል አለበት ብለዋል - ተቃዋሚ ፓርቲዎች፡፡ሃያ አንድ ነጥቦችን ባካተተው የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የአንድነት ፓርቲ ሃላፊ አቶ አስራት ጣሴ፤ የፖለቲካ ምህዳሩ በተጣበበበትና የፕሬስ ነፃነት በሌለበት ሁኔታ ነፃ፣ ግልጽና ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ የማይታሰብ ነው ብለዋል፡፡ ወደ ጊዜ ሰሌዳ ውይይት ከመገባቱ በፊት የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡ ከህዳር 17 ጀምሮ የወረዳ የምርጫ ጽ/ቤቶች ተከፍተው ስራ እንደሚጀምሩና ሚያዚያ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ምርጫው እንደሚደረግ የጠቀሱት አቶ አስራት፤ ከጊዜ ሰሌዳ በፊት መቅደም ያሉባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁመው፤ አጃቢ እና አሯሯጭ ሳይሆን ነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ምርጫ ላይ መሳተፍ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩ ከሰፋና ሌሎች ችግሮች ከተፈቱ አንድነትና መድረክ በአካባቢ ምርጫ እንደሚሳተፉ ገልፀዋል፡፡ የኢዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ወንድወሰን ተሾመ በበኩላቸው፤ ከጊዜ ሰሌዳው በፊት የምርጫው ሜዳ መስተካከል አለበት ብለዋል - “የመራጮች ምዝገባ እና የፓርቲዎቹ የምርጫ ክርክር ጊዜ የተጣጣመ አይደለም” በማለት፡፡ ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ያሉትን ችግሮች አጽድቶ የተመቻቸ የምርጫ ሜዳ እንዲፈጠር ጠይቀዋል - አቶ ወንድወሰን፡፡ http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=3019:%E1%89%B0%E1%89%83%