የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ስለምርጫ ሥነ ምግባር አዋጁና ድርድር ምን ይላሉ?
‹‹የሥነ ምግባር አዋጁን ፈርመን ብንደራደር በግሌ ችግር የለብኝም›› አቶ ግርማ ሰይፉ (መድረክ) ‹‹እንደ ዜጋ አዋጁን አከብራለሁ አስገድደው ሊያስፈርሙን ግን አይችሉም›› ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (መድረክ) ‹‹አጠቃላይ መፍትሔ አምጪ ባይሆንም አንድ ዕርምጃ ነው›› አቶ ሙሼ ሰሙ (ኢዴፓ) ‹‹አዋጁን ፈርመን ብንቀበልም ያስከበረልን ነገር ስለሌለ ከጋራ መድረክ ወጥተናል›› አቶ ወንድማገኝ ደነቀ (መኢአድ) በዮሐንስ አንበርብር የፓርቲዎች የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ የበርካታ ፓርቲዎች ይሁንታን አግኝቶ ከፀደቀ ሦስት ዓመታት ያለፉት ቢሆንም፣ ይህ የሥነ ምግባር አዋጅ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሒደት ውስጥ ካበረከተው አስተዋጽኦ ይልቅ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ፈተና የሆነ ይመስላል፡፡ አንዳንዶቹ በአዋጁ ዙሪያ እርስ በእርስ አይግባቡም፤ ሌሎች ደግሞ አዋጁን ፈርመን የገባንበት የድርድር መድረክ ያመጣልን ነገር የለም ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በተቋቋመው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተሳታፊ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥታቸውን አቋም ባለፈው ማክሰኞ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ከመድረክ ፓርቲ ለቀረበላቸው የድርድር ጥያቄ የኢሕአዴግንና የሚመሩትን መንግሥት አቋም አሳውቀዋል፡፡ መድረክ ከኢሕአዴግ ጋር ለመወያየት በመጀመሪያ የሥነ ምግባር አዋጁን መፈረም አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የውይይት መድረኩ የተዘጋ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ይህንን አስመልክቶ የመድረክ አመራሮችን ያነጋገርን ሲሆን፣ መድረክ በተሰጠው ምላሽ ላይ ተነጋግሮ አቋም ያለመያዙን ለመረዳት ተችሏል፤ አመራሮቹ ግን እርስ በርሳቸው በጉዳዩ ላይ ያላቸው አቋም የተለያየ ነው፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመድረክ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ድርድር ለመጀመር የቀረበው