የሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች
ከታዛቢው ሲኣን በሲዳማ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት ያለፈ ስራ ስሰራ ኣይታይም የሲዳማ ዲያስፖራ የፖለቲካ ድርጅቶች የኢንተርኔት ላይ ኣንበሶች ናቸው ይሄ ቀጥዬ የማቀረበው ኣስተያየት የእኔ የግሌ ኣስተያየት ነው። ምናልባት በእኔ ማንነት ላይ ጥርጣሬ ቢኖር እኔ የመንግስት ደጋፊ ወይም ተቃዋሚም ኣይደለሁ፤ እንዲሁም የተቃዋሚዎች ደጋፊም ሆነ የተቃዋሚዎች ተቃዋሚም ኣይደለሁ። እኔ የሲዳም ህዝብ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መብቶች ስከበሩ ማየት የምሻ የሲዳማ ህዝብ ተቆርቋር ነኝ። እባካችሁ ከዚህ ባለፈ ሌላ ስም ኣትለጥፉብኝ ኣደራ። ስለ እራሴ ይህንን ያህል ካልኩ ወደ ጉዳዬ ልለፍ፦ በተለይ ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ ሲዳማ በፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ ናት ማለት ይቻላል። በተለይ ከክልል ጥያቄ እና ከሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣ ፋንታ በምወሰኑ ጉዳዮች ላይ ህዝቡ ከመንግስት ጋር ተፋጦ መክረሙ ይታወሳል። ታዲያ ይህ ፍጥጫ ከፍጥጫነት ኣልፎ ወይም ኣፍትልኮ የወጣበትም ኣጋጣም ተከስቶ ነበረ በተለይ በወረዳዎች ኣከባቢ። የሆነ ሆኖ ዛሬ ግን ፍጥጫው እየረገበ ያለ ይመስላል። ይህንን ያነሳሁት ያለፈ ታሪክ ልተርክላችሁ ብዬ ኣይደለም፤ ያነሳሁበት ዋናው ምክንያት ስለ ሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የታዘብኩትን ጀባ ልላችሁ ብየ ነው። ምን ታዘብክ ብላችሁ ጠይቁኝ ታዲያ ! ኣዎን የሲዳማ የፖለቲካ ድርጅቶችን ብዙ እየታዘብኩ ነው። ለመሆኑ የሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች እነማናቸው ? ይመስለኛል ስለ ፓርቲዎቹ ማውራታችን ካልቀረ ስለ ማንነታቸው በስሱ ማንሳቱ የግድ ይመስለኛል። እኔ ከልጅነተ ጀምሮ የማውቀው ኣንዳንዴ ስለው ተቃዋሚ ስለው ደግሞ የመንግስት ደጋፊ እየሆነ ሁለት መልክ የሚይዘው የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ( ሲኣን ) ከቀድሞው ሲ