Posts

SIDAMA ECONOMY

Image
Dr. Wolassa L. Kumo The Sidama economy is based primarily on the subsistence agriculture characterized by archaic production techniques. However, a substantial area of the Sidama land produces coffee , which is the major cash crop in the region. Coffee has been the major source of income for the rural households in the coffee producing regions of the Sidama land. However,the recent plunge in international coffee price drew most of these households back into the subsistence production and absolute poverty(coffee prices fell dramatically even during the commodity price boom of 2001 to mid 2008). Sidama is one of the major coffee producing regions in Ethiopia. It supplies over 40% of washed coffee to the central market. Coffee is the single major export earner for the country.Export earnings from coffee ranges from 60-67% although the country's share in the world market is less than 3%.  The Sidama people have never faced major hunger and famine until very recently. Due to

Sidama Zone

Image
From Wikipedia, the free encyclopedia A map of the regions and zones of Ethiopia. Sidama  is a Zone in the  Ethiopian   Southern Nations, Nationalities and Peoples Region  (SNNPR). It is named for the  Sidama people , whose homeland is located in this zone. Sidama is bordered on the south by the  Oromia Region  except for a short stretch in the middle where it shares a border with Gedeo , on the west by the  Bilate River  which separates it from  Wolayita , and on the north and east by the Oromia Region. The administrative center for Sidama is  Awasa ; other towns include  Irgalem  and  Wendo . Sidama has 879 kilometers of all-weather roads and 213 kilometers of dry-weather roads, for an average road density of 161 kilometers per 1,000 square kilometers. [1] The  Central Statistical Agency  (CSA) reported that 63,562 tons of coffee were produced in Sidama and Gideo combined in the year ending in 2005, based on inspection records from the Ethiopian Coffee and

በደቡብ ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ትኩረት ተሰጥቷል

Image
አዋሳ፡- በደቡብ ክልል የተደራጀ የትምህርት ሠራዊት በመገንባት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳካት ትኩረት እንደተሰጠው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ትናንት በአዋሳ ከተማ ሲዳማ ባህል አዳራሽ የተጀመረውን የክልሉን 18ኛ የአጠቃላይ ትምህርት ጉባዔ በንግግር ሲከፍቱ እንደገለጹት፤ በተያዘው የበጀት ዓመት በክልሉ የተደራጀ የትምህርት ሠራዊት በመገንባት ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት በትኩረት ይሰራል። የትምህርት ሥርዓቱ ብቃት ያለውና የተደራጀ ባለሙያ የሚያፈራ መሆን እንዳለበት የገለጹት አቶ ሽፈራው፤ የትምህርት ጥራት ተማሪዎች ውጤታማ ሆነው ለራሳቸው እና ለሀገራቸው በሚያበረክቱት አስተዋፅኦ እንደሚለካ ተናግረዋል። የትምህርት ጥራት ተጠብቆ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል አመራሩ የትምህርት ሥራውን በባለቤትነት መምራት እንዳለበት አሳስበዋል። እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለፃ፤ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የትምህርት ሠራዊት ግንባታ እንዲካሄድ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ይኖርባቸዋል። በ2004 ዓ.ም በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ሥራዎች በተማሪው ውጤት ላይ በተወሰነ ደረጃ መሻሻል ታይቷል። በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች የተማሪዎችን ውጤት አሁን ካለበት ደረጃ ለማሳደግ በርካታ ሥራዎችን ማከናወን ያስፈልጋል። ሕፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን በአካባቢያቸው እንዲያገኙ ለማድረግ በ2004 ዓ.ም የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በክልሉ በሚገኙ 958 ቀበሌዎች እስከ 8ኛ ክፍል የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውን አቶ ሽፈራው አስረድተዋል። ትምህርት ቤቶች ያልተከፈቱባቸው ቀበሌዎች እንዳሉ ጠቁመው፤ በተያዘው የበጀት ዓ

ባለፉት ሁለት ዓመታት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የተጀመረው ጥረት ውጤት እያስገኘ ነው-ሚኒስትር ደሴ

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 6/ 2005 ባለፉት ሁለት ዓመታት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የተጀመረው ጥረት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አስታወቁ። የቅጂ መብት ጥሰት መጠን ከ95 በመቶ ወደ 65 በመቶ መውረዱንም ገልጸዋል። ሚኒስትሩ አቶ ደሴ ዳልኬ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ የተጀመረውን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ዘላቂነት እንዲኖረው ጠንካራ አገራዊ የቴክኖሎጂ አቅም የመገንባቱ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአገሪቱ የውጭ ቴክሎጂዎችን የመማር የማላመድና የመጠቀም አቅም አሁንም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም፤ ባለፉት ሁለት አመታት ግን አመርቂ የሚባል መሻሻል ተመዝግቧል። ፈጣኑን የኢኮኖሚ እድገት በሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀት እንዲታገዝ አገራዊ ጥረት እየተደረገ መሆኑንምተናግረዋል። የዩኒቨርሲዎችና የኢንዱስትሪዎች ትስስርን ከማጠናከር አኳያም የተሻለ ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል። አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማፈላለግ የማስገባትና የመጠቀም አቅምን የሚያዳብሩ የአሰራር ሥርዓቶች በመዘርጋታቸው ቴክኖሎጂን በማዛመድና በመቅዳት ረገድ ጥሩ ጅምሮች እየታዩ ስለመሆኑም አስረድተዋል። ቴክኖሎጂን አስመስሎ በመስራት ከውጭ የሚገቡትን በአገር ውስጥ በማስቀረት ረገድም ተስፋ የሚሰጥ ውጤት እየታዬ መሆኑን ሚኒስትሩ አስረድተዋል። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ቅበላ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ኃይል ልማት ፍላጎት ጋር እንዲጣጣምና የተግባር ስልጠናውም ከማምረቻና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር የማስተሳሰሩ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል። እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ ከሆነ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የቅጅ መብት ጥሰትን ለመቆጣጠር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተካሄደው የጋራ ጥረት የሚያበረታታ ውጤት ተገኝቷል። 

መንግሥት ባከናወናቸው ተግባራት የዋጋ ግሽበቱ ወደ 19 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ገለጹ

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 6/2005 መንግሥት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ባከናወናቸው ተግባራት ባለፈው ዓመት የዋጋ ግሽበቱ ከ40 በመቶ ወደ 19 በመቶ ዝቅ ማለቱን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ መስከረም 28 ቀን 2005 የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ላይ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት በቀረበው የማሻሻያ ሞሽን ላይ ተወያይቶ አጽድቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ እንደገለጹት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር መንግሥት በገበያ ውስጥ ያለውን የገንዘብ መጠን በመቆጣጠር፣ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግና የንግድ ሥርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት የዋጋ ግሽበቱ ዝቅ ብሏል። መንግሥት የሚያጋጥመውን የበጀት ጉድለት ለመሸፈን የብሔራዊ ባንክ ብድር ሳይወስድ የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድን በመሸጥ የበጀት ጉድለቱ ከ1 ነጥብ 2 በመቶ እንዳያልፍ ማድረጉን አብራርተዋል። መንግሥት በጅምላ ንግድ ውስጥ የሚታዩትን ችግሮች ለማስወገድ ያካሄደው ጥናት በማጠናቀቁ የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር ጥናቱ በዚህ ዓመት ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የዋጋ ግሽበቱን በመቆጣጠር ረገድ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑን በመገንዘብ ባለፈው ዓመት ከ1ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያና ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ምርጥ ዘርፍ ለአርሶ አደሮች እንዲሰራጭ መደረጉን ተናግረዋል። የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት በተያዘው በጀት ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ኃይለማርያም አመልክተዋል። እንዲ