Posts

የወቅቱ የሲዳማ ኣመራሮች ለሲዳማ ህዝብ የክልል ይገባዋል ጥያቄ የሚያነሱ ኣካላት ጸረ-ሲዳማ ናቸው ኣሉ፤ የክልል ጥያቄውን ከወላይታ ጋር በማያያዝ መግለጫ ስጥተዋል

ETV News - Ato Shiferaw Shigutae calls Sidama oriented movements detractors | October 2, 2012 ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው ወረዳዎችን ጨምሮ የዞኑ ካቢኔ ኣባላት ጉባኤ ሲጠናቀቅ የዘጠኝ ነጥብ የኣቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን በመግለጫውም የሲዳማ ክልል ጥያቄ ያነሱ ኣካላት ጸረ ሲዳማ ናቸው በማለት ኮንነዋል።

Ethiopia: A call for genuine road-map for democracy

Enough is enough: a call for genuine road-map for democracy, maintaining the status quo of the Zenawi regime is a recipe for disaster by Adisie Tesfu, Oslo, Norway Ethiopia’s political landscape for the most part of the century has been volatile, controversial, unpredictable and at times chaotic. The Emperor’s Ethiopia was monarchical with its own defects; Mengistu’s Ethiopia was “Marxist” and Ethiopia under Zenawi and his continued regime remains under the noxious ideology of ethnic politics. All past and the present regime of Ethiopia had their own varied values, albeits, diametrically opposite to each other; there had never been smooth transition of power, it was all marked with bloodshed, violence, social and economic destruction and the loss of millions that could and should have been the foundation of human capital and material resources for now and the future. All those who assumed political power did so by iron fist and not by the will of ballot. They all did little to c

ከሲዳማ የፖለቲካ እስረኞች መካከል ሶስቱ በዛሬው እለት መፈታታቸው ተሰማ

Image
ከሲዳማ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ  ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት ወንጀል ተከሰው ላለፈው ኣንድ ወር እስር ላይ ካሉት ግለሰቦች መካከል በዛሬው እለት ካላ ዱካሌ ላሚሶ፤ ኣባተ ኪሞ እና ኡጋሞ ኣንጋና በዋስ ከእስር መለቀቃቸውን ከወደ ሲዳማላንድ ተሰምቷል።

በመንግስት መስሪያ ቤቶች የተደራጀ የለውጥ ሰራዊት በመፍጠር የ5 ዓመቱን የልማትና የትራንስፎሜሽን እቅድ ማሳካት እንደሚቻል በሲዳማ ዞን የአሮሬሳ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በመንግስት መስሪያ ቤቶች የተደራጀ የለውጥ ሰራዊት በመፍጠር የ5 ዓመቱን የልማትና የትራንስፎሜሽን እቅድ ማሳካት እንደሚቻል በሲዳማ ዞን የአሮሬሳ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ወራና እንደተናገሩት ዘመናዊ  የሰው ሀይል በመገንባት መስሪያ ቤቶች መልካም አስተዳዳር ማስፈን እንደሚገባ ገልፀው ሁሉም ባለሙያ በተመደቡበት የስራ መስክ ውጤት ለማምጣት መጣር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ የወረዳው ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈተ ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ድኬ በበኩላቸው በመንግስት ሠራተኛው በፖለቲካዊ ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስክ የለውጥ ሰራዊት ሆኖ በተመደቡበት ቦታ ግንባር ቀደም መሆን እንዳለበት ጠቁመው ለሠራተኛው የስራ ተነሳሽነት፣ ቅልጥፍናና በብቃት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ከሰልበጣኞች አንዳንዶች በሰጡት ሀሳብ ስልጠናው የተሻለ ግንዛቤ እንደጨበጡና በመንግስት መመሪያና ደንብ መሠረት በመስራት የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ሲል የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡

መንግሥት ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን የሚከለክል ሕግ ለማውጣት እያሰበ ነው

በዮናስ አብይ በአገሪቱ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉና ሃይማኖታዊ ግጭቶችን እየፈጠሩ ነው የሚባሉ ማናቸውም ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ምስሎች፣ ጥቅሶች፣ ድምፅን የሚበክሉ የጐዳና ላይ ስብከቶችና መዝሙሮች፣ ከሕዝባዊ ቦታዎች የሚከለክል አዲስ ሕግ አውጥቶ በሥራ ላይ ለማዋል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መንግሥት አስታወቀ፡፡ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች የሚመለከቱት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ሃይማኖት ጥልቅና ጥንቃቄ የሚያሻው ጉዳይ በመሆኑ፣ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጥልቀት እየመረመረው መሆኑንም ገልጿል፡፡  በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ ወርቁ በተለይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ መንግሥት በአሁኑ ጊዜ ሃይማኖታዊ መልዕክት ያላቸውን ይዘቶች በተመለከተ፣ የአምልኮ ሥርዓት ምን መምሰል እንዳለበትና የድምፅ ብክለትን ጨምሮ የሚፈጠሩ ችግሮችን ከሕዝባዊ ቦታ እንዴት ማራቅ እንደሚቻል፣ ሕግ እንደሚያስፈልግ ከምንጊዜውም በላይ እያሰበበትና እየተዘጋጀ ነው፡፡ “በማናቸውም አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንደ ታክሲ፣ ሆቴሎች፣ ሕዝባዊ ተቋማትና አደባባዮች ላይ የሚለጠፉ ሃይማኖታዊ ነክ መልዕክቶችን፣ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ሊያጋጩ የሚችሉ በኤሌክትሮኒክስ የሚተላለፉ መልዕክቶች በሙሉ በሕግ ተደንግገው የሚከለከሉበት ሥራ በመሠራት ላይ ነው፤” ብለዋል አቶ አበበ፡፡  “የሃይማኖት ጉዳይ ጠለቅ ያለ ነገር ስለሆነ ጠለቅ ያለ ሕግና ደንብ ያስፈልገዋል፡፡ ስለሆነም የአዋጁንና የደንቡን ይዘት እያዘጋጀን ለሚመለከታቸው አካላት እያሳየን ነው፡፡ የድምፅ ብክለትን በተመለከተ አዋጁና ደንቡ በማውጣት ሥርዓት ለማስያዝ እየተሠራ ነው፤” ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ነገር ግን እስካሁን ድረስ ቃል በቃል የሚጠቀስ ዝርዝር ይዘት ያለው ረቂቅ ሕግ ወይም አዋ