ምክር ቤቱ የሕዳሴ ጉዞን በሚያስቀጥሉ አቅጣጫዎችና ስልቶች ላይ ከስምምነት ደረሰ
አዲስ አበባ፡- የኢህአዴግ ምክር ቤት ሕዝቡን በማሳተፍ የተጀመረውን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ የሕዳሴ ጉዞ ለማስጠቀል በሚያስችሉ አቅጣጫዎችና ስልቶች ላይ ከስምምነት ላይ ደረሰ። የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ለዝግጅት ክፍላችን እንዳስታወቀው፤ የሕዳሴውን ጉዞ መላው የግንባሩ አባላትና የትግሉ ደጋፊዎች እንዲሁም የለውጡ ባለቤቶችና ተጠቃሚዎች የሆኑት መላው ኢትዮጵያውያንን በማሣተፍ ማስቀጠል እንደሚገባ ምክር ቤቱ ስምምነት ላይ ደርሷል። ትናንት የተጀመረው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ለታላቁ የድርጅቱ ሊቀመንበር ለክቡር አቶ መለስ ዜናዊ የሕሊና ፀሎት በማድረግ ተከፍቷል። ከአራቱ ብሔራዊ ድርጅቶች በእኩል ድምፅ የሚወከሉት የምክር ቤቱ አባላት ምልዓተ ጉባኤ መሟላት መሠረት በማድረግ ከሕሊና ፀሎቱ በኋላ ለምክር ቤቱ በመወያያነት በቀረቡት አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ በማፅደቅ ሥራውን ጀምሯል። በዚሁ መሠረት በሁለቱ ቀናት ምክር ቤቱ ለመወያየት ከያዛቸው አጀንዳዎች መካከል በቅድሚያ፡-የሚመክረው የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ተግባራዊ ልዕልናን በማረጋገጥ የመለስ/ኢህአዴግን ራዕይ ለማሳካት እንረባረብ በሚል ርዕስ የተዘጋጀና በታላቁ መሪና በድርጅቱ አመራር የተገኙትን ስኬቶች ማስቀጠል በሚቻልባቸውና ቀጣይ ፈተናዎችን ለመቋቋም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ነው። ከዚህ በማስቀጠልም ታላቁ መሪ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ ተዘጋጅቶ በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውይይት ተደርጎበት የነበረው የአመራር ግንባታና የሕዳሴው ጉዞ በሚል ርዕስ ኪራይ ሰብሳቢነትን ከምንጩ ለማድረቅና የሕዝቡን ዘላቂ ጥቅምና ተጠቃሚነት በሕዝቡ የተደራጀና ቀጣይነት ያለው ንቅናቄና ተሣትፎ ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ እና ከዚሁ ሂደት ጠንካራ የድርጅትና መንግሥት አመራር መፍጠር በሚቻልባቸው የአሠራር የአደረጃ