Posts

የመለስ ኢትዮጵያና ወራሾቿ

Image
ፎቶ ኢንተርኔት በሰለሞን ጎሹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባረፉ በሁለት ሳምንታቸው ግብዓተ መሬታቸው ተፈጽሟል፡፡ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በተለያዩ መንገዶች ሐዘን ከመግለጽ ጋር በተያያዙ እንቀስቃሴዎች ተወጣጥሮ የነበረው መንግሥት ወደ መደበኛው ሥራው እንደሚመለስ ይጠበቃል፡፡ የሥራዎቹ ሁሉ መጀመርያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲመርጥ ወይም የተመረጠውን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲያፀድቅ ማድረግ ነው፡፡ በቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ምርጫ ዙሪያ እየተደረጉ ያሉት የሐሳብ ልውውጦች ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የግል ሰብዕናና የፖለቲካ አመራር ብቃት፣ ከኢሕአዴግ የፖሊሲ ለውጥ የማምጣትና ያለማምጣት ጥያቄ፣ ከፓርቲ ፖለቲካውና ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ባለፉት 21 ዓመታት ኢትዮጵያን በፈለጉት መንገድ የቀረጿት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ የአገሪቱን ፖሊሲዎች በመንደፍ፣ አመራራቸውን ማዕከላዊ በማድረግ፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ነጥረው በመውጣታቸው የተነሳ የተተኪውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሥራ ከማክበዳቸውም በላይ፣ ኢትዮጵያውያን፣ የውጭ ዜጎችና መንግሥታት በቀጣይ ሥራዎች ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጓል፡፡ የመለስ የአመራር ዘዬ መለስ ከልጅነታቸው ጀምሮ ብልህና ጎበዝ ተማሪ እንደነበሩ ስለእሳቸው የተጻፉ ሰነዶች ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ በአድዋም ሆነ በአዲስ አበባ ዊንጌት ትምህርት ቤት ያሉ መዛግብትም ይህን ያስተጋባሉ፡፡ ያቋረጡትን የሕክምና ትምህርትም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩም ጉብዝናቸው ተከትሏቸዋል፡፡ የ1960ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውና ከዩኒቨርሲቲ ተማሪነታቸው ጋር አብሮ በመሄዱ፣ የንባብ ፍላጎታቸው ከመደበኛው የትምህርት ጥናት ውጪ ወደ ፖለቲካው እንደተሸጋገረ ይ

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ መልካም እድል ለሲዳማ ተማሪዎች

Image
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2 (ኤፍ ቢ ሲ)አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በ2005 የትምህርት ዘመን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎችን የመግቢያ ነጥብ ይፋ አደረገ፡፡ ሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው በ2005 የትምህርት ዘመንበከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች 116, 651 ሲሆኑ ፥ ከእነዚህም መካከል 75 ሺህ 69 (64.35%) ወንዶች እና 41,582 (35.64%)  ያክሉ ደግሞ ሴቶች ናቸው። በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለሁሉም መደበኛ ወንድ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብ 294 ሲሆን ፥ ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 290 ሆኗል። ለታዳጊ ክልልና ለአርብቶ አደር ልጆች ወንድና ሴት ተማሪዎች 285 እና ከዚያ በላይ ሲሆን በተመሳሳይ ለግል ተፈታኞች ወንዶች 299 ለሴቶች 297 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ገልጿል። በማኀበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ ሁሉም ለመደበኛ ተማሪ ወንዶች 275 ፥ ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 270 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ፥ በዚሁ የትምህርት መስክ ለታዳጊ ክልልና ለአርብቶ አደር ልጆች ወንድ ተማሪዎች 270  ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 268 እና ከዚያ በላይ ሆኗል።  መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች ደግሞ 230 እና ከዚያ በላይ እንደሆነም ኤጀንሲው አስታወቋል። እንዲሁም ለግል ተፈታኝ ወንድ ተማሪዎች 299 ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 297 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ወደ ከፍተኛ ተቋማት እንዲገቡ መወሰኑን ገልጿል። በተመሳሳይም ወደ መሰናዶ የትምህርት መስክ የመግቢያ ነጥብ ለመደበኛና ለማታ ወንድ ተማሪዎች 2.57 ሲሆን ፥ ለሴት ተማሪዎች

ህዝቡ ካድሬ እንደማያስፈልገው አረጋገጠ!

የቤተመንግስቱ በር ተከፈተልን፤ የመንግስት ልብስ? ዘንድሮ አሪፍ ዓመት አልነበረም፡፡ ታላላቆቻችንን በሞት የነጠቀንና ህዝቡንም የሀዘን ማቅ ያለበሰ ክፉ ዓመት ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ የጠ/ሚኒስትሩ ድንገተኛ ህልፈት እጅግ አስደንጋጭና ልብን የሚሰብር ነበር፡፡ ለዚህም ነው አገር ሙሉ ህዝብ በሀዘን የሰነበተውና የአገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ የተውለበለበው፡፡ “ኖሮ ኖሮ ወደ አፈር” እንዲሉ ባለፈው እሁድ የጠ/ሚኒስትሩ የቀብር ሥነስርዓት በታላቅ ክብር በአስደማሚ የህዝብ አጀብ ተፈጽሟል፡፡ ከዚያ በኋላ ኢህአዴግ የእስካሁኑ ሀዘን በቂ ነው በሚል በማግስቱ “ሀዘን አብርድ” በሚል ስሜት ሁሉም ወደ ወትሮው ሥራ እንዲመለስ ማድረጉን ወድጄለታለሁ፡፡ የሀዘን ብዛት አቶ መለስን ከሞት እንደማይመልሳቸው እያወቅን ከዚህ በላይ ሥራ ፈትተን ሃዘን ብንቀመጥ አንዳችም ትርፍ - የለውም፤ ኪሳራ እንጂ፡፡ የእሳቸው አጥንትም ቢሆን እኮ ይወቅሰናል፡፡ እኔማ ሳስበው እሳቸው በእስካሁኑም ሀዘን ቢሆን ደስተኛ የሚሆኑ አይመስለኝም፡፡ በድህነት አበሳዋን የምትበላ አገር በሀዘን ሰበብ ሥራ ፈትታ መቀመጥ የለባትም እንደሚሉ ቅንጣት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ግን ግዴለም ይሁን፡፡ መሪ ሞቶብን በቅጡ አዝነን በክብር ስንቀብር የመጀመሪያችን ነውና የሀዘን ጊዜው በዝቷል ላይባል ይችላል፡፡ ይልቅስ በሃዘኑ ወቅት ጐጂ ባህል ነው ተብለው የተከለከሉ እንደ ደረት መደለቅ ያሉ የሃዘን ሥርዓቶች ሲከናወኑ ታይተዋል፡፡ አንዳንድ ታዛቢዎቹ እንደሚሉት፤ በአሁኑ ጊዜ በለቅሶ ወቅት እንዲህ ያሉት ጐጂ ባህሎች አይፈቀዱም፡፡ ሲደረጉ ከታየም የሰፈር ዕድሮች ድንኳናቸውን ነቅለውና እቃቸውን ሸክፈው እብስ ነው የሚሉት አሉ፡፡ ይሄኛው ግን ብሔራዊ  ሀዘን ስለነበር “ግዴለም ይሁን” ሊባል ይችላል፡፡ (ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚ

አቶ ሃይለማርያም በጠቅላይ ሚኒስትርነት ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል

Image
የስልጣን ክፍተትና አለመረጋጋት እንዳይፈጠር የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሹመት ከሁለት ሳምንት በፊት በፓርላማ እንዲፀድቅ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም፤ የአገሪቱን መረጋጋትና የህዝቡን ስሜት በማየት እንዲሁም የፕሮቶኮልና የአሰራር ደንቦችን ለማሟላት ሲባል ወደ መጪዎቹ ሳምንታት እንደተሸጋገረ ምንጮች ገለፁ።የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወትን በተመለከተ የመጀመሪያ መግለጫ በተሰጠበት ማክሰኞ እለት፤ በህገመንግስቱ መሰረት ምክትል ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ መንግስትን የመምራት ሃላፊነቶችን በሙሉ እንደተረከቡ መገለፁ ይታወሳል። የሚቀር ነገር ቢኖር፤ የክረምት እረፍት ላይ የሚገኘው ፓርላማ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቶ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ሹመት ማፅደቅ እንደሆነም የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ ሚኒስትር በረከት ስምኦን በእለቱ ተናግረዋል። የአቶ በረከት መግለጫ ሁለት አላማዎች እንደነበሩት የሚገልፁ ምንጮች፤ ሁሉም ነገር በህገመንግስቱ መሰረት እንደሚቀጥል መተማመኛ መስጠት አንዱ አላማ ሲሆን፤ የስልጣን ክፍተትና ሽኩቻ እንደማይኖር ማረጋገጫ በመስጠት አለመረጋጋት እንዳይፈጠር በር መዝጋት ሁለተኛው አላማ ነበር ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት በፍጥነት እንዲፀድቅ ታስቦ እንደነበር የሚገልፁት ምንጮች፤ ሃሙስ ነሐሴ 17 ቀን የፓርላማ አባላት ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተው እንደነበር ይጠቅሳሉ። በእለቱ የአቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነስርዓት በሚፈፀምበት የቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን አጠገብ በሚገኘው ፓርላማ ውስጥ ስብሰባውን ማካሄድ አመቺ ስላልነበረ ለአርብ ቀን መተላለፉንም ያስታውሳሉ ምንጮቹ። ይሁንና አርብ ነሐሴ 18 ቀን በተካሄደው የፓርላማ ስብሰባ የጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት ጉዳይ አልተነሳም፤ የህሊና ፀሎት በማካሄድና የሃዘን መግለጫ በማው

Ethiopia party divided on Zenawi successor

Image
IN SUMMARY U-turn. The top ruling party organ appeared to contradict the Cabinet’s original decision and state media have dropped references to Mr Hailemariam as prime minister-designate. In a sign of a growing internal power struggle, Ethiopia’s ruling party has further delayed choosing its new leader, further extending the process of choosing the prime minister for the country. Executive council members of the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF), in a closed-door meeting early this week, failed to agree on election procedures for the new party leader, exposing the divide among the ruling elite. Former party leader and country’s prime minister, Meles Zenawi died in a Brussels hospital on August 20. Mr Meles had also been the chairman of the powerful Tigrian People’s Liberation Front (TPLF), one of the four ethnic-based parties in the coalition. Following his death, Ethiopia’s cabinet endorsed his deputy, Mr Hailemariam Desalegn, as acti