Posts

በሐዋሳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲታከሙ አስመስለው የተነሱ ፎቶዎችን ሲሸጡ የተገኙ በፖሊስ ተያዙ፤በሐዋሳ ከተማ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ነዋሪዎች እንዲሁም እሑድ የሲዳማ ብሔረሰብ አባላት በባህላዊ ሥርዓት ሐዘናቸውን በገለጹባቸው ቀናት በርካታ ፎቶ ግራፎችና ፖስተሮች የተሸጡ ሲሆን፣ ሁለቱ ግለሰቦች የጠቅላይ ሚኒስትሩን የተሳሳቱ ፎቶ ሲሸጡ መያዛቸውን የፖሊስ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

Image
በሐዋሳ ከተማ የጠቅላይ ሚኒስትር  መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ሕይወት ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በርካታ ፎቶግራፎች ሲሸጡ የሰነበቱ ሲሆን፣ በሕክምና ላይ እያሉ አስመስለው የተነሱ ፎቶግራፎችን ሲሸጡ የተገኙ ግለሰቦች ደግሞ በፖሊስ ተይዘዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆስፒታል ውስጥ ጉሉኮስ ተደርጎላቸው የተነሱ አስመስለው በማሳተም በተለይ መስቀል አደባባይ በሚባለው አካባቢ ፎቶግራፉን በአምስት ብር ሲሸጡ፣ ትክክለኛ መስሎአቸው ነዋሪዎች እየተሻሙ ሲገዙ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡  ይሁንና ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ሁለት ሰዎች በዚህ ድርጊት  ምክንያት ከቁጥጥር ሥር ሲውሉ፣ ሕገወጥ ፎቶዎችን በማሰራጨት ድርጊት ተጠያቂ ተደርገው በፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምርያ አስታውቋል፡፡  ስሙን መጥቀስ ያልፈለገ አንድ ፎቶግራፍ ሲሸጥ የነበረ ወጣት ጠቅላይ ሚኒስተሩ በሕክምና ላይ እያሉ የሚያሳየውን ፎቶግራፍ ከየት እንዳገኙት ተጠይቆ፣ ‹‹እኔ ያንን ፎቶ አላገኘሁትም፣ ነገር ግን ሲሸጡ የነበሩት ሰዎች ከኢንተርኔት እንዳገኙት ሰምቻለሁ፤›› በማለት ለሪፖርተር ተናግሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉሉኮስ ተሰጥቶአቸው ተኝተው ሲታከሙ የሚያሳየውን ፎቶግራፍ ትክክለኛ መስሎዋቸው እንደገዙ የገለጹት የሐዋሳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዳንጊሶ ተሰማ፣ ‹‹ሐሰተኛ መሆኑን  ባውቅ አልገዛውም ነበር፤›› ብለዋል፡፡ ስለጉዳዩ የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መከላከል የሥራ ሒደት ኃላፊ ኢንስፔክተር ታደሰ በንቲ ተጠይቀው፣ ጠቅላይ ሚኒስተሩ በሕክምና ላይ እያሉ አስመስለው  የተነሱትን ፎቶግራፎች በማተም ሲሸጡ የነበሩ  ሁለት ሰዎች በመናኸሪያ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን ጠቁመው፣ ሌሎች ፎቶግራፎችና ፖስተሮችን እየሸጡ በሚገኙት ላይም ክትትል እየተደረገ መሆኑን ለሪፖርተር አስ

Human Rights Violations in Sidama Escalating

Image
New August 31 2012-Arrest and abduction have been commonplace occurrences in Sidamaland and it has been worsened since last June when Sidama public pressed the demand of regional Self adminstration right. Since then, many innocent Sidamas are languishing in jails illegally and whereabouts of many are unknown. Fabricated charges are used against those who are imprisoned as means to lock them up indefinitely. For instance, Ougamo Hanaga, who is an employee of Save the Children Awassa branch, made the following comment on facebook about the ordeal of innocent Sidamas and he was arrested few days later. He then charged with terrorism under the country's antiterrorism law without hard evidence that links him to terrorism. http://sidamaliberation-front.org/

A Shadow Government set to rule Post-Meles Ethiopia

Image
As expected, although they have no choice but to elevate Hailemariam Desalegn formally to replace Meles’ position, the ruling elites have formed a shadow government that will make all the real decisions  behind the scenes. This shadow government – a “transition time caretaker” – is made up of seven members. According to individuals privy to the process of selection, the justification given for the appointment is that the shadow government should be made up of one person from each of EPRDF’s member parties, and one each from key government agencies – intelligence, foreign affairs, and the military. Below is the list. Name Representing Parent Party Ethnicity General Se'are Mekonnen Military TPLF Tigrean Getachew Assefa Intelligence TPLF Tigrean Berhane Gebrekiristos Foreign Affairs TPLF Tigrean Seyum Mesfin TPLF TPLF Tigrean Bereket Simon ANDM ANDM Tigrean (Eritrean) Kuma Demeksa OPDO OPDO Unknown (Tigrean/Amhara) Hailemarim Desalegn SEPDM SEPDM Walayta It is asto

የኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡ ፍቅሩን ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲለውጥ ጥረት እንዲያደርጉ ታዘዙ::

ኢሳት ዜና:- ሰሞኑን በመካሄድ ላይ ያለው አቶ መለስ ዜናዊን ልዩ ሰው አድርጎ የመሳል እንቅስቃሴ ድርጅቱን ስጋት ላይ እየጣለው በመምጣቱ ካድሬዎች የፕሮጋንዳ ስራቸውን ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲያዞሩ ታዘዋል። ኢህአዴግ በመጀመሪያ በአቶ መለስ ዜናዊ የግለሰብ ስብእና አስታኮ ስልጣኑን ለማደላደል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ቀይሶ የነበረ ቢሆንም፣ የፕሮፓጋንዳው እንቅስቃሴ አቅጣጫውን እየቀየረ መምጣቱ ድርጅቱን ስጋት ላይ ጥሎታል። አቶ መለስ የሁሉም ፕሮጀክቶች አፍላቂ ፣ የኢህአዴግ ጭንቅላት ተደርገው እንዲሳሉ መደረጉ ሌሎች ሰዎች በድርጅቱ ውስጥ እንደሌሉ፣ ድርጅቱ እርሳቸው ከሌሉ ህይወት የሌለው ድርጅት ነው የሚል መልእክት እያስተላለፈ መምጣቱ ሌሎች የደርጅቱን አባላት በተለይም የህወሀት ባለስልጣኖችን  እያበሳጨ ነው። ከሁሉም በላይ ኢህአዴግ ያለመለስ ህይወት አይኖረውም የሚለው አመለካከት በስፋት እንዲሰራጭ ያደረገው የአቶ በረከት ስምኦን የፕሮፓጋንዳ ስልት ነው በሚል ህወሀቶች ወቀሳ እያቀረቡ ነው። ከኢህአዴግ የደህንነት ምንጮቻቸን ባገኘነው መረጃ መሰረት ግንባሩ የፕሮፓጋንዳ ስራው ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲዞርና የሁሉም መስሪያቤት ሰራተኞች ለኢህአዴግ  ያላቸውን ታማኝነት መግለጥ እንዲጀምሩ መመሪያ አውርደዋል። ኢህአዴግ እንደ ድርጅት ያደረገው አስተዋጽኦ ተረስቶ ሁሉም ነገር አቶ መለስ እንደሆኑ ተደርጎ የሚተላለፈው ቅስቀሳ፣ ድርጅቱን ሰው አልባ አድርጎ ከመሳል በተጨማሪ በድርጅቱ ውስጥ ፈላጭ ቆራጩ አንድ ሰው ብቻ እንደሆኑ ተደርጎ እንዲሳል እያደረገው ነው። ህዝቡ አቶ መለስ ኬለለ ኢህአዴግ የለም የሚል አመለካከት እዬያዘ መምጣቱ እየተነገረ ነው። የኢህአዴግን ስርአት የሚቃወሙትም ከአቶ መለስ በሁዋላ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም መጠየቃቸው የህወሀት

የሥልጣን መተካት በሕገ መንግሥቱ

የዚህ ሰሞን የአገራችን ድባብ ተለውጧል፡፡ ሚዲያው በሐዘን ዜና፣ ሕዝቡም በትካዜ ተውጧል፡፡ በአንድ ሳምንት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና የኢትዮጵያ ሕዝብ መሪዎቹን አጥቷል፡፡ ፓትርያርኩም ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከነበራቸው አገራዊና አኅጉራዊ ተሰሚነት አንፃር ዜና ዕረፍታቸው አስደንጋጭ ነበር፡፡ በየሚዲያው የምንሰማው የእንጉርጉሮ የዋሽንት ድምፅ፣ በየመንገዱ የተመለከትናቸው ጥቁር አልባሳት፣ የሐዘን መግለጫዎችና ለቅሶዎች ሁሉንም የኩነቱ አካል አድርጎታል፡፡ ‹‹ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ . . . ›› እንዲል ሰዎች ከሞታቸው ጋር የሚኖሩ ቢሆንም፣ መልካም ለሠሩት ወይም ለሚሠሩት የሥራ ጊዜ ቢያገኙ መልካም ነበር፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ግን የሥራው መቀጠል፣ የተተኪ አመጣጥ ወዘተ. እኛው ጋ የሚቀሩ ሀቆች ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ‘ዓቃቤ መንበረ ፓትርያርክ’ የኢትዮጵያ መንግሥትም ‘ጊዜያዊ የጠቅላይ ሚኒስትር’ የሾሙት፡፡ የፕትርክናው አመራረጥ አካሄድ በቃለ አዋዲ የሚመራና ለሲኖዶሱ ደንብ የማውጣት፣ ኮሚቴ የማዋቀርና ምርጫውን የማስፈጸም ሥልጣን የተሰጠ ቢሆንም፣ ሥራው የተወሰኑ ተግዳሮቶች እንዳሉት ይታመናል፡፡ የቤተ ክርስቲያኗን አንድነት መጠበቅ፣ አካሄዱን በተቀደሰ መንፈስ መምራት፣ ነገሮችን በጥበብና በጥንቃቄ መፈጸም ግቡን ያሳምረዋል፡፡ የመንግሥትም ጠቅላይ ሚኒስትሩን የመሾም ወይም የመተካት አካሄድ የሚኖረው የሕግ ክርክር ሊኖር እንድሚችል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕመም ላይ በነበሩበት ጊዜ በሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ አምዶች ላይ ሲስተናገዱ የነበሩ የአቋም ልዩነቶች አመላካች ናቸው፡፡ ክርክሮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜና ዕረፍት በኋላም የሚነሱ በመሆናቸው ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርጎ እልባት መስጠቱ አማራጭ የለውም፡፡ በዚህ ጽሑፍ የሚስተናገደ