Posts

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስክሬን ከሰዓታት በኋላ አዲስ አበባ ይገባል፤ በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ መሰረትም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ቃለ መሀላ እስኪፈፅሙ ድረስ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስራ በተጠባባቂነት ተረክበው ይሰራሉ ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስክሬን ከሰዓታት በኋላ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ  እየተጠበቀ ነው ።  በአሁኑ ወቅትም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትሩን  አስክሬን በክብር ለመቀበል በቦሌ  አውሮፕላን ማረፊያ  አከባቢ  እየተሰባሰቡ ይገኛሉ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ትናንት ማምሻውን በህክምና ሲረዱ በነበሩበት  ሆስፒታል ማረፋቸውን  ነው ያስታወቀው ።  ምክር ቤቱ በመግለጫው ኢትዮጵያን ላለፉት 21 ዓመታት በከፍተኛ ብስለትና ብቃት ሲመሩ የቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስው ዜናዊ ካደረባቸው ህመም ለመፈወስ በውጭ አገር በህክምና ሲረዱ መቆየታቸውን ጠቅሷል ። ላለፉት ሁለት ወራት በህክምና ሲረዱና በጤናቸውም ላይ መሻሻል ሲታይ ከቆየ በኋላ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ  በተከሰተ ደንገተኛ  ኢንፌክሽን ህመማቸው አንደገና ተባብሶ ለአስቸኳይ የህክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል  ገብተው ነበር ። በህክምና ሙያተኞች ከፍተኛ እገዛ ቢደረግላቸውም በትናንትናት እለት ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ40 ላይ በድንገት ማረፋቸውን ምክር ቤቱ ለአገራችን ህዝቦች በታላቅ ሀዘን ገልጿል ። ኢትዮጵያንና  ህዝቦቿን ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነትና በታማኝነት አገራቸውን  አገልግለው ከፍተኛ የለውጥ ተስፋ ያሳዩን  መሪ እንደነበሩ  ነው ምክር ቤቱ የገለፀው  ። አቶ መለስ ኢትዮጵያ በልማታዊ ዲሞክራሲያዊ አቅጣጫ እንድትጓዝ ጥራት ያላቸው ፖሊሲዎችንና  ስትራቴጂዎችን  ነድፈው በብቁ አመራራቸው በገነቧቸው ድርጅቶችና መንግሰት አማካይነት ተግባራዊ ማድረግ የቻሉና በአገራችን

ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

 ማክስኞ, 21 ንሐሴ 2012 የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ የኢህአዴግ አባላትና መላ የትግላችን ወደጆች በዛሬው እለት ድርጅታንን ገና ከውልደቱ በመምራት ለታላቅ ሀገራዊ ለውጥ ያበቃንና በሀገራችን ታሪክ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ያስቻለንን ታላቁ የድርጅታችን መሪ ጓድ መለስ ዜናዊ ለህልፈተ ሕይወት በመብቃቱ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰማውን ከፍተኛ ሀዘን ይገልጻል፡፡ ዛሬ በእርግጥም ድርጅታችንና መላ የሀገራችን ህዝቦች ታላቁን የለውጥ መሪያችንን ተነጥቀናል፡፡ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በድርጅታችን ሊቀመንበር በጓድ መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማውን ልባዊ ሃዘን እየገለጸ ለመላ የሀገራችን ህዝቦችና የድርጅታችን አባላት እንዲሁም ለመላ ቤታሰቦቹ ከፍተኛ መጽናናትን ይመኛል፡፡ የድርጅታን ሊቀመንበር ጓድ መለስ ዜናዊ ገና ከውልደቱ አመራር እየሰጠ ለዚህ ያበቃው ኢህአዴግና መላ አባላቱ በድርጅታችን ታላቅ መሪ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ከፍተኛ ምሬትና ሃዘን የሚሰማን ቢሆንም በታላቁ መሪያችን አኩሪ ስራና ጥሎልን ባለፈው ትክክለኛና የጠራ የትግል መስመር ፀንተን በመታገል ራዕዩን እውን ለማድረግ በከፍተኛ ቁርጠኝነት መነሳታችንን እንገልጻለን፡፡ የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ የኢህአዴግ አባላትና መላ የትግላችን ወዳጆች የድርጅታችን ሊቀመንበር ጓድ መለስ ዜናዊ ከምንም ነገር በላይ የለውጥ ሃሳቦችን በማፍለቅና እነዚህን ተግባራዊ የሚያደርግ ጠንካራ ድርጅትና መንግስት በመገንባት የሚያምንና ይህንኑም በተግባር ላይ ያዋለ ፅኑ የህዝብ ልጅ ነበር፡፡ መሪያችን ጓድ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን በእውቀትና በዘመናዊ መንገድ ብቻ መምራት እንደሚቻል አውቆ ሁሌም ራሱን ለማስተማርና በጥረቱም ያካበተውን እው

በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብቡን አስታወቀ፡፡

በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብቡን አስታወቀ ፡፡ ጽህፈት ቤቱ በአመቱ ለመሰብሰብ ያቀደው 6 ሚሊዮን ብር ሲሆን  ከ9 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ሊሰበሰበብ መቻሉን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምስራቅ በቴ ገልፀዋል ፡፡ የአመቱ እቅድ ክንውን አፈፃፀም 98 ነጥብ 2 ከመቶ መሆኑንና ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ3 ሚሊዮን 61ዐ ሺህ 196 ብር ብልጫ ማሳየቱን ኃላፊው አስረድተዋል ፡፡ ገቢው ሊሰበሰብ የቻለው ከቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆኑ ገቢዎች እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢዎች መሆኑን አብራርተዋል ፡፡ ለገቢው መጨመር የግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግብር የመክፈል ግንበዛቤ እያደገ መምጣት፣ የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነት መፈጠርና የወረዳው መስተዳደርና ባለድርሻ አካላት ከገቢ ሰብሳቢው ጽህፈት ቤት ጋር የተቀናጀ ሥራ በማከናወናቸው መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል ፡፡ በቀጣይ አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በማፈላለግ የተጀመረውን የ5 ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አቶ ምስራቅ መናገራቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዘግቧል ፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/14NehTextN604.html

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር እስከሚፈጸም ድረስ በመላው አገሪቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ ይቆያል

Image
አዲስ አበባ ነሐሴ 15/2004 የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር እስከሚፈጸም ድረስ በመላው አገሪቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ እንደሚቆይ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ገለጹ። በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ መሠረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱን የመምራት ኃላፊነት መረከባቸውን ገልጸዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሥርዓተ ቀብርን የሚመራ ሰባት አባላት ያሉት ብሔራዊ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑን አስታውቀዋል። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር እስከሚፈጸም ድረስ በመላው አገሪቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ ይቆያል። "ዛሬ ለኢትዮጵያ አሳዛኝ ቀን ነው። ላለፉት 21 ዓመታት አገሪቱ መሠረታዊ የዴሞክራሲ ሥርዓትና የኢኮኖሚ ዕድገት እንድታመጣ ያስቻሏትን ታላቅ መሪዋን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን አጥታለች።" ብለዋል አቶ በረከት። በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ መሠረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱን የመምራት ኃላፊነት መረከባቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ምክር ቤት /ኢህአዴግ/ ጠቅላላ ጉባዔ በሚካሄድበት ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ምርጫ የሚደረግ ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የፓርቲውንና የመንግስትን ኃላፊነት ይዘው የሚቀጥሉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችልም ጠቁመዋል። በተቀመጠው የአምስት ዓመት የአዲስ አመራር የመተካካት ሥርዓት መሠረት የአዲስ አመራሮች ምር

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

Image
አዲስ አበባ ነሐሴ 15/2004 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ የሚኒትሮች ምክር ቤት ሙሉ መግለጫ የሚከተለው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አገራችንን ላለፉት 21 ዓመታት በከፍተኛ ብስለትና ብቃት ሲመሩ የቆዩት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ካደረባቸው ሕመም ለመፈወስ በውጭ አገር በሕክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋላ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 5፡40 በድንገት ማረፋቸውን ለመላው የአገራችን ሕዝቦች በታላቅ ሐዘን ይገልጻል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላለፉት ሁለት ወራት በህክምና ሲረዱና በጤናቸው ላይ መሻሻል ሲታይ ከቆየ በኋላ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በተከሰተ ድንገተኛ ኢንፌክሽን እንደገና ሕመማቸው ተባብሶ ለአስቸኳይ የህክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ገብተው በህክምና ሙያተኞቻቸውም እገዛ ቢደረግላቸውም በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 5፡40 ሲሆን ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነትና በታማኝነት አገራቸውን አገልግለው ከፍተኛ የለውጥ ተስፋ ያሳዩንን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እልፈተ ህይወት ሲገለጽ በኃዘን በተሰበረ ልብ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከምንም ነገር በላይ አገራቸውንና ሕዝባቸውን የሚወዱ ለዚች አገርና ሕዝብ የላቀ ራዕይ የነበራቸው መሪ ነበሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ራዕያቸውን እውን ማድረግ የጀመረና አስተማማኝ ውጤት ማምጣት የቻለ ድርጅትና መንግሥት የገነቡ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ከፍ ብላ መጠራት እንድትጀምር ያደረጉ ታላቅና እ