ተቋሙ በተያዘው የበጀት ዓመት ከ1ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ሊያበድር ነው
አዋሳ ነሐሴ 05/2004 በደቡብ ክልል በተያዘው የበጀት ዓመት ቁጠባን መሰረት ያደረገ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር ገንዘብ ለተጠቃሚዎች ማመቻቸቱን የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አሰታወቀ፡፡ በክልሉ በሚገኙ የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች የተጀመረው የቁጠባ ኤክስቴንሽ አገልግሎት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተመልክቷል፡፡ የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሀላፊ አቶ ሰሎሞን ገለቱ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት ብድሩ የተመቻቸው ሀዋሳን ጨምሮ በክልሉ ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ተደራጅተውና በግል ስራ ፈጥረው ለሚንቀሳቀሱ ከ200 ሺ በላይ ተጠቃሚዎች ነው፡፡ ለስራቸው ማጠናከሪያና ማንቀሳቀሻ የሚሰራጨው ይሄው የብድር ገንዘብ ለእያንዳንዳቸው ከ5 ሺ እስከ 100 ሺ ብር የሚሰጥ መሆኑን አመልከተው ሰርተውበት ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ ተመላሽ እንዲያደርጉ የክትትልና የሙያ ድጋፍ እንደሚሰጣቸው አስረድተዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በተመሳሰይ ሲሰጥ የቆየው የብድር ገንዘብ በአብዛኛው ተመላሽ መደረጉን ያመለከቱት ኃላፊው ህብረተሰቡ የወሰደውን የብድር ገንዘብ በአግባቡ በመጠቀም በወቅቱ የመመለሱ ባህሉ እየዳበረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም ከ896 ሺ በላይ አዲስና ነባር ደንበኞች ላይ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ በቁጠባ ለማሰባሰብ መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ባለፈው የበጀት ዓመት በክልሉ በሚገኙ ቀበሌዎች ባለሙያዎች በመመደብ የተጀመረው የገንዘብ ቁጠባ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በዚህ ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ሰሎሞን አመልክተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ በክልሉ የተለያዩ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በሚገኙ ከ3 ሺ በላይ የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች መጀመሩን አመልከተው እስካሁንም ከ120 ሺ በላይ የቁጠባ ሳጥኖች ለተጠ