Posts

ኢትዮጵያ ከሶስት አመት በኋላ በምግብ ዋስትና ራሷን እንደምትችል ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከሶስት አመት በኋላ በምግብ ዋስትና ራሷን እንደምትችል የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት የዛሬ ሶስት አመት፤ ከ400 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የግብርና ምርት በዓመት የማምረት አቅም ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል። ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ይህን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል አሰራር እየተዘረጋ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት ተናግረዋል። እቅዱ በይፋ በተጀመረበት በ2003 ዓመተ ምህረት ከዋና ዋና ሰብሎች የተገኘው 203 ሚሊዮን ኩንታል የግብርና ምርት በልማት እቅዱ ከተቀመጠው የዘጠኝ በመቶ እድገት አሳይቷል። በተመሳሳይ በ2004 ዓመተ ምህረት 218 ሚለዮን ኩንታል የምርት መጠን ለማግኘት ታስቦ እቅዱን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት መቻሉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።     ለእቅዶቹ መሳካት ደግሞ በዋነኝነት አርሶ አደሩን በልማት ሰራዊት በማደራጀት ንቅናቄ መፈጠሩ በምክንያትነት ተቀምጧል። በቀጣይነት ይህን የተደራጀውን አርሶ አደር አቅም መገንባት ከተቻለም እቅዱን ለማሳካት አያዳግትም ባይ ናቸው። በኢትዮጵያ አምስት ሚሊዮን ሄክታር የሚደርሰው መሬት በመስኖ ሊለማ ይችላል። ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር ያህሉ በአነስተኛ መስኖ የሚለማ ሲሆን ፥ ቀሪው ደግሞ በመካከለኛና በከፍተኛ መስኖ ሊለማ የሚችል ነው። አሁን እየታየ የሚገኘው የምግብ እህል የዋጋ ንረትም እንደሚረጋጋ ጠቁመው ፥ በመንግስት በኩል ይህን የዋጋ ማሻቀብ ለመቀልበስ ዋና ዋና የግብርና ምርቶች ወደ ውጭ እንዳይላኩ ከመከልከል ጨምሮ ብዙ የፖለሲ እርምጃዎች እንደተወሰዱ መናገራቸውን ታደሰ ብዙአለም ዘግቧል።  http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=25312&K=

የያዬ ሃርቤጎና ሃይድሮ ኤለክትሪክ ማምንጫ ከየት ደረስ?

Image
በሲዳማ ልማት ኮፖሬሽን ባኃላ ላይ የሲዳማ ልማት ኣክሽን ተብሎ በተሰየመው የልማትድርጅት ለምቶ ኣገልግሎት ይሰጥ የነበረው እና ኣሁን ያለበት ደረጃ  የማይታወቀው  የያዬ ሃርቤጎና ሃይድሮ ኤለክትሪክ ማምንጭን በተመለከተ ከታች ካለው ሊንክ ላይ ተጭናችሁ ኣንብቡ። የሃርቤጎና ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የሃርቤጎና ያዬ ኃይድሮ ኣኤክትሪክ ማመንጫ እንደ ፈረንጆቹ ዘመን ኣቆጣጠር በ2006 የቢቢስ World Challenge ተፎካካር እንደነበር ያውቁ ነበር? የኃይልማመንጫውን በተመለከተ በBBC የተዘጋጀውን ድክሜንታሪ በዚህ ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ   Some eight hours' drive from the Ethiopian Capital Addis Ababa is the small community of Yayee. The surrounding countryside is a far cry from Ethiopia's stereotypical image: lush green pastures interwoven with rivers and streams. But this idyllic appearance is deceptive. Until the 1990s, political and economic marginalisation had rendered Yayee one of the poorest communities in Ethiopia. At the overthrow of the Marxist regime in 1991, just 23 percent of Yayee's children were attending school and the community had no medical facilities whatsoever. It was then that the people of Yayee decided to help themselves to a better s

ጊዳቦ ፍልውሃ ገና ያልተነካ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም

Image
ቅዱስ ኃይሉ ይርጋለሞች፣ ዳሌዎች እንዲሁም እነዚህን አካባቢዎችና የተለያዩ አገልግሎታቸውን ያዩ ሁሉ ሳይቋደሱት አያልፉም። የጊዳቦ ፍልውሃን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልላዊ መንግሥት ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ ይርጋለም ከተማ የሚገኘው ይህ የፍልውሃ ቀደም ሲል በዋቢ ሸበሌ ሆቴሎች አስተዳደር ሥር ይተዳደር ነበር። አሁን ደግሞ የሲዳማ ልማት ማኅበር ተቋም ነው። በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደ እዚህ አካባቢ በሄድኩ ቁጥር እኔም ይህንን ሀብት ሳልቋደስ አልመለስም። በቅርቡም ወደዚሁ ፍልውሃ አገልግሎት ዘልቄ ያለፈውን እያስታወስኩ የአሁኑን አገልግሎቱን ቃኘሁ። ወደፊትም ሊኖረው የሚችለውን አቅምም ተንብያለሁ።  የፍልውሃ አገልግሎቱን ተጠቃሚ የሚያደርገውን ትኬት የሚቆርጡበት ቢሮ ቀድሞ ከነበረበት ወደ መግቢያው አካባቢ መጥቷል። ራሱን የቻለ ቤትም የፍልውሃ አገልግሎት መስጫ ቤቶቹ ከራስጌያቸው ያደረጉት ኮረብታውን ጥግ ይዞ ተሠርቶለታል።  የፍልውሃ አገልግሎቱ ሁሌም በወረፋ የተጨናነቀ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ቀን ምሳ ሰዓት ላይ ነው ወደ ሥፍራው ያቀናሁት። በእኔ ቤት ብልጥ ሆኜ ቶሎ አገልግሎቱን አግኝቼ ልመለስ።  የትኬት መቁረጡ ተራ እስኪደርሰኝ ድረስ ዙሪያ ገባውን ተመለከትኩት። ትኬቱ የሚቆረጥበት ሥፍራ ፍልውሃው የሚገኝበትን አካባቢ በሙሉ ለመቃኘት ያስችላል።  ቁልቁል ስመለከት የጊዳቦ ወንዝ ግራ ቀኙን በልምላሜ ታጅቦ በርበሬ መስሎ መፍሰሱን ተያይዞታል። ወቅቱ ክረምት ነውና የውሃው መጠን በጣም ጨምሯል፤ የሚጣደፍ አይመስልም። ድምፁ አይሰማም ከወንዙ ባሻገር የአርሶ አደሮች መንደር፣ እንሰት፣ ዛፎች እና የተለያዩ ተክሎች ይታያሉ። ከነዚህ ተክሎች ውስጥ ቡናና የፍራፍሬ ዛፎች ሊገኙበት እንደሚችሉ ጠጋ ብዬ ያየኋቸው የከተማና የገጠር መኖሪያ ጊቢዎች

በ5 አመቱ (2002-2007) የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና አቶ አለማየሁ አሰፋ በሲዳማ ህዝብ ላይ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደባ ለመፈጸም ያዘጋጁት ምስጥራዊ እቅድ ተጋለጠ

Image
Top secret /unclassified Dossi / ከውስጥ ኣዋቂ ምንጭ(ሲዳማ ዊኪሊክ)  የ5 አመቱ (2002-2007) ለሲዳማ የታቀደ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድና ውይይትና ውሳኔ  ማስታወሻ፡-  1) የዚህ ዕቅድ ውይይትና ውሳኔ ፋይል በከፍተኛ ሚስጥር የሚጠበቅ ሆኖ ለኔም የደረሰኝ በጣም ቅርብ ከሆነው ጓደኛዬና ከሁሉም በላይ ለሰው ልጅ ማንነትና መብት ከሚቆረቆር ዜጋ ነው፡፡ 2) ውይይቱ የተካሄደው በሶስት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሲሆን እነሱም፡- አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና አቶ አለማየሁ አሰፋ ናቸው፡፡ ቦታው በኃ/ማሪያም ደሳለኝ ቢሮ አ/አበባ ነው፡፡ ውይይቱ የተደረገው ከአራት ወር በፊት ሲሆን ዕቅዱ የተነደፈው በ2002ዓ.ም ሆኖ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእቅዱ ውሳኔዎች አንዳንዶቹ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ሆኖ የዚህኛው ውይይት ውሳኔ ካለፈው በበለጠ ተግባራዊ ስለሚደረግበት ሁኔታ ነው፡፡ 3) የውይይቱ ውሳኔ ሙሉ ይዘቱ ለሌሎች አምስት ም/ፕረዝዳንቶች ባሉት ብቻ የተገለፀው በአቶ ሽፈራውና በአቶ አለማየሁ አሰፋ ሲሆኑ ሌሎቹ የካብኔ አባላት ግን ሙሉውን ውሳኔ ሳይሆን ለጊዜው ተግባራዊ ለማድረግ የፈለገውን ውሳኔ ብቻ ተራ በተራ ነው፡፡ 4) የትኛው ውሳኔ በምን ጊዜ በአጀንዳነት ተዘጋጅቶ ለታችኛው መዋቅር መውረድ እንዳለበ የሚወሰኑት አቶ ሽራውና አቶ አለማየሁ ናቸው፡፡ 5) አንዳንድ ውሳኔዎች ለታችኛው መዋቅር በተለይም ለሲዳማ ካድሬዎች የማይወርዱ/የማይገለፁ/ እንዳሉ የሚገልፅ ቢሆንም የትኞቹ ውሳኔዎች እንደሆኑ ግን በግልፅ አያስቀምጥም፡፡ 6) ወደ ውይይቱና ወደ ውሳኔው ከመግባታቸው በፊት ሦስቱም እርስ በእርስ ሂስና ግለሂስ የተደራረጉ ሲሆን በኃ/ማሪያም ላይ የቀረበው ሂስ ‘አንተ የራስህ ወገ

በሃዋሳ ከተማ በ60 ሚሊዮን ብር የህግ ታራሚዎችን በሙያ አሰልጥኖ የሚያወጣ ዘመናዊ የማረሚያ ተቋም በመገንባት ላይ ነዉ

Image
  ሃዋሳ ፎቶ ወራንቻ ኔት ሃዋሳ 4/2004 የህግ ታራሚዎችን በተለያዩ ሙያዎች በማሰልጠን፣በእውቀት በማነጽ የክህሎት ባለቤት ለማድረግ 60 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ ዘመናዊ የማረሚያ ተቋም ግንባታ በመካሄድ ላይ መሆኑን የደቡብ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ ። የክልሉ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽነር አቶ አዳነ ዲንጋሞ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በመደበው ገንዘብ የሚካሄደው ግንባታ ታራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ የተለያዩ ሙያ ባለቤት በመሆን አምራችና ብቁ ዜጋ ሆነዉ እንዲወጡ ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡ በሃዋሳ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው ይኽው ዘመናዊ ማዕከላዊ የማረሚያ ተቋም የመመገቢያ አዳራሽ፣የህክምና ክፍል፣የመጀመሪያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ቤተ እንዲሁም የተለያዩ የሙያ ማስልጠኛ ማዕከላት፣ የመዝናኛና የስፖርት ሜዳዎችን ያካተተ መሆኑን አስታዉቀዋል ። የማእከላዊ ማረሚያ ተቋሙ ግንባታ በሚቀጥለው የበጀት አመት አጋማሽ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ የማዕከሉ መገንባት ታራሚዎች በቆይታቸው በሚያገኙት ዕውቀት በሀገራችን በመካሄድ ያሉ የሰላም ፣የመልካም አስተዳደርና የልማት ስራዎች ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችላቸዉ መሆኑንም አስታዉቀዋል ። በማዕከሉ የሚገኘዉ የህክምና ተቋም በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ሪፈር የሚጻፍላቸዉን ህሙማን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድ ገልጠዋል ። ከዚሁ በተጨማሪ 86 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የወላይታ ሶዶ ፣ የዲላ፣ የሆሳዕናና የሚዛን ተፈሪ ማረሚያ ተቋማት ትምህርት ቤቶች፣ ስልጠና ማዕከልና ሌሎችንም በማካተት በአዲስ መልክ የመገንባት ለሌሎች 18 ማረሚያ ተቋማት የጥገናና የእድሳት ስራ በመከናወ