Posts

በመልጋ ወረዳ በተነሳ ግጭት ከ19 በላይ ፖሊሶች በጽኑ ቆሰሉ

Image
ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት ከአዋሳ ከተማ  በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ  በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ መቁሰላቸውን የዘገብን ቢሆንም፣ ዛሬ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያጠናከረው መረጃ እንደሚያመለክተው ከ19 በላይ ፖሊሶች እና ከ20 በላይ ነዋሪዎች በጽኑ ቆስለዋል። አናታቸው የተፈነከተ ፣ እግራቸው የተሰበረ፣ እንዲሁም በጥይት የቆሰሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገድ ላይ ወድቀው ይታዩ ነበር። በገበያ ላይ የነበረው የአካባቢው ህዝብ ባገኘው መሳሪያ ሁሉ በመጠቀም ከፖሊሶች ጋር ግብ ግብ የገጠመ ሲሆን፣ መሳሪያ የታጠቁ ነዋሪዎች፣ አፈሙዛቸውን ወደ ፖሊሶች በማዞር በርካቶችን አቁስለዋል። ከተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች የተውጣጡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው ደርሰው በህዝቡ ላይ በከፈቱት ተኩስ ከ20 በላይ ነዋሪዎች በጽኑ ቆስለዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ግጭቱን ለማብረድ የቻሉት ከአጎራባች ወረዳዎች የፌደራል ፖሊስ አባላትን በብዛት በማምጣት ነው። ፖሊሶቹ ዛሬ በእየቤቱ አሰሳ በማድረግ አንዳንድ ወጣቶችን እየያዙ ወደ እስር ቤት ወስደዋል። በአካባቢው ያለው ውጥረት እየጨመረ፣ የአካባቢው ሰውም ራሱን ከጥቃት ለመከላከል የሚችለበትን መሳሪያ ሁሉ ማዘጋጀቱን ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚናገሩት። የሲዳማ ተወላጆች ካለፈው ወር ጀምሮ መብታችን ይከበር፣ የክልል አስተዳዳር ይሰጠን የሚሉ ጥያቄዎችን በማቅረብ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሲወዛገቡ እንደነበር ይታወቃል። የመልጋ ወረዳ ነዋሪዎች ያቀረብነው ጥያቄ በአግባቡ እስካልተመለሰ ድረስ፣ መንግስት አለ ብለን ግብር ለመክፈል እንቸገራለን በማለታቸው ነው የትናንትው ግጭት የተነሳው። የአካባቢው ነዋሪዎች ለ

የኦሮሚያ ህዝብ ለሲዳማ ህዝብ ያለውን ኣጋሪነት ኣሳየ፤ በማልጋ ወረዳ በመንግስት ሃይል እና በወረዳው ነዋሪዎች መካከል ተከስቶ በነበረው ግጭት ከሲዳማ ህዝብ ጎን በመቆም ድጋፋን ገለጸ

ከትናንትና ወዲያ በማልጋ ወረዳ ከሲዳማ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተነሱ ጉዳዩች ላይ ሲመክር የነበረውን የወረዳውን ህዝብ ስብሰባ ለመበተን በሞከሩ የመንግስት ልዩ ሃይል እና በስብሰባው ተሳታፊዎች መካከል ተከስቶ በነበረው ግጭት የኦሮሞ ተወላጆ ከሲዳማ ጎን በመቆም የልዩ ሃይሉን ድርጊት ተቃውመዋል። የወራንቻ ኢንፎ ርሜሽን ኔትዎርክ ከኣካባቢው የሚወጡትን ዜናዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የኣጎራባች የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች እና ሲዳማ ለብዙ ዘመናት ኣብረው የኖሩ፤ተጋብተው  የተዋለዱ ወንድማማች ህዝቦች በመሆናቸው ኣንዱ ህዝብ ሲበደል ሌላው ቆሞ ኣያይም። ለዚህም የኦሮሞ ህዝብ የሲዳማ ህዝብ ላነሳው የክልል ይገባኛል ጥያቄ ከመንግስት በኩል እየተሰጠው ያለው ኣሉታዊ ምላሽ ትክክለኛ ባለመሆኑ ከሲዳማ ህዝብ ጎን በመቆም ኣጋሪነቱን በመግለጽ ላይ መሆኑ ተነግሯል። በጉጉማው ግጭት ሰው መሞቱን የተነገረ፤ ሲሆን ዘጠኝ የፈዴራል ፖሊስ እና ሶስት የወረዳው ነዋሪዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።

የመልጋ ወረዳ ህዝብ ከ ፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ሲጋጭ ዋለ

ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአዋሳ ከተማ  በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ ዛሬ በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ ሲቆስሉ ከህዝቡም በተመሳሳይ ሰዎች ቆስለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ለእረፍት ወደ አካባቢው ከሄዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በመሆን፣ በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተከሰተውን ችግር እየተወያዩ በነበረት ጊዜ የፌደራል ፖሊስ አባላት  ለመበትን ጥረት በማድረጋቸው ግጭቱ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል ” በግጭቱ እስካሁን በፖሊስና በህዝብ ወገን ሶስት ሶስት ሰዎች ሲቆስሉ፣ ሁለት መኪኖች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል:: ውጅግራ በሚባለው የወረዳው ከተማ 7 ሰዎች መታሰራቸውን፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት መሰፈራቸው ታውቋል። ከታሰሩት መካከል ታምሩ በሻጋ፣ ሲናራ ሲዳሞ፣ አየለ፣ ዘለላምእንዲሁም  ደረጃ ናስሩ የሚባሉት ይገኙበታል። በአሁኑ ጊዜ አካባቢው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ስቱዲዮ ከገባን በሁዋላ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን መረጃዎች የደረሱን ሲሆን፣ ዘጋቢዎቻችን እስካሁን ለማረጋገጥ አልቻሉም። ቦርቻ፣ ጭኮ እና ሌሎች አካባቢዎችም ከፍተኛ ውጥረት ይታያል። ህዝቡ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዝም ብለን አንሞትም በማለት ባገኘው መሳሪያ ሁሉ ለመከላከል መቁረጡን ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚናገሩት። በሲዳማ ዞን ከክልል እና ከመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ካለፈው ወር ጀምሮ ተደጋጋሚ ግጭት ሲከሰት  መቆየቱን መዘገባችን ይታወሳል።

ሰበር ዜና ፦ በሲዳማ ዞን በማልጋ ወረዳ በመንግስታ ሃይሎች እና በሰላማዊ ሰዎች መካከል በተከሰው ግጭት ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸው ተነገረ

በዛሬው እለት በማልጋ ወረዳ በጉጉማ ከተማ የሲዳማ ህዝብ ለክልሉ መንግስት ለቀረበው የክልል ጥያቄዎች የመንግስት ኣካል የሰጠውን ኣሉታዎ ምላሽ በመቃዎም ተቃውሞኣቸውን በገለጹ ሰላማዊ ሰዎች እና በመንግስት ልዩ ሃይል መካከል ግጭት ተከስቷል። ያልተረጋገጡ ከኣካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ ወደ ማታ ኣካባቢ በተከሰተው በዚህ ግጭት ሁለት ሰዎች ሞተዋል እና ሁለት ሰዎች ደግሞ በጹኑ ቆስለዋል። ግጭቱን ተከትሎ ኣካባቢው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ያለ ሲሆን፤ በመሆኑ በርካታ ቁጥር ያለው የመንግስት ልዩ ሃይል ወደ ኣካባቢው በመግባት ላይ መሆኑን የኣይን እማኞች ለወራንቻ ኢንፎ ርሜሽን ኔትዎርክ ገልጸዋል። ሞቱና ቆሰሉ ስለተባሉ ሰዎች ቁጥር እና ማንነት በተመለከተ እንዲሁም  ስለ መረጃው ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ወደ ኣካባቢው በስልክ ያደረግ ነው መኩራ  በኔዎርክ መጨናነቅ ምክንያት ኣልተሳከም። ሆኖም በጉዳዩ ላይ ማረጋገጫ እና ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ለኣንባቢዎቻችን እናሳውቃለን።

Another Meles Zenawi’s agent ‘Tsegaye Berhe’ sent to terrorize Sidama people is in Hawassa

from http://www.sidama.org/persecution/2012-07-23-another-meles-zenawi-agent-tsegaye-berhe-terrorizing-sidama-people-in-hawassa.pdf Mele’s regime cadres are doing what it takes to intimidate and coerce Sidama people to oblige them to abandon their quests for regional self administration that was accorded to the nations whose populations are 15 times smaller than theirs. Unrepentant of its crimes for breaking its constitution, Meles’s regime cadres are working day and night to stifle Sidama people’s quest for the said rights. We have been updating the Sidama people, Ethiopians and the global communities about the whole sagas surrounding this issue since the regime introduced its Manifesto on Federalizing the Sidama capital town ‘Hawassa since the 4th of June 2012; the action that angered Sidama people from corner to corner. Since then, the Sidama people are legally & peacefully demanding their rights whilst the regimes’ cadres are leaving no stone unturned