Posts

የመልጋ ወረዳ ህዝብ ከ ፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ሲጋጭ ዋለ

ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአዋሳ ከተማ  በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ ዛሬ በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ ሲቆስሉ ከህዝቡም በተመሳሳይ ሰዎች ቆስለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ለእረፍት ወደ አካባቢው ከሄዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በመሆን፣ በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተከሰተውን ችግር እየተወያዩ በነበረት ጊዜ የፌደራል ፖሊስ አባላት  ለመበትን ጥረት በማድረጋቸው ግጭቱ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል ” በግጭቱ እስካሁን በፖሊስና በህዝብ ወገን ሶስት ሶስት ሰዎች ሲቆስሉ፣ ሁለት መኪኖች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል:: ውጅግራ በሚባለው የወረዳው ከተማ 7 ሰዎች መታሰራቸውን፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት መሰፈራቸው ታውቋል። ከታሰሩት መካከል ታምሩ በሻጋ፣ ሲናራ ሲዳሞ፣ አየለ፣ ዘለላምእንዲሁም  ደረጃ ናስሩ የሚባሉት ይገኙበታል። በአሁኑ ጊዜ አካባቢው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ስቱዲዮ ከገባን በሁዋላ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን መረጃዎች የደረሱን ሲሆን፣ ዘጋቢዎቻችን እስካሁን ለማረጋገጥ አልቻሉም። ቦርቻ፣ ጭኮ እና ሌሎች አካባቢዎችም ከፍተኛ ውጥረት ይታያል። ህዝቡ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዝም ብለን አንሞትም በማለት ባገኘው መሳሪያ ሁሉ ለመከላከል መቁረጡን ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚናገሩት። በሲዳማ ዞን ከክልል እና ከመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ካለፈው ወር ጀምሮ ተደጋጋሚ ግጭት ሲከሰት  መቆየቱን መዘገባችን ይታወሳል።

ሰበር ዜና ፦ በሲዳማ ዞን በማልጋ ወረዳ በመንግስታ ሃይሎች እና በሰላማዊ ሰዎች መካከል በተከሰው ግጭት ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸው ተነገረ

በዛሬው እለት በማልጋ ወረዳ በጉጉማ ከተማ የሲዳማ ህዝብ ለክልሉ መንግስት ለቀረበው የክልል ጥያቄዎች የመንግስት ኣካል የሰጠውን ኣሉታዎ ምላሽ በመቃዎም ተቃውሞኣቸውን በገለጹ ሰላማዊ ሰዎች እና በመንግስት ልዩ ሃይል መካከል ግጭት ተከስቷል። ያልተረጋገጡ ከኣካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ ወደ ማታ ኣካባቢ በተከሰተው በዚህ ግጭት ሁለት ሰዎች ሞተዋል እና ሁለት ሰዎች ደግሞ በጹኑ ቆስለዋል። ግጭቱን ተከትሎ ኣካባቢው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ያለ ሲሆን፤ በመሆኑ በርካታ ቁጥር ያለው የመንግስት ልዩ ሃይል ወደ ኣካባቢው በመግባት ላይ መሆኑን የኣይን እማኞች ለወራንቻ ኢንፎ ርሜሽን ኔትዎርክ ገልጸዋል። ሞቱና ቆሰሉ ስለተባሉ ሰዎች ቁጥር እና ማንነት በተመለከተ እንዲሁም  ስለ መረጃው ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ወደ ኣካባቢው በስልክ ያደረግ ነው መኩራ  በኔዎርክ መጨናነቅ ምክንያት ኣልተሳከም። ሆኖም በጉዳዩ ላይ ማረጋገጫ እና ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ለኣንባቢዎቻችን እናሳውቃለን።

Another Meles Zenawi’s agent ‘Tsegaye Berhe’ sent to terrorize Sidama people is in Hawassa

from http://www.sidama.org/persecution/2012-07-23-another-meles-zenawi-agent-tsegaye-berhe-terrorizing-sidama-people-in-hawassa.pdf Mele’s regime cadres are doing what it takes to intimidate and coerce Sidama people to oblige them to abandon their quests for regional self administration that was accorded to the nations whose populations are 15 times smaller than theirs. Unrepentant of its crimes for breaking its constitution, Meles’s regime cadres are working day and night to stifle Sidama people’s quest for the said rights. We have been updating the Sidama people, Ethiopians and the global communities about the whole sagas surrounding this issue since the regime introduced its Manifesto on Federalizing the Sidama capital town ‘Hawassa since the 4th of June 2012; the action that angered Sidama people from corner to corner. Since then, the Sidama people are legally & peacefully demanding their rights whilst the regimes’ cadres are leaving no stone unturned

ሲዳማ ቡና አሰልጣኙን ዳኜን አሰናብቷ በቦታው ሌላ ሰው ሊቀጥር ነው የሀዋሳ ከነማው ዘላለም ሊገባ ነው ተብሎ እየተጠበቀ ነው

ማክሰኞ ሐምሌ 3 ቀን 2004 ዓ.ም ፀጋዬ ኪዳነማሪያም የሐረር ቢራ አሰልጣኝ ቡና ገብቷል ፣ዛሬ ሲዳማ ቡና አሰልጣኙን ዳኜን አሰናብቷ በቦታው ሌላ ሰው ሊቀጥር ነው የሀዋሳ ከነማው ዘላለም ሊገባ ነው ተብሎ እየተጠበቀ ነው፣ ባንኮች ጥላሁንን አሰናብቶ ውበቱ አባተን በሀላፊነት መድቧል፣ የሲዳማ ቡናው ግብ ጠበቂ ሲሳይ ባንጫ 550ሺ ብር ተከፍሎት ደደቢት ፈርሟል፣ መሱድ መሐመድ ሌላ ክለብ 650ሺ ብር ቀርቦለታል ዛሬ ከቡና ጋር ተነጋግሯል ከጠየቀው ክለብ የቀረበለትን ገንዘብ ሰምተዋል ቡና ምን ያህል ሊከፍለው እንደሚፈልግ ማወቅ ይፈልጋል ድርድር ላይ ናቸው ፡፡ ይህን ያህል ክፈሉኝ አላለም፡፡ ከሌላ ክለብ የቀረበለትን ስለሰሙ የነሱን ዋጋ ማወቅ ይፈልጋል፡፡ የክለቡን መልስ ይጠበቃል፡፡ ቡና መሱድ፣ዳዊት ( ሞገስና እስጢፋኖስ) መዳኔ፣ሙሉዓለም ኮንትራታቸው አልቋል፡፡ የወቅቱን ገበያ አይተው ክለቡ ሊደራደር ይገባል፡፡ ጊዮርጊስ አዳነ እና ያሬድ ኮንትራታቸው አልቋል፡፡ ለዘንድሮ 1 ሚሊየን ነው የተጠየቀው፡፡ በድርድር እስከ 700ሺ ይፈረማል ነው የተባለው፡፡ ተጫዋቹ በእግር ኳሱ ለውጥ ማምጣቱ አለማምጣቱ ሳይሆን ዛሬ በፊርማ መልክ ለነገ መተዳደሪያቸው ለመስጠት የተሸለ ነው የሚሆነው፡፡ በሌላ በኩል በሴቶች በኩል የፊርማ ክፍያ እየተለመደ መጥቷል በጣም ጥሩ ጅማሬ ነው፡፡ በሴቶቹ የፊርማ የተጀመረው የዛሬ ሶስት አመት አካባቢ ነው፡፡ በ2002 ሰሚራ 3ሺ አገኘች፡፡ ባለፋው ዓመት ብርቱካን ወደ ደዲቢት ስትገባ 35ሺ በማግኘት ሪከርድ ሰበረች፡፡ አሁን ደግሞ ዳጋማዊት ወደ ባንክ በ50ሺ ብር ለመዘዋወር ስምምነት ላይ ደርሳለች፡፡ ዳጋማዊት የብሔራዊ ቡድን ተጠባባቁ በረኛ ነች፡፡\ http://librogk.com/2010-08-10-08-41-47.html

HwU’s department of Informatics in collaboration with Google

Image
HwU’s department of Informatics in collaboration with  G o o g l e  Company has started capacity building project on computer technology for teachers and students selected from governmental and non-governmental schools around Hawassa. Mr.Tesfaye Baye, lecturer at informatics department and the project coordinator noted that the main objective of the training is enhancing teachers’ and students’ computer skills at the lower level mainly at high& preparatory schools there by making them beneficiaries of modern computer technologies. In the training, that lasts for a year (2012/13 academic year), it is intended to involve more than 500 teachers and students. On top of that, it was noted Google Company has donated 10,000 US dollars to successfully run the project. It was also noted that the university has won this project of Google Company competing with other strong East African Universities.   http://www.hu.edu.et/hu/index.php/84-hawassa-university/events/news/197-hwus