ታሪክ ተደገመ፤ከዛሬ 10 ኣመት በፊት እንደተደረገው ሁሉ ዛሬም የክልል ጥያቄውን ተከትሎ የሲዳማ ህዝብ ሰብኣዊ እና ፖለቲካዊ መብት ታፈነ፤ ሲዳማዎ ች በገዛ መሬታቸው የመወሰን መብት ተነፈጉ
በፉቄ ዲሬሞ ከሃዋሳ ሲዳማ የሲዳማ ህዝብ እንደ ፈረንጆ ች ዘመን ኣቆጣጠር ከ1993 ኣንስቶ በኣቅጣጫ ከሚጠራው ክልል ጋር ከተጠረዘ ጊዜ ጅምሮ፤ ክልል ይገባኛል ጥያቄ በተደጋጋሚ ኣንስቷል። ሲዳማ የክልል ይገባኛል ጥያቄ ምንም እንኳን በሰላማዊ መንገድ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት በየጊዜው የቀረቡ ቢሆኑም ለጥያቄው ከሚመለከተው ኣካል የተሰጡ ምላሾች ግን ህገ መንግስቱን በማይፈቅደው መ ንገድ መሆናቸው ብዙዎችን ግራ ኣጋብተዋል። የዛሬ ኣስር ኣመት የህገ መንግስቱ ኣርቃቅዎ ች እና ኣጽዳቅዎች ህገ መንግስቱ በማይፈቅደው መንገድ የተሰጡት የክልል ጥያቄው ምላ ሽ ከሃምሳ በላይ ለሚሆኑት ሲዳማዎች ሞት እና ከመቶ በላይ ለሚሆኑት ደግሞ መቁሰል ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። ከኣስር ኣመት በሃሏ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር እንከልሳለን ብለው በያዙት ቀጠሮ መሰረት የደኢዴን ማእከላዊ ኣመራር ኣባላት በቅርቡ በጻፉት ፍሬፍርስኪ የማወያያ ጽሁፍ ለሲዳማ ህዝብ ያላቸውን ንቀት በይፋ ኣሳይቷል። ንቀተቸው ያንገበገበው የሲዳማ ህዝብ ላሰማው ህዝባዊ ንቅናቄ ምላሽ በማን ኣለብኝነት፤ በጉልበታቸው ተማምነው ያሰፈሯቸው የጸጥታ ሃይሎች በተለይ ሃዋሳ ከተማ ውስጥ ሲዳማዎችን በኣደባባይ እየተደበደበ ነው። የሲዳማ ህዝብ ለመብቱ እንድታገሉለት መርጦ የሾማቸው ሹመኞች ሆዳቸውን ከመሙላት ባሻገር ለመረጣቸው ህዝብ መብት መከበር ምንም ማድረግ ኣልቻሉም እና ህዝቡ ስበደል ኣይተው እንዳለዩ በመለፍ ላይ ናቸው። እስቲ የዛሬ ኣስር ኣመት በፊት የነበረው ሁኔታ ምን ይመስል እንደት ነበር የሚቀጠለውን ጽሁፍ ያንብቡ። Human Rights Abuses Escalate In Sidama, Ethiopia, Following A Popular Dema