ሲዳማ ውስጥ ሰዎች እየተራቡ ነው፡ህጻናት በተመጠጠነ ምግብ እጦት ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ ነው።
ሲዳማ በታሪኩ የተራበባቸው ግዚያት ብዙም ኣይደለም። ሲዳማ መራብ የጀመረውም ከቅርብ ኣመታት ወዲህ ነው። ሲዳማ ከሚመገበው የምግብ ኣይነት ማለትም እንሴት ካለው ደርቅን የመቋቋም ኣቅም የተነሳ ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ የሚያጠቃውና በተለያዩ መዝገቤ ቃላት ለኣገሪቱ እስከ ብያኔ መስጫነት እያገለገለ ያለው ረሃብ ብዙ ጊዜ የሲዳማን ኣካባቢ ኣይዳፈሪም ነበር። ታዲያ ዛሬ ዛሬ ያ ታሪክ ተቀይሮ የሲዳማ ህዝብ እየተራበ እና የውጭ እርዳታ መጠባበቅ መጀመሩ እየተነገረ ነው። ከዛሬ ሰባት እና ስምንት ኣመታታ በፊት የሲዳማ ህጻናት በተለይ በቦርቻና በሽቤዲኖ ወረዳዎች ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በተመጣጠኔ ምግብ እጦት ለበሽታ ተዳርገው እንደነበር ይታወሳል፤ በወቅቱ ኣለም ኣቀፍ ድርጅቶች ባደረጉት ከፍተኛ ህይወት የመታደግ ርብርብ የበርካታ ህጻናትን ህይወት ለመታደግ ተችሏል። የኣከባቢው ባለስልጣናት ላለፉት ኣስር ኣመታት በኣከባቢው የምግብ ዋስትናን በተመለከተ ይህ ነው የሚባል ስራ ባለመስራቻቸው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኣካባቢ በድጋሚ በረሃብ መጠቃቱን እና ህጻናትም በተመጠጠነ ምግብ እጥረት ተጠቅተው ወደ እርዳታ መስጫ ጣቢያዎች በመጉረፍ ላይ መሆናቸውን የተለያዩ ኣለም ኣቀፍ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በሪፖርታቸው እያመለከቱ ነው። በቦርቻ ወረዳ ህጻናት በተመጣጠኔ ምግብ እጥረት በየትምህርት ቤቶች ተስላፍልፈው እየወደቁ መሆ ናቸው እና የበሰባቸው ደግሞ ወደ ማገገሚባ ጣቢያዎች በመግባት ላይ ናቸው። በየጣቢያዎቹ ህጻናቱን ይዘው የመጡ እናቶች እንደምሉት ከሆነ በኣከባቢው ካለው ድርቅ የተነሳ ልጆ ቻቸውን መመገብ ኣልቻሉም። ወደ ኣካባቢው በኣስቸኳይ የምግብ እርዳታ ካልተላከበሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ልደርስ እንደምችል ኣለም ኣቀፍ ድርጅቶች በሪፖርታቸው ኣመልክቷል። ሪፖር