Posts

በስብሰባው ላይ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሲዳማ ተወላጆችና በሌሎች ነዋሪዎች መካከል ልዩነት በመፍጠር ግጭት እንዲፈጠር ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካለቸውም ተባለ

በአዋሳ ከተማ በተደረገው ስብሰባ ህዝቡ ስብሰባውን ረግጦ ወጣ ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት የክልሉ መስተዳደር ሀላፊ የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎችን በአዋሳ ባህል አዳራሽ ውስጥ በሰበሰቡት ወቅት ነው ውዝግቡ የተፈጠረው። አቶ ሽፈራው ” ሲዳማ ክልል እንዲሆን የጠየቃችሁት መቼውንም አይሳካም ቁርጡን እወቁት ” በማለት ሲናገሩ ተሰብሳቢው ተቃውሞውን ገልጧል። በአዋሳ ተወልደው የኖሩ የሲዳማ ብሄረሰብ ተወላጅ ያልሆኑ የከተማው ነዋሪዎች ” እኛን የሲዳማ ህዝብ አላጠቃንም፣ ሲዳማ እኛን አይጠላንም፣ እኛን እያስጠቃን ያለው አመራሩ የሚያወጣው ህግ ነው፣ እኛ ተከባብረን፣ ተዋልደን የምንኖር ህዝብ ነን” በማለት አስተያየት ሲሰጡ፣ ከሲዳማ ተወላጆች በስተቀር የሌላ አካባቢ ተወላጆች አዳራሹን ለቀው እንዲወጡ አቶ ሽፈራው ሲናገሩ ነው፣ ውዝግቡ የተፈጠረው። የከተማው ነዋሪዎችም እኛ የትም አንሄድም፣ ብትፈልጉ እንደ ጓደኞቻችን እዚሁ እሰሩን በማለት ሲቃወሙ ከዋሉ በሁዋላ አንድ ሽማግሌ ” ህዝቡ አልቆ ሲዳማ የሚለው ስም እሲኪሰረዝ ድረስ ትግላችንን አናቆምም፣ ጥያቄያችን እስኪመለስ ድረስ” በማለት ተናግረው አዳራሹን ለቀው ሲወጡ፣ ህዝቡም ተከትሎአቸው ወጥቷል። በስብሰባው ላይ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሲዳማ ተወላጆችና በሌሎች ነዋሪዎች መካከል ልዩነት በመፍጠር ግጭት እንዲፈጠር ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካለቸውም ሲል በአዳራሹ የተገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል። ህዝቡም በግልጽ ከሌሎች ወንድሞቻችን ጋር ልታጋጩን አትሞክሩ በማለት ተቃውሞውን አሰምቷል። በቡድን የተደራጁት የአዋሳ ወጣቶች ህዝቡን እያስመቱ የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናት የሚል በርካታ ስም ዝርዝሮችን የያዙ ወረቀቶችን እየበተኑ ነው። የዩኒቨርስቲ ተማሪ

The Sidama people are surrounded and forced not to move about by the Special Forces which are currently granted shoot to kill authority by the government. The Woredas such as Aleta Wondo, Yirgalem, Bensa, Harbegona, Chuko, Arroresa, etc are facing harsh treatments by the Special Forces.

The Second Round Massacre of Sidama People by Prime Minister Meles Zenawi and Deputy Prime Minister Hailemariam Desalegn of Ethiopia 26 June 2012 1.  YET ANOTHER Massacre of Sidama people of Ethiopia BY MELES ZENAWI AND HAILEMARIAM DESALEGN has begun. The second round of the massacre of innocent people of Sidama in Ethiopia started a week ago.  However, the first massacre of about 100 innocent people of Sidama took place at a village called Loqqe in Hawassa at about midday on Friday 24 th  May 2002.  The killing of Sidama people went on throughout the day and the bodies were dumped at Hawassa Health Centre compound and the Police station.  Other bodies were collected from the maize plot in Hawassa.  The main architects of the massacre were Bereket Simon and Hailemariam Desalegn with direct instruction and approval by Meles Zenawi. The following personalities took the pleasure of finalising and authorising the massacre of Sidama people on that day, 10 years ago: Bereket Simo

የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ አሁን የተነሣ ሳይሆን ለዓመታት ሲታገልለት የቆየ መሆኑን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ፡፡

Image
ኢሕአዴግ በ1984 ዓ.ም አምስት የነበሩትን ክልሎች ወደ አንድ በማምጣት አሁን ደቡብ የሚባለውን ክልል የፈጠረበት ሁኔታም ድንገተኛና የሚመለከታቸው ያልመከሩበት ነው ሲሉ የክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተችተዋል፡፡ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ - ሲአን ለሰጠው መግለጫ መነሻ የሆነው የሃዋሣ ከተማን ዕጣ ፈንታ አስመልክቶ በክልሉ ገዥ ፓርቲ ለውይይት ቀረበ የተባለው ሠነድ ነው፡፡ ሜትሮፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራው በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሠነድ ከግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ለውይይት መቅረቡን ፓርቲው አስታውቋል፡፡ ሠነዱ ለውይይት የቀረበውም ለሲዳማና ለሃዋሣ ከተማ አስተዳደር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ለሲዳማ ተወላጅ የደኢሕዴን አባላት መሆኑን ጠቅሷል፡፡ ሠነዱ ሃዋሣ በተለያዩ ብሔረሰቦች ስብጥር እንድትተዳደር የሚጠይቅ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ ይህንን ሠነድ አጥብቆ እንደሚቃወመው የገለፀው ሲአን የዞኑ ተወላጆችም ይቃወሙታል ባይ ነው፡፡ ፓርቲው በዚሁ መግለጫ የሲዳማ ሕዝብ “ክልል የመሆን ጥያቄ”ም ሊመለስ ይገባል ሲልም አሣስቧል፡፡ የሃዋሣው ሠነድ ጉዳይ ወቅታዊ ይሁን እንጂ የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ በተደጋጋሚ የተነሣና ሲታገልለት የቆየ መሆኑንም ሲአን አስታውቋል፡፡ ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡ ሜትሮፖሊታን ሃዋሣ እና “ክልል” ሲዳማ እያነጋገሩ ነው

በሲዳማ ዞን ጭኮ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

Image
ሰኔ ፲፱ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የወረዳው የመረጃ ምንጭ እንደገለጠው ተቃውሞው የተነሳው ዛሬ 4 ሰአት ላይ ነው። በትናንትናው እለት እንደዘገብነው የካናዳ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተነሳውን ተቃውሞ ያነሳሱት ባለሀብቶችና ተቃዋሚዎች ናቸው በማለት የተናገሩትን ለመቃወም ነበር ዛሬ ሰለማዊ ሰልፉ የተጠራው። አቶ ሽፈራው ያደረጉትን ንግግር ያስቆጣቸው የጭኮ ወረዳ ነዋሪዎች በተወካዮቻቸው አማካኝነት ሰለማዋዊ ሰልፍ ለማድረግ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄያቸውን ወረዳው አስተዳዳሪ ለሆኑት ለአቶ አሻግሬ ጀምበሬ ደብዳቤ አስገብተው ነበር። በዚህም መሰረት ዛሬ ጧት የተቃውሞ ሰልፉን ለማካሄድ ወደ ስታዲየሙ ሲያቀኑ የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ክፍሌ የፌደራል ፖሊስ በመጥራት የህዝቡ መሪዎች እንዲያዙ አድርገዋል። የከተማው ነዋሪ ተወካዮችን ለማስለቀቅ ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ፣ ፖሊሶች ለተቃውሞ የመጣውን ሰላማዊ ሰው በቆመጥ እየደበደቡ ለመበትን ሲሞክሩ ቆይተዋል። ከሰአት በሁዋላ የከተማው ህዝብ በነቂስ በመውጣት የታሰሩት መሪዎች እንዲፈቱለት ፖሊስ ጣቢያውን በመክበብ ጥያቄውን አቅርቧል። ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ህዝቡ የፖሊስ ጣቢያውን እንደከበበ ነበር። ህዝቡን ውስጥ ለውስጥ ለአመጽ እንዲነሳ አድርገዋል በሚል የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ዘላለም ላላም ታስረዋል። እንዲሁም ከመንግስት ሰራተኞች መካከል አቶ ገረመው ፊሳ፣ አቶ ኤፍሬም ተፈራ፣ ኢዛ እንዳለና ንጉሴ ታደሰ የታሰሩ ሲሆን፣ ባለሀብቱ አቶ አስቻለው በቀለም ታስረዋል። አቶ ገረመው ፊሳ፣ አቶ ኤፍሬም ተፈራ፣ አቶ

ደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖረዉ የሲዳማ ብሔረሰብ እራሱን የቻለ መስተዳድር እንዲሰጠዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባደረገዉ ሠላማዊ ሠልፍ ጠየቀ

Image
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ እንዳስታወቀዉ የሕዝቡ ጥያቄ ሠላማዊና የሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌዎች የጠበቀ ነዉ።በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድርን ከኦሮሚያ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞት፥ መቁሰላቸዉ ተነግሯል። ደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖረዉ የሲዳማ ብሔረሰብ እራሱን የቻለ መስተዳድር እንዲሰጠዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባደረገዉ ሠላማዊ ሠልፍ ጠየቀ።በደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሠ-ከተማ በአዋሳና በአካባቢዉ ከተሞች አደባባይ የወጣዉን ሕዝብ ለመቆጣጠር መንግሥት በርካታ ፀጥታ አስከባሪዎች አስፍሯል።የሲዳማ አርነት ንቅናቄ እንዳስታወቀዉ የሕዝቡ ጥያቄ ሠላማዊና የሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌዎች የጠበቀ ነዉ።በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድርን ከኦሮሚያ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞት፥ መቁሰላቸዉ ተነግሯል።ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ከአዲስ አበባ ሁኔታዉን ተከታትሎታል። ሙሉ ዘጋባውን በሚቀጥለው ሊንክ ያዳምጡ ሠላማዊ ሠልፍና ግጭት በደቡብ ኢትዮጵያ