በደቡብ ክልል የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር የተጀመረው የለውጥ አሰራር መሻሻል አሳይቷል
የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ጉዬ በበኩላቸው በስራቸው በሚገኙ 19 ወረዳዎችና ሀዋሳን ጨምሮ በሁለት የከተማ አስተዳደሮች አዲሱ የለውጥ አሰራር ተግባራዊ ተደርጓል ሃዋሳ, ጥር 5 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በደቡብ ክልል የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጎልበትና ለማጠናከር የተጀመረው የለውጥ አሰራር መሻሻል ማምጣቱን አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችና ባለጉዳዮች ገለጹ፡፡ ዘንድሮ በክልሉ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ለሚበልጡ ሰዎች የህግ ግንዛቤ የሚያሳድግ ትምህርት እንደሚሰጥም ተመልክቷል፡፡ የክልሉ ፍትህ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል እንዳሻው ስመኖ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ተከትሎ የመጣው አዲሱ የውጤት ተኮር የምዘና ስርዓት ፕሮግራም በክልሉ ከፍተኛ ለውጥ አምጥቷል፡፡ በዚህም ቀደም ሲል ፍርድ ቤቶች፣ ዐቃቢያነ ህግ፣ ማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ በተናጠል የሚያካሄዱትን የተበታተነ አሰራር በማስወገድ በአንድ ላይ ተቀናጅተው እንዲሰሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በተለይ የምርመራና የክስ፣ የህግ ጥናት ረቂቅ ዝግጅትና ግንዛቤ መፍጠር፣ የጠበቆችና ሲቪክ ማህበራት ፍቃድ ውልና ምዝገባ ክትትል ከተገኙት ለውጦች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን አመልከተዋል፡፡ በዚህም የፍትህ አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ቀደም ሲል ከስድስት ወር በላይ የሚፈጀው አሁን በሰዓታት፣ በቀናት ቢበዛ እስከ አንድ ወር ባለው ጊዜ ውሳኔ እያገኙ ናቸው ብለዋል፡፡ ከወንጀልና ከፍትሃብሄር ክሶች ጋር ተያይዞ ንፁሃን እንዳይጎዱና አጥፊዎች እንዳያመልጡ የተቀመጠው ግብም ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የፍትህ አካላቱ ተቀናጅተው መስራታቸው ፈጣን ፍትህ ለተጠቃሚው ለመስጠት ትል