Posts

በደቡብ ክልል የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር የተጀመረው የለውጥ አሰራር መሻሻል አሳይቷል

የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ጉዬ በበኩላቸው በስራቸው በሚገኙ 19 ወረዳዎችና ሀዋሳን ጨምሮ በሁለት የከተማ አስተዳደሮች አዲሱ የለውጥ አሰራር ተግባራዊ ተደርጓል ሃዋሳ, ጥር 5 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በደቡብ ክልል የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጎልበትና ለማጠናከር የተጀመረው የለውጥ አሰራር መሻሻል ማምጣቱን አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችና ባለጉዳዮች ገለጹ፡፡ ዘንድሮ በክልሉ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ለሚበልጡ ሰዎች የህግ ግንዛቤ የሚያሳድግ ትምህርት እንደሚሰጥም ተመልክቷል፡፡ የክልሉ ፍትህ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል እንዳሻው ስመኖ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ተከትሎ የመጣው አዲሱ የውጤት ተኮር የምዘና ስርዓት ፕሮግራም በክልሉ ከፍተኛ ለውጥ አምጥቷል፡፡ በዚህም ቀደም ሲል ፍርድ ቤቶች፣ ዐቃቢያነ ህግ፣ ማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ በተናጠል የሚያካሄዱትን የተበታተነ አሰራር በማስወገድ በአንድ ላይ ተቀናጅተው እንዲሰሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በተለይ የምርመራና የክስ፣ የህግ ጥናት ረቂቅ ዝግጅትና ግንዛቤ መፍጠር፣ የጠበቆችና ሲቪክ ማህበራት ፍቃድ ውልና ምዝገባ ክትትል ከተገኙት ለውጦች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን አመልከተዋል፡፡ በዚህም የፍትህ አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ቀደም ሲል ከስድስት ወር በላይ የሚፈጀው አሁን በሰዓታት፣ በቀናት ቢበዛ እስከ አንድ ወር ባለው ጊዜ ውሳኔ እያገኙ ናቸው ብለዋል፡፡ ከወንጀልና ከፍትሃብሄር ክሶች ጋር ተያይዞ ንፁሃን እንዳይጎዱና አጥፊዎች እንዳያመልጡ የተቀመጠው ግብም ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የፍትህ አካላቱ ተቀናጅተው መስራታቸው ፈጣን ፍትህ ለተጠቃሚው ለመስጠት ትል

በሀዋሳ ከተማ የተገነቡ አንድ ሺህ 675 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች በእጣ ተላለፉ

Image
አዋሳ, ጥር 5 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በሀዋሳ ከተማ በ200 ሚልዮን ብር የተገነቡ አንድ ሺህ 675 የጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ዛሬ ተመዝግበው ለሚጠባበቁና ቅድመ ክፍያ ላጠናቀቁ ግለሰቦች በእጣ ተላለፈ፡፡ መንግስት ባመቻቸው የቤቶች ልማት የመኖሪያ ቤት ባለቤት በመሆናቸው መደሰታቸውንም ተጠቃሚዎች ገልጸዋል፡፡ በሀዋሳ ከተማ አራት አካባቢ ተገንብተው በእጣ ለነዋሪዎች ከተላለፉት የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል አንድ 575 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቀሪዎቹ 100 የንግድ ቤቶች መሆናቸውን የከተማው ከንቲባ አቶ ዮናስ የሱፍ በዕጣው ስነ ስርዓት ላይ አስታውቀዋል፡፡ ሶስት ደረጃ ያላቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንግስት የተጠቃሚዎችን የመክፈል አቅም በማየት ያደረገውን ከፍተኛ ድጎማና ድጋፍ ሳይጨምር ከንግድ ቤቶቹ ጋር 200 ሚልዮን ብር ወጪ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የተቀናጀ የቤቶች ፕሮግራም በከተሞች ልማት ስራ ውስጥ ለቤቶች ልማት ልዩ ትኩረት የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም የሚመጥን የቤት ልማት ስራ በማከናወን የመጠለያ ችግርን መቅረፍ፣ የቁጠባ ባህልን በማዳበር ሰፊ የስራ ዕድልና የቴክኖሎጂ ሽግግር በመፍጠር በኩል ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡ በከተማው ቀደም ሲልም የአንድ ሺህ 648 የጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ለተጠቃሚዎች መተላለፋቸውን ገልጸው ግንባታቸው 95 በመቶ የተጠናቀቀና ዕጣ የወጣላቸው 1 ሺህ 575 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መጋቢት 15/ 2004 ለባለዕድሎች እንደሚተላለፉ አስረድተዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ስራ አጥነትን የመቅረፍ አላማ እንዳለው ገልጸው በእስካሁኑ ሂደት ለ5ሺህ 985 ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን አስታውቀዋል፡፡ የደቡብ ክልል ቤቶች ልማት ኤጄንሲ ዋና ስራ አስኪያ አቶ ወ

በደቡብ ክልል የመሬት ይዞታ ባለቤትነት ምዝገባ ሥርዓትን ዘመናዊ ለማድረግ እየተሠራ ነው

Image
ሀዋሳ ፤ ጥር 04 2004 ዋኢማ  - በደቡብ ክልል የመሬት ይዞታ ባለቤትነት የምዝገባ ሥርዓትን በዘመናዊ መንገድ ለማካሄድ የሚያስችለውን የሙከራ ተግባር ማከናወኑን የክልሉ የተፈጥሮ ሀብትና የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አበራ ዊላ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል  እንዳስታወቁት የምዝገባ ሥርዓቱ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በሙከራ ደረጃ የተካሄደው በሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ወረዳ አባዶ ቀበሌ ውስጥ ነው ፡፡ በቀበሌው የ 2 ሺህ 528 አባወራና እማወራ አርሶአደሮች መሬት ተለክቶ በኮምፒዩተር በመመዝገብ የባለቤትነት ማረጋገጣጫ ሰነድ እንደተሰጣቸው ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡ የአርሶአደሮችን የመሬት ባለቤትነት ይዞታ ለማረጋገጥ ቀደም ሲል  የመሬት ልኬት ሥራው በገመድና በሜትር ሲካሄድ መቆየቱን ያስታወሱት ሥራ አስኪያጁ ይህም ሂደቱን አድካሚ ከማድረጉም በላይ የመሬቱን ይዞታ ሙሉ አቀማመጥ ለመለየትና መረጃዎችን በኮምፒዩተር ለማደራጀት አስቸጋሪ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ አዲሱ የይዞታ ባለቤትነት ምዝገባ  በሳተላይት ቴክኖሎጂ  በመታገዝ የሚካሄድ በመሆኑ የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች የየአንዳንዱን አርሶአደር የመሬት ይዞታ ሥፍራው ድረስ መጓጓዝ ሳያስፈልጋቸው ከቢሯቸው ሆነው ለማወቅ እንደሚያስችላቸው አስረድተዋል፡፡ በክልሉ በሙከራ ደረጃ የተካሄደው የመሬት ይዞታ ባለቤትነት የምዝገባ ሥርዓት ውጤታማ ስለመሆኑ ከክልልና ከፌዴራል በተውጣጡ ባለሙያዎች በተደረገ ግምገማ መረጋገጡን ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ ባለሥልጣኑ  በሙከራ የተገኙ ውጤቶችን መሠረት በማድረግ ሙሉ የመሬት ልኬቱን  በከፊል  የክልሉ ዞኖች እና በተመረጡ ወረዳዎች ለመጀመር  የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡ የመሬት ል

Kaaye kaamballi kayatamaho Sidamu osso

Image
New

በሃዋሳ ከተማ ወደ ባለሃብትነት የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ተመረቁ

Image
ሃዋሳ, ታህሳስ 27 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዝ ልማት የተሰማሩ ወጣቶች ሀገሪቱ ስራ አጥነትን በመቅረፍ ልማታዊ ባለሃብትን ለመፍጠር በምታደርገው ጥረት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገለጸ፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ተሰማርተው ወደ ልማታዊ ባለሃብትነት የተሸጋገሩ 16 ማህበራት መመረቃቸው ተገልጿል፡፡ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የከተማውን ነዋሪ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ በመቀየር በርካታ ስራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢንተርፕራይዞቹ በከተማው ስራአጥነትና ድህነትን በመቀነስ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር በሚደረገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኙ ገልጸው አመራሩ ባለሙያውና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ ጥንካሬ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ማህበራቱ ሙስናና ብልሹ አሰራር እንዲቀረፍ እንዲሁም ፍትሃዊ የሃብት አከፋፈልና አጠቃቀም በከተማው እንዲሰፍን እስካሁን ያበረከቱት አስተዋጽኦ አበረታች እንደነበር አስታውሰው ኪራይ ሰብሳቢነት በልማታዊ አስተሳሰብ እንዲለወጥ ጠንክረው ሊሰሩ አንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በሃዋሳ ከተማ በስምንቱ ክፍለ ከተሞች በተለያየ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ከ100 የሚበልጡ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማቶች እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ዮናስ በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የተቀናጀ ስራ ወደ ልማታዊ ባለሃብትነት የተሸጋገሩ 16 ማህበራት መመረቃቸውን ተናግረዋል፡፡ ማህበራቱ ባለፉት አምስት ዓመታት እያንዳንዳቸው ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገ