Posts

የኤርትራን መንግስት አስከፊ ስርዓት ለማስወገድ የሚያስችል አዲስ የስትራቴጂ ትግል የሚቀይስ የኤርትራ ብሄራዊ ጉባዔ ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ውይይት በሐዋሳ ተጀምሯል፡፡

Image
የኤርትራ ኮሚሽን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች ልዩነታቸውን አጥብበው የሀገሪቱን አምባገነን ስርዓት እንዲያስወግዱ ጥሪ አቀረበ ማክስኞ, 22 ህዳር 2011 16:23 የኤርትራ ህዝብ የጭቆና አገዛዝን በመቃወም ለበርካታ ዓመታት የታገለ ቢሆንም ከነጻነትም በኋላ በአምባገነን ስርዓት ለመገዛት ተገዷል፡፡ በውጤቱም የኤርትራ መንግስት በሚከተለው የአፈናና አገዛዝ ሀገሪቱ የሰብአዊ መብት የሚረገጥባትና ዜጎች በአፈና እና በፍርሃት የሚኖሩባት ለመሆን በቅታለች፡፡ በመሆኑም የኤርትራን መንግስት አስከፊ ስርዓት ለማስወገድ የሚያስችል አዲስ የስትራቴጂ ትግል የሚቀይስ የኤርትራ ብሄራዊ ጉባዔ ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ውይይት በሐዋሳ ተጀምሯል፡፡ ጉባዔው ከዚህ በፊት የተቋቋመው የኤርትራ ኮሚሽን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ባለፉት 16 ወራት የደረሰበትን አፈጻፀም ይገመግማል፡፡ የኤርትራ ኮሚሽን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሊቀመንበር አምሃ ዶሞኒካ ፍትህና ዴሞክራሲ የናፈቀውን የኤርትራን ህዝብ ከአምባገነን ስርዓት የማላቀቅ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም የስርዓቱ በርካታ ተቃዋሚዎች ልዩነታቸውን በማጥበብ የኤርትራን ህዝብ እንዲታደጉት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስትን አቋም ያቀረቡት የኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ ህዝብ ጫንቃ ላይ የተጫነውን አምባገነን አገዛዝ ለማስወገድ የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች አመርቂ ውጤት ማግኘት አልቻሉም፡፡ በመሆኑም የተጀመረው ጉባዔ የነበሩትን ችግሮች በማስወገድ የጋራ ግንዛቤና መግባባት ላይ እንደሚደርስ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ በኤርትራ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማስፈን ለሚደረገው ትግልም ወንድም የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስትም አስፈላጊው ድጋፍ

Ethiopian Music : Himanot Girma - Lembo

Image
New

Menalush Reta Dayo Bushu Ethiopian Ethiopia Habesha Amharic Music dvd Qu...

Image
New

Ethiopian new 2011 Mulatua Abate, Kai Kai * Sidama s Groove*

Image
New

በደቡብ ክልል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሶስት ቢሊዮን በሚበልጥ በጀት የልማት ስራ እያካሄዱ ነው

አዋሳ, ህዳር 5 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በደቡብ ክልል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመደቡት ከሶስት ቢሊዮን ብር የሚበልጥ በጀት ህብረተሱቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡ አብዛኛዎቹ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱት በሀዋሳ ከተማ ፣በሲዳማ ፣ በወላይታ ፣ በጋምጎፋ ፣ በሀዲያና በጉራጌ ዞኖች መሆኑን አስታውቀው የልማት ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ሁሉንም የክልሉ ህዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ታፈሰ ገዳዎ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ 2015 የሚካሄዱት የልማት ስራዎች 490 ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ ፕሮጀክቶቹ በ202 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንደሚካሄዱ አመልክተው የልማት ስራዎቹ የሚያተኩሩት በግብርና ፣በጤና ፣በትምህርት ፣ በመጠጥ ውሃ ፣በመስኖና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው ዘርፎች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱት በሀዋሳ ከተማ ፣በሲዳማ ፣ በወላይታ ፣ በጋምጎፋ ፣ በሀዲያና በጉራጌ ዞኖች መሆኑን አስታውቀው የልማት ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ሁሉንም የክልሉ ህዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። አፈጻጸማቸውን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ክትትልና ቁጥጥር እንደሚካሄድ ገልጸው መንግስታዊ ያልሆኑት ድርጅቶች ለመንግስት የልማት አጋር በመሆን የአምስት አመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለማሰካት የበኩላቸው አስተዋጾኦ እንዳላቸ ገልጸዋል፡፡