Posts

የሲዳማ ባህላዊ ሙዚቃ እና ጭፈራ

የኢትዮጽያ በርካታ ባህላዊ እሴቶች የሚገኝበት አንዱ የሲዳማ ክልል በደቡብ ክልል ከሚገኘኑት ከአስራ ሶስት ዞኖች አንዱ ነዉ። በለቱ ዝግጅታችን ስለ ሲዳማ ክልል በባህላዊ ሙዚቃዉ እና ጭፈራ የሚያጫዉቱን የባህል ኤክስፐርት የለቱ እንግዳችን ናቸዉ ሌላዉ ፎክሎር ማለት ምን ማለት ነዉ ? በባህል እና በፎክሎር መካከል ምን አይነት ልዪነት አለ። ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በለቱ አንድ ምሁርን ጋብዘናል። በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝም እና የመንግስት ኮሚኒኬሽን መስራ ቤት ዉስጥ የባህል ጉዳይ ኤክስፐርት እንደሆኑ የገለጹልን አቶ ስለሺ ወርቅነህ ከመስሪያ ቤታቸዉ የከፍተኛ ትምህርት እድልን በማግኘት በማግኘት በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጽያ ስነ - ጽሁፍና የፎክሎር ትምህርት መስክ የሁለተኛ አመት የማስትሪት ተማሪ ናቸዉ። የሲዳማ ዞን ባህላዊ ሙዚቃ እና ጭፈራ በተለያዩ መከሰቻዎች ቢታይም በተለይ ዞኑ የራሱ በሆነዉ የዘመን መለወጫ በአል ማለት ፍቼ በአል እንደሚታይ ይገልጻሉ። በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የስነ - ጽሁፍ እና የፎክሎር ትምህርት መስክ ለማስትሪት ዲግሪ የሁለተኛ አመት ተማሪ የሆኑት አቶ ስለሺ ወርቅነህን መነሻ በማድረግ በዪንቨርስቲዉ የሚሰጠዉን ትምህርት አስመልክቶ የፎክሎር ትምህርት ስንል ምን ማለታችን ነዉ በማለት በዚሁ ተቋም መምህር የሆኑትን አቶ ወንዶሰን አዳነን አነጋግረናል። ያድምጡ ! http://www.dw-world.de/dw/article/0,,6190673,00.html

የሲዳማ ባህላዊ ሐይማኖት (በኖሞናኖቶ)

ሲዳማ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል አንዱ ሲሆን፡ ቀድሞ የሲዳሞ ክፍለ አገር ይባል በነበረው እና በአሁኑ ጊዜ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት አካል በሆነው ሲዳማ ዞን ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ነው። ህዝቡ ከሲዳማ ዞን ውጪ በአጎራባቹ የኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች ውስጥ ይኖራል። የህዝብ ብዛቱም ከአራት ሚሊዮን በላይ እንደሆነ የተለያዩ ዶክመንቶች ያመለክታሉ። ሲዳማዎች የአፍሮ - እስያቲክ ግንድ ካላቸው እና በሰሜን አፍሪካ፣ በአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ እስያ ከሚነገሩ 375 ቋንቋዎች አንዱ የሆነ እና ከኩሽ ወይም ከኩሺቲክ የቋንቋ ቤተሰብ የሚመደብ ቋንቋ ይናገራሉ። ከቋንቋቸው ባሻገር እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔሮ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ሁሉ የራሳቸው የሆነ ባህል፣ እምነት፣ አስተዳደራዊ ስርዓት፣ መገበያያ ገንዘብ፣ የጊዜ እና ዘመን አቆጣጠር ስርዓት እና ሌሎች ማህበራዊ እሴቶች ያሉት ህዝብ ነው። ሲዳማዎች ለዘመናት ከአባት ወደ ልጅ እያወረሱ ካቆዩት እሴቶቻቸው መካከል ባህላዊ ሐይማኖት ይገኝበታል። በሐይማኖቱ መሰረት ሲዳማዎች በማጋኖ ( አምላክ ወይም እግዚአብሔር ) ያምናሉ። ማጋኖ ፣ ሐላሌ ( እውነት ) እና አካካ ( አባቶች፣ አያቶች፣ ቅድመ አያቶች ) የእምነታቸው መሶሶዎች ናቸው። በእነዚህ ሶስቱ መሶሶዎች ላይ እና በእምነቱ አጠቃላይ ጽንሰ ሐሳብ ላይ አንዳንድ ሀሳቦችን ከማንሳት በፊት ስለአካኮዎች ወይም አባቶች፣ አያቶች፣ ቅድመ አያቶች ወይም ስለሲዳማ ጎሳዎች ትንሽ ልበል። ሲዳማዎች ከመካከለኛው ምስራቅ ባህርን ተሻግረው ወደ አፍሪካ ቀንድ መምጣታቸውን፣ በመጀመሪያ '' ዳዋ '' 1 ከሚባል ቦታ ላይ መስፈራቸውን ቀጥሎም በባሌ አድርገው አሁን ወዳሉበት አከባቢ መምጣታቸውን የብሔሩ ሽማግሌዎች

The Sidama Nation: An Introduction Seyoum Hameso

The Sidama Nation: An Introduction Seyoum Hameso To appreciate a people’s explanation of life and misfortune, one needs to have a general picture of the wider framework of their existence (Brøgger 1986:21) Little is known about the Sidama nation, its people, its history and culture. Sidama studies were virtually non-existent even for academic purposes. Th ere are many reasons for this. First and foremost, the emergence of enlightened nationalists and the promotion of Sidama nationalism were late and slow in comparison to other regions. Secondly, the Ethiopian historiography had no room for the promotion or development of non-Habasha cultures and peoples. Worse, still, it had circumvented and undermined knowledge production and dissemination of the latter. Th e combination of these factors engendered ambiguity about the past and uncertainty about contemporary developments. Th e ensuing lack of critical scholarship, as William Shack noted, had “distorted the human achievements of conquer