Posts

Showing posts from September, 2012

Ethiopians in New York hold the first rally against Hailemariam Desalegn

Image
Tedla Asfaw The rainy cloudy Sept. 28, 2012 was not a welcome weather for anyone. It was raining hard from early morning and we followed the weather hour by hour fearing for a washout of our rally scheduled for 3pm at 47 Street and 2nd Avenue at UN. Rain started to tamper down at noon but still the cloud was threatening. Hailemariam Desalegn might have liked the rainy day to avoid any protest after he gave a very unwelcome interview to VOA’s Peter Heinlein yesterday which angered most of us.  Our protest rally was not organized to unwelcome or welcome Hailemariam. It was a Freedom rally which was dubbed as May 18 the Freedom rally which forced the late Meles Zenawi to bow his head in front of his foreign supporters at Regan Building in DC on May 18 this year. The slogan we prepared were calling for all political prisoners to be released and the backers of the Ethiopian regime to stop financing dictatorship that violated civil rights of its citizens. However, after the Sept

Any Decision on the status of Hawassa Administration and the Sidama Regional Question without Referendum will remain Illegal

By Hawassa Teessonke 28 September 2012 The ongoing meeting in Hawassa called by the EPRDF President of Southern region about which our various reporters have provided an excellent account is said to have continued as misguided as ever. Reports indicate that the meeting has discussed the following five agenda during the past three days: 1) How the development of Sidama can be sustained. 2) Why the people of Sidama do not accept the concept of EPRDF/SEPDM. The Oromo people are more numerous than the Sidama people but they are under the EPRDF/ OPDO rule. 3) As long as the Sidama people are forced to be under SEPDM rule, they would be forced to allow joint administration of the Hawassa town. The Sidama cadres should apologize for not letting that happen up till now. 4) The question of regional self-administration is not possible for now and for ever. 5) Anybody who is interested to fight for the freedom of the Sidama people can continue to fight but the members of the SEPD

የሕግ ፍትህ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምን ሠራ?

Image
ባለፈው ዕትማችን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2004 ዓ.ም ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ከኮሚቴው አባል የተከበሩ አቶ ዳዊት ተፈራ ጋር ባደረግነው ቃለ ምልልስ ማስነበባችን ይታወሳል፤ በዚህ እትማችን ደግሞ ቀሪውን ክፍል ይዘን ቀርበናል፡፡   ሕግ ከማውጣት አንፃር ቋሚ ኮሚቴው ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ አምስት ረቂቅ አዋጆችን ከሌሎች ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር በመተባበር ሰርቷል፡፡ረቂቅ ሕጎቹ የሕግ አወጣጥ ሥርዓትን በተከተለ ሁኔታ ተረቅቀው የውሳኔ ሃሳብ ሪፖርት ቀርቦባቸው በምክር ቤቱ እንዲፀድቁ ተደርጓል፡፡ ሌላው ቋሚ ኮሚቴው ብቻውን የሚመለከተው እና ኃላፊነቱን ወስዶ በማርቀቅ ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳብ በማቅረብ የፀደቀው 'የወሳኝ ኩነት እና ብሔራዊ መታወቂያዎች' የሚለው አዋጅ ነው፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረት የእያንዳንዱ ሰው ከልደት እስከ ሞት ያለው መረጃ ይመዘገባል፡፡ ለዚሁ ሥራ ከታች እስከ ላይ መዋቅር ያለው ጽ/ቤት ይቋቋማል፡፡ በአዋጁ መሰረትም እንደ ኢትዮጵያዊነት ለሁሉም ብሔራዊ መታወቂያ ይዘጋጃል፡፡መታወቂያው ሙሉ የማንነት መረጃን የያዘ ሲሆን ፤ለብሔራዊ ደህንነት እንዲሁም መንግሥት ሊዘረጋቸው ለሚፈልጋቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶች ጭምር አጋዥ ነው የሚሆነው፡፡  ምንም እንኳን በበቂ ሁኔታ ተሳትፎበታል ለማለት ባያስደፍርም በረቂቅ አዋጁ ላይ ሕዝቡ ተሳትፎ እንዲያደርግበት ኮሚቴው ጥረት አድርጓል የሚሉት አቶ ዳዊት ረቂቁን ለማዳበር ከሚመለከታ ቸው አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተፈጥሮ ጠቃሚ ግብአትም ከመገኘቱም በላይ ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው ተብሎ ለሚታሰቡ ወገኖችና ተቋማትም ረቂቁ ላይ የበኩላቸውን ሃሳቦች ሰንዝረዋል። ሌላው ቋሚ ኮሚቴው ከሚያከናውናቸው

መረጃ:- የግልጽነትና የተጠያቂነት ቁልፍ መሳሪያ

ከኢፌዲሪ ህገ- መንግስት አምስት መሰረታዊ መርሆዎች ውስጥ የመንግስት አሰራርና ተጠያቂነት አንዱ ነው፡፡ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ በመንግስት ሀላፊዎች የሚወሰዱ ውሳኔዎችና የስራ እቅስቃሴዎች ለህዝቡ ግልጽ መሆናቸውንና ህዝቡም ይህንን በተመለከተ ያሉትን መረጃዎች ለማግኘት ያለውን መብት የሚያረጋግጥ መርህ ነው፡፡ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ የዲሞክራሲ ዋልታ በመሆኑም ከመርሁ ተግባራዊነት ውጪ ዲሞክራሲን ማስፈን የማይታሰብ ነው፡፡ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት ትልቁን ድርሻ የሚይዘውን የህዝቦች ተሳትፎና የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥም ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግስት አሰራርን እውን ማድረግ የግድ ይላል፡፡ ዜጎች በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግና የመንግስት ሀላፊዎች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን ለመመርመር ተገቢውን መረጃ ሊያገኙ ይገባል፡፡ ግልጽነትም ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ሲሆን ለተጠያቂነትም እንደ ቅድመ ሁኔታ ይቀመጣል፡፡ በመሆኑም የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ የህዝቦችን ተሳትፎ ከማሳደጉም በላይ የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ዜጎች መረጃ የመጠየቅ፣ የማግኘትና የማስተላለፍ መብታቸው መከበሩ አንድም ተሳትፎአቸውን ለማሳደግ ሌላም የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህን በመተግበር የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተግባራዊነትን ለማረጋገጥ የሚኖረው ድርሻ የጎላ ነው፡፡፡ ዜጎች መረጃ ለማግኘት በራሳቸው ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተጨማሪም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በመፈለግና ለህዝቡ ተደራሽ በማድረግም የመገናኛ ብዙሀን ጉልህ ሚና አላቸው፡፡ የመገናኛ ብዙሀንና የመረጃ ነጻነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 የመደንገጉ ምክንያትም የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብትንና የመገ

በቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባና ሌሎች የከተማዋ አስተዳደር ሃላፊዎች ላይ ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላለፈ

Image
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2005  (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የቀድሞውን የሀዋሳ ከንቲባ ጨምሮ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ በነበሩ የከተማዋ አስተዳደር ሃላፊዎች በተከሰሱበት በእነ አቶ እንድርያስ ኦሌሳ መዝገብ የተለያዩ ትአዛዞችን አስተላለፈ፡፡  ከመሬት ጋር በተያያዘ ያልተገባ ጥቅም ለራሳቸውና ለቤተሰቦቿቸው ለማስገኘት በማሰብ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የተከሰሱት እነዚሁ የከተማዋ አስተዳደር የተለያዩ ሃላፊዎች የፍርድ ሂደት የሀዋሳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲመለከተው ቢቆይም በነጻ አሰናብቷቸው ነበር፡፡ የከልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩን ማየት ከጀመረ በኋላ ግን ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ያልቻሉትን 1ኛ ተከሳሽ እንድሪስ አሎሳና 2ኛ ተከሳሽ ጉደታ ጎምቢ በፖሊስ ተፈልገው ሊገኙ ስላልቻሉ ስማቸውና ምስላቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ እንዲፈለጉ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡ ፍርድ ቤቱ በዚሁ መዝገብ የተከሰሱ የሌሎች 4 ተከሳሾች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ትእዛዝ ማስተላለፉን ነብዩ ይርጋአለም ዘግቧል። http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=26121&K=

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በ579 ሚልዮን ብር ግንባታ አጠናቀቀ

Image
አዋሳ መስከረም 18/2005 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ በ579 ሚልዮን ብር የጀመረው የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማዘጋጀቱን ገለጸ፡፡ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን በ2 ቢልዮን 460 ሚልዮን ብር ወጪ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል፡፡ የዩኒቨርስቲው የቢዝነስና ዲቨሎፕመንት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ንጋቱ ረጋሳ ከትናንት በስቲያ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት በዩነቨርስቲው ሜዲካልና ይርጋዓለም ካምፓሶች እንዲሁም በዋናው ግቢና ግብርናና ጤና ሳይንስ ኮሌጆች ከአንድ አመት በፊት የተጀመሩት አዳዲስ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቀዋል፡፡ ከተጠናቀቀው ፕሮጀክቶች መካከል በተለምዶ ኋይት ሀውስ የሚባለው የተማሪዎች ማደሪያ ፣ የመማሪያ ክፍሎች ቤተ መፃህፍት፣የአስተዳደርና የመምህራን ቢሮዎች ጨምሮ ሌሎችም ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ መገልጋያዎች እንዳሏቸው ተናግረዋል፡፡ በሜዲካልና በይርጋለም ካምፓስ ብቻ በእያንዳንዳቸው 780 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስማር የሚያስችሉ መሆናቸውን አመልከተው የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው ተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተናገድ እየተዘጋጁ ናቸው ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሰቲው በ460 ሚልዮን ብር ወጪ ባለፈው ዓመት ግንባታው ያስጀመረው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አምስት ትላልቅ ዶርሚቴሪዎች በመያዝ እያንዳንዱ ዶርሚተሪ 780 ተማሪዎች ለማስተናገድ የሚያስችሉ ህንፃዎች ማካተቱን ተናግረዋል፡፡ በሁለት ሀገር በቀል ተቋራጮች የሚካሄደው የቴክኖሎጂ እንስቲትዩት 145 የመማሪያ ክፍሎች በተጨማሪ የአስተዳደር ቢሮዎች እና ሌሎችም ዲፓርትመንቶች ያካተተ ግዙፍ ህንፃ መሆኑን ከሁለት ዓመት በኋላ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ አስታውቀዋል፡፡ የቴክኖሎጂ እንስቲትዩቱ የሚ

ኮሚሽኑ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕጎችን በሦስት ቋንቋዎች በመተርጎም ያሳተመውን ሰነድ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስረከበ፤ በሲዳማ ኣፎ መቼ ነው መሰል ሰነዶች መቶርጎም የምጀምሩት?

Image
አዲስ አበባ መስከረም 15/2005 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አገሪቱ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕጎች፣ ስምምነቶችና መርሆዎችን በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በትግርኛ ቋንቋዎች በመተርጎም ያሳተመውን ሰነድ ዛሬ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስረከበ። ኮሚሽኑ በሁለት ሚሊዮን ብር ወጪ ያሳተማቸውን 35 ሺህ "የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች" ሰነድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች አስረክበዋል። በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዳራሽ በተካሄደው የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አምባሳደር ጥሩነህ ዜና እንደገለጹት አገሪቱ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕጎች፣ ስምምነቶችና መርሆዎች በሰብአዊ መብት ማስከበር ተግባር ላይ ሳይውሉ ቆይተዋል። እንዲሁም ወደ አገር ውስጥ ቋንቋዎች ለረጅም ጊዜያት ሳይተረጎሙ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል። ኮሚሽኑ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ህጎቹን ወደተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመው ዳኞች እና ዐቃቤ ሕጎች ከአገሪቱ ሕጎች ጋር አቀናጅተው እንዲጠቀሙባቸው ማሳተሙን አስረድተዋል። በአገሪቱ የሰብአዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ዳኞች እና ዐቃቤ ሕጎች "የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች" ሰነድ በሥራ ላይ በማዋል ሊጠቀሙበት እንደሚገባም ገልጸዋል። እንዲሁም ለፌዴራልና ለክልል ሕግ አውጪ አካላት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በሰብአዊ መብት ዙሪያ ለሚሰሩ መንግሥታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች "የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች" ሰነዱን ለማሰራጨት የሚያስችል ስትራቴጂ የተነደፈ መሆኑን

ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከደቡብ ክልል ፕሬዚዳንትነት የተነሱት በብቃት ማነስ ተገምግመው ኣይደለም፤ ኣምባሳደር ማርቆስ ተክሌ

Image
የኢትዮጵያ ኣምባሳደር በጃፓን፤ ኣውስትራልያ፤ በኒውዝይላንድ እና በፓፓ ኔው ጊኒያ ኣምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ሪቄ Markos Tekle Rike, Ethiopian Ambassador responsible for Japan, Australia, New Zealand and Papua New Guinea, talks about the leadership ability of newly elected PM Haile Mariam Desalegn and Ethiopia's future direction. The ruling party council of the Ethiopian Peoples' Revolutionary Front (EPRDF) elected last weekend the former Deputy Prime Minister and Foreign Minster Haile Mariam Desalegn as Chairman of the Front. Desalegn who assumed the position of Prime Minster of Ethiopia is to be endorsed by the parliament in the coming weeks.

ባለስልጣኑ የገበያ ደህንነት ክትትልን ለማስፋፋት የማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት አቋቋመ

Image
አዲስ አበባ መስከረም 14/2005 የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን የገበያ ደህንነት ክትትልን ለማስፋፋት በሶስት ከተሞች የማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ማቋቋሙን አስታወቀ፡፡ ባለሥልጣኑ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በግብይት ሥርዓቱ ምርመራና ክትትል ስልቶች ዙሪያ ለሁለት ሳምንት የሚቆይ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡ ባለሥልጣኑ የሰው ሃብት ሥራ አመራር ዳይሬክተር አቶ አበበ መስፍን ስልጠናው ዛሬ ሲጀመር እንደተናገሩት የፅህፈት ቤቶቹ መቋቋም ጤናማ ግብይትና የምርት ርክክብ መፈፀሙን ለመከታታልና ለማረጋገጥ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው፡፡  ፅህፈት ቤቶቹ የተቋቋሙት በአዋሳ፣ በጅማና በጎንደር ከተሞች ነው፡፡ ዳይሬክተሩ እንዳሉት ከተሞቹ የተመረጡበት ዋና ምክንያት በብዛት የሰሊጥና የቡና ምርት የሚገኝበት አገር በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ እንዲሁም የክትትል ሥራውን ይበልጥ ለማስፋፋትና የምርት ገበያ መረከቢያ መጋዘኖች በቅርበት በመሆን ክትትል ለማድረግ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ የህግ ጥሰት እንዳይፈፀም ለመከላከል ተፈፅሞ ሲገኝ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ አቅም ለመገንባት የሚያስችል ከፍተኛ የምርመራና የክትትል ክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና መሆኑንም አቶ አበበ ጠቁመዋል፡፡ ሥልጠናው የግብይት ሥርዓቱን ተአማኒነት ለማጎልበት ህብረተሰቡ ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት ላይ ያለው አመኔታና ተጠቃሚነት ይበልጥ እንዲረገጋጥ ለማድረግ የሚያስችል ተቋማዊ ጥንካሬ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  በግብይት ሂደት የሚያጋጥሙ ጥሰቶች ለመከላከል የተሻለ አቅም ይፈጠራል የሚል እምነት እንዳላቸውም አስታውቀዋል፡፡ ህብረተሰቡ የዘመናዊ ምርት ግብይት ሥርዓት ጠቀሜታ ተገንዝቦ ለግብይት ስርዓቱ መዳበርና ማደግ ይበልጥ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ተሳትፎው እንዲጎለብት መልዕክታቸውን ዳይሬ

Message to Newly Appointed Ethiopian Prime Minster

Image
From United Sidama Parties for Freedom and Justice (USPFJ), September 25, 2012 Ethiopia's newly-appointed Prime Minister Mr 'Hailemariam Desalegne' was sworn in on September 21ST 2012 in the Ethiopian capital Addis Ababa. Mixed opinions and reactions are pouring in from Ethiopians of all walks of life within the country and from the Diaspora. Numerous Ethiopians believe that, if the new PM takes the decision to be brave enough to think and act as a mature politician whose personal interest is put aside for the interest of the majority in the country, then there will be hope for all Ethiopians. He has before him the opportunity of establishing institutions that safeguard genuine democracy, freedom of expression and an independent system that accommodates and learns from divergent political opinions that will guarantee a respect for people's rights to hopes and opinions both individually and collectively, and which will guarantee that his name be well-remembered.

ቀይ መብራት --የሃይለማርያም ደሳለኝን እና የደመቀ መኮንን የተደበቀ ታሪክ

Image
አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ደቡብ ክልል በነበሩበት ጊዜ የራሳቸውን የብሔረሰብ አካላት ወደ ስልጣን የመሰብሰብ ስራ ሲሰሩ ከሲዳማ ማህበረሰብ በኩል ለምን እኛስ ? የሚል ጥያቄ መነሳቱን የቅርብ ምንጮች ይጠቁማሉ ፤ አቶ ኃ/ማርያም ለዚሀ የሰጡት መልስ “ከእናንተ የተማረ ማህበረሰብ ስለሌለ ነው ካቢኔውን በተማረ ማህበረሰብ ያዋቀርኩት” የሚል መልስ ነበር (አንድ አድርገን መስከረም 10 2005 ዓ/ም)፡-  አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ እና የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ አቶ ደመቀ መኮንን የትምህርት ሚኒስትር ፤ አቶ ሶፊያን አህመድ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ፤ እነዚህ  በስም የተዘረዘሩት ሶስት ከፍተኛ የሀገሪቱ ቱባ ባለስልጣናት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በህይወት በተለዩበት ወቅት የኢህአዴግ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ለውድድር ያቀረባቸው ሰዎች ናቸው ፡፡ ፓርቲው ባደረገው ምርጫ መሰረት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝን ሊቀመንበር ፤አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መሾሙ የሚታወቅ ነው ፤ በቂ ድምጽ ያላገኙት በወ/ሮ አዜብ መስፍን የተጠቆሙት አቶ ሶፍያን አህመድ በሶስተኝነት ወደ ኃላ ቀርተዋል ፤ ነገ 11/01/2005 ዓ.ም ፓርላማው ምርጫውን በ99.6 በመቶ ድምጽ ያጸድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል ፤  አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የOnly Jesus እምነት ተከታይ ናቸው ፤ ምክትላቸው አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ሶፍያ አህመድ ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታይ ናቸው ፤ በመሰረቱ ደመቀ መኮንን ብሎ የእስልምና እምነት ተከታይ ይኖራል ብለው ሰዎች ላያስቡ ይችላሉ ፤  አቶ ደመቀም ከወደ ወሎ መሆናቸው ሰዎች ይናገራሉ ፤ አሁን እኛን ያሳሰበን ነገር የኢህአዴግ የፓርቲ ምርጫ አይደለም ፤ የነዚህ ሰዎ

የፍጥጫው አካል የሆነው የመከላከያ ጄነራሎች ሹመት እንዴትና በማን ሹመቱ ተሰጠ? ጸደቀ?

የፍጥጫው አንዱ አካል የሆነው የመከላከያ ጄነራሎች ሹመት ይገኝበታል። በአንዳንድ ወገኖች የሚሰነዘር ተገቢ ጥያቄ አለ። «የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠ/ሚ/ር በሌለበት እንዴትና በማን ሹመቱ ተሰጠ? ጸደቀ?» የሚል ሲሆን፣ ለዚህ ደግሞ ከመንግስት አፈ ቀላጤዎች የሚስጠው ምላሽ ሹመቱ ቀደም ሲል በአቶ መለስ የጸደቀ እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህ ግን ውሀ የማይቕጥር ነው ሲሉ የመከላከያ ምንጮች ማስተባበያውን ያጣጥላሉ። ምክንያቱንም ሲያስረዱ ከተሾሙት ጄነራሎች መካከል በአንጃነት ተፈርጀው የቆዩ፣ በመለስ በጥሩ አይን የማይታዩና ለረጅም አመት ለእስር የተዳረጉ እንዳሉም                              ይገልጻሉ። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ መለስ እነዚህን  ይሾማሉ ብሎ ማሰብ ጨርሶ የማይታሰብ ነው ሲሉ ያክላሉ። እርከን ጠብቀው የተሾሙ  እንዳሉም ይጠቁማሉ። ቢሆንም ግን ህገ መንግስቱን ያልተከተለና ተገቢውን መንገድ  የልተከናወነ ሹመት እንደሆነ አልሽሽጉም። የብ/ጄኔራል ሹመት ከሰጣቸው አንዱ ኮ/ል አ ታክልቲ በርሄ  ይገኝበታል። ከዚህም ቀደም ባቀረብኩት መጣጥፌ «መለስ ካጠፋቸው የፓርቲው አባላት» ይኸው ኮ/ል እንደሚገኝበት ጠቅሼ ነበር። በተሰነይ ግንባር ከፍተኛ ጀግንነት የፈጸመው ኮ/ል አታክልቲ  ከጦርነቱ በሁዋላ መለስን ሀይለ-ቃል በመናገሩና በማውገዙ እስር ቤት ወርዶ ለረጅም አመት ድምጹ ጠፍቶ ቆይቶአል።በ 2000 አ.ም  ከእስር ተለቆ እንደቆየና በቅርቡ የብ/ጀነራልነት ሹመት አግኝቶ በተሻለ ሀላፊነት ላይ መቀመጡ ታውቆአል። ሌላዋ የሴት ጄነራል ተሿሚ አስካለ ብርሀኔ ትባ ላለች። ህወሀትን የተቀላቀለችው ከበርካታ ታዳጊ  እኩዮችዋ ጋር ሲሆን ጊዜው ደግሞ ግንቦት 1970 አ.ም ነበር። አብረዋት ጫካ ከገቡት ሴቶች ሁሉም ማለት ይቻላል

የኒዮሊበራሊዝም ቀውስና የአፍሪካ ተስፋ

አፍሪካ ምንም እንኳ ከሃምሳ ዓመታት በፊት ሙሉ ለሙሉ ከቅኝ ግዛት ብትላቀቅም መለያዋ ከሆነው ድህነት ነፃ መውጣት አልተቻላትም፡፡ «በአህጉሪቷ ድህነት ስር ሰዶ ሊነቀል በማይችል መልኩ ተተክሏል» የሚሉት በርካቶች ናቸው፡፡ ያደጉት አገሮችም አህጉሪቷ ከድህነት እንድትወጣ የሚያስችላትን አቅጣጫን ከማመላከት ይልቅ በየጊዜው ዕርዳታ እየሰጡ እጅ በመጠምዘዝ በፈለጉት መንገድ መምራቱን ነው የመረጡት። ያደጉት አፍሪካ አምርታ የምታገኘውን ውጤት ለዓለም ማቅረብ የማትችል እንደሆነች የበለፀጉት አገሮች ያስባሉ፡፡ አፍሪካውያን ለዘላለም ከድህነትና ከተረጂነት መላቀቅ እንደማይችሉ ይገምታሉ፡፡ እነርሱ ሊተገብሩት የሚፈልጉትን ነገር በአፍሪካ መሞከርም ምርጫቸው ነበር። አፍሪካ መሞከሪያ ከተደረገችበት ነገር ውስጥ አንዱ የኒዮሊበራሊዝም የኢኮኖሚ ርዕዮተ ዓለም አንደኛው ነው፡፡ በ1930ዎቹ መገባደጃ መወጠኑ የሚነገርለት ይህ ርዕዮተ ዓለም የሚያጠነጥነው ኢኮኖሚውና ገበያው ሙሉ ለሙሉ ከመንግሥት ውጪ ሆኖ ይንቀሳቀስ በሚለው መስመር ላይ ነው፡፡ በእዚህ አካሄድ ላለፉት ከሦስት ያላነሱ አስርት ዓመታት አፍካውያኑም ሆኑ ያደጉት ሀገራት ተግባራዊ ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡ ይህንን ርዕዮተ ዓለም ተግባራዊ ያደረጉ ሀገራት በተለይም የአፍሪካ ሀገራት ዕድገት ማምጣትም ሆነ ከድህነት መላቀቅ አልቻሉም፡፡ ያደጉት ሀገራትም ቢሆኑ ቀስ በቀስ ሊወጡት በማይችሉት የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቀዋል፡፡በተቃራኒው የኒዮሊበራ ሊዝምን ርዕዮተ ዓለም ከመቀበል የታቀቡ ሀገራት ደግሞ የራሳቸውን መንገድ ቀይሰው በመንቀሳቀሳቸው ከስህተታቸው እየተማሩ ፈጣን እድገት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡  የ21ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹ አስርት ዓመታት ኒዮሊብራሊዝምን በሚከተሉና በማይከተሉ ሀገራት መካከል ግልፅ ልዩነት የታ

ቅድስት ማርያም ኮሌጅ ለአስራ ሶስተኛ ጊዜ በተከታታይ ርቀት ትምህርት ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፤ እንኳን ደስ ኣላችሁ የሲዳማ ተመራቂዎች

Image
New አዲስ አበባ መስከረም12/2005 ቅድስተ ማርያም ኮሌጅ በዲግሪ ፣በዲፕሎማ እና በሰርተክፌት መርሀ ግብር ያስተማራቸውን 3 ሺ 325 ተከታታይ የርቀት ትምህርት ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ እና በሀዋሳ ከተሞች አስመረቀ። ምሩቃኑ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በቢዝነስ 1 ሺህ 498፣ በመምህራን ትምህርት ፕሮግራም 76፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ፕሮግራም በደረጃ 4 መርሀ ግብር 1ሺህ 430 በደረጃ አራት ደግሞ 319 ተማሪዎች ናቸው ። ኮሌጅ ለአስራ ሶስተኛ ጊዜ በተከታታይ ርቀት ትምህርት ያስተማራቸውን ተማሪዎች ባስመረቀበት ፕሮግራሙ ላይ የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር ወንደሰን ታምራት ባደረጉት ንግግር ምሩቃኑ የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር በመለወጥ ለሀገራቸው ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋፆኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ። በክብር እንግድነት የተገኙት ታዋቂው የግብርና ሳይንስ ተመራማሪ ዶክተር ስሜ ደበላ ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎቹ ስራ ጠባቂ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ በመሆን ራሳቸውንም ሌሎችንም ዜጎች መጥቀም እንደሚገባቸው ተናግረዋል ። በተለይ በቴክኔክና ሙያ ዘርፍ ተመራቂዎች በግብርና ዘርፍ ላይ ቴክኖሎጂዎችን በሰፋት በመጠቀም ኋላ ቀር የግብርና አሰራሮችን ለማስወገድ በሚደረገው ስራ ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርባቸዋል ሲሉ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል ።

ጉዳዩ፡-ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንድሰጠን ስለማሳሰብ ይሆናል::

ቀን፡-11/01/2005 ቁጥር፡-ድሩ ቄለ01/2005  ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞከራሲዊ ሪፓብልክ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት  አዲስ አበባ ጉዳዩ፡-ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንድሰጠን ስለማሳሰብ ይሆናል:: ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው በኢትዮጵያ ፌ/ዴ/ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 9 በንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ የበላይ ህግ ያጎናፀፋቸው መብቶች በሰላማዊ አሰራር የመንግስት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደማይኖራቸው ይደነግጋል፡፡ ይህ ህገ-መንግስት እንደገና በአንቀጽ 8 በንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉአላዊ ሥልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ይደነግጋል፡፡ ይሄ ሕገ-መንግሰት ከደነገገው ውጪ የደቡብ ብሔሮች በሔረሰቦችና ሕዝቦች ከልል የሚገኙ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ለሕዝብ መልካም አስተዳደርና ልማት ማረጋገጥ ካለመቻላቸውም በላይ በሕዝብና በመንግስት መካከል አመኔታ የሚሸረሽሩ ድርጊቶችን ፣ክራይ ሰብሳብነትንና ምግባረ-ብልሹነትን ለረጅም ጊዜያት ከመፈፀማቸው ጋር ተያይዘው ሕዝቡ አንቅሮ ስለተፋቸው ይህንን ለማስለወጥ የህዝቡን ብሶት የሚቀሰቅሱ አጀንዳዎችን አንስተው በሕዝቡ መካከል በመዛት ያንኑ መልሰው ለመሸንገል በሚል አጀንዳ የመንግስትን ታአማንነት ለማግኘት ስሉ የመንግስትን ውስን ሀብት ለማባከን ላይ ታች ሲሉና የሥልጣን ዕድሜ ሲያራዝሙ ቆይተዋል፡፡ በዚህም መነሻ ህገ-መንግስቱ ለሲዳማ ህዝብ ካጎናፀፈለት መብቶች አንዱ የሆነውን ባህሉን ለማሳደግ የፍቼ-ጫምባላላ በዓል ስያከብር እስከ ዛሬ ደርሷል፡፡በነቂስ የሚወጣው ህዝብም በዝህ በዓል እንደባህሉ የሚወደውን አወድሶ፣ያልተመቻቸውንና ህጋዊነቱን ያጎደለውን ነገር ወቅሶ በሰላም ወደቤቱ ይመለሳል፡፡በነሐሴ 8

ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና ሲዳማ

ፉቄ ዲሬሞ ከሃዋሳ የሲዳማ የራስ ገዝ የክልል ኣስተዳደርን በተመለከተ በህዝቡ ዘንድ የምነሱት ጥያቄዎች እድሜ ጠገብ ናቸው። ኣብዛኛዎች እንደምገምቱት በተለይ ከዛሬ ኣስር ኣመት ወዲህ የተጀመረና ከግዜ ወደ ጊዜ በህዝቡ ዘንድ እየሰረጸ የመጣ ጉዳይ ሳይሆን የሲዳማ ህዝብ ላለፉት ከሰላሳ ኣመታት በላይ ለነጻ ዲሞክራሲያዊ የራስ ኣስተዳደር ሲያደርግ የ ነበረው ትግል ኣካል ነው። የሲዳማ ህዝብ ከማንም የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ቀደሞ ለራስ ገዝ ኣስተዳደር እና ለመልካም ኣስተዳደር ብሎም ለዲሞክራሲያዊ ስርኣት መስፈን የታገለ ህዝብ ነው። ይህም ማለት የሲዳማ ህዝብ የ መልካም ኣስተዳደር እና የዲሞክራሲያዊ ስርኣት ግንባታ ኣስፈላግነትን በቅጡ የተ ረዳ ብሎም ሲታገልለት ቆየው ህዝብ ነ ው ፤ ለስኬቱም ብሆን ኣያሌ ውድ የሲዳማ ልጆች መስዋዕት ሆኖለታል እየሆኑም ይገኛል። የሲዳማ የምንም ጊዜ ውድ ልጆቿ የተሰውለት የመልካም ኣስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ የክልል ኣስተዳደር በተለይ ከሃያ ኣመታት በፊት በሲዳማ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላዋ ኢትዮጵያ የነበረው የደርግ ስርኣት ተገርስሰው ኣዲስ ስርኣት ሲቋቋም እውን ሆኖ ነበር ብሆንም ከጥቂት ጊዚያት በኃላ የራስ ክልል ኣስተዳደር መብቱን እንደገና መነጠቁ ይታወሳል። የሲዳማ ህዝብ ከመቶ ኣመታት በላይ ከሌሎች የኣገሪቱ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር ተፋቅሮ፤ ተቻችሎ በኣንድነት የኖረ ህዝብ ብሆንም ፖለቲካዊ የራስ ገዝ ክልላዊ ኣስተዳደሩን መነጠቁ እና ከሌሎች ኣናሳ ብሄሮች ጋር በስሜ ደቡብ በኣንድ ክልል ውስጥ መጠፈሩን ሳይቀበለው ኖሯል። በኢህኣዴግ የምመራው መንግስት የወሰደውን ይህንን እርምጃ በተመለከተ በወቅቱ ህዝቡ ተቃውሞውን በተለያዩ ኣጋጣሚዎች እና በተለያየ መልኩ የገለጸ ቢሆንም ሰሚ