POWr Social Media Icons

Thursday, May 3, 2012የፋሽን ኢንዱስትሪ እየተስፋፋ ከመጣበት ዘመን አንስቶ በርካታ የአለባበስ ልምዶችም አብረው ተፈጥረዋል። በተለይ በአውሮፓውያኑ አካባቢ አንድን ልብስ ከመምረጣቸው በፊት ለምን ጉዳይ እንደሚለብሱትና በምን ወቅት እንደሚያዘወትሩት ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአገራችን የሚዘጋጁ ባህላዊ አልባሳት ጊዜና ቦታ ተመርጦላቸው እንዲለብሱ እየሆነ ነው።

ብዙ ጊዜ የባህላዊ አልባሳት በበዓላት ቀን ላይ ብቻ እንዲለበሱ የተወሰኑ ነበሩ። አሁን አሁን ግን የባህላዊ አልባሳትን በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት በተለያዩ ወቅቶች በማንኛውም ቦታ እንዲለበሱ እየደተረገ ነው።
በሐዋሳ ከተማ የሚገኘው አበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ማምረቻና ማከፋፈያም ከአገራችን አልፎ እስከ ውጭ አገር ድረስ ባህላዊውን አልባሳት በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት ዕውቅናን እያተረፈ መጥቷል፡፡ 
ዋና ሥራ አስኪያጇ ወይዘሮ አበባ ዘነበር እንደ ገለጹልን፣ የባህላዊ አልባሳት በዘመናዊ መንገድ በመዘጋጀታቸው ፈላጊያቸው መብዛቱን ነው።
ለዛሬ ሊያስተዋውቁን የወደዱት በሲዳማ የባህል ጨርቅ የሚሠራውን ሸሚዝ ወይም የሱሪ አላባሽ ነው። ልብሱ የሚሠራው የሲዳማ ባህላዊ አልባሳት ከሚጠቀምባቸው ሦስት ቀለሞች አንዱ በሆነው በቀይ ቀለም ነው። የጨርቁ ምርት ሳባ ይባላል።
አሠራሩ ብዙዎች እንዲጠቀሙበት በማሰብ በአፍሪካውያን አለባበስ ዲዛይን ተደርጓል። ሰፋ ያለና ለሁሉም ሰው እንዲያመች ተደርጐ ተዘጋጅቷል። ሸሚዙን ወፍራምም ሆነ ቀጭን ሰው፤ ወንድም ሆነ ሴት በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሊለብሰው ይችላል።
«ወንዶች ከመረጡት ሱሪ ጋር ሴቶች ደግሞ በጂንስና በታይት ቢለብሱት የበለጠ ውበታቸውን ያጐላላቸዋል» የምትለው ዲዛይነር ወይዘሮ አበባ፣ በተለይ በሙቀት ወቅት ቢለበስ የበለጠ ምቾትን ይሰጣል ትላለች። 
ሸሚዙን ለማስዋብ ከወንዝ ውስጥ የሚወጣው ዛጐል ወይም በሲዳምኛ «ኤሌሌ» ትጠቀማለች። በተጨማሪም ጨሌዎችንም በማሳመሪያነት ትጠቅማባቸዋለች። ሸሚዙ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ የበለጠ ተወዳጅ ቢሆንም በአዲስ አበባና በውጭ አገር ሣይቀር ፈላጊው በመበራከቱ በብዛት እየተመረተ መሆኑንም ወይዘሮ አበባ ነግራናለች። አንዱ ሸሚዝ እስከ 350 ብር ለገበያ ይቀርባል።
http://www.ethpress.gov.et/ethpress/main/entertainment.php?entertainmentType=others&entertainmentId=330