Posts

የሻሼው ውሎ

በኦሮሚያ ክልል ስምንት ሰዎች ሞቱ Etiopia: nuove proteste in Oromia, almeno 8 morti e 30 feriti ረቡዕ ጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በተደረጉ የተቃውሞ ሠልፎች የስምንት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ታወቀ፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት በአምቦ፣ በዶዶላና ሻሸመኔ በተቀሰቀሰው ግጭት የሰው ሕይወት ጠፍቷል፡፡ ሻሸመኔ ከተማ በነበረው የተቃውሞ ሠልፍ የአምስት ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ፣ በሦስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ቦኬ ወረዳ በነበረው ተቃውሞም ለሦስት ሰዎች ሕይወት መጥፋትና ለሦስት ሰዎች አካል ጉዳት መንስዔ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች ከ30 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል፡፡ ተቀውሞው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋና ባለበት እንዲቆም የክልሉ መንግሥት ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ በዚህ መሠረት የክልሉ ወጣቶችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል፡፡ የፀጥታ አካላትም በወጣቱ ላይ አላስፈላጊ ዕርምጃ እንዳይወስዱ መልዕክት ማስተላለፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዓቢይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም የቆሙ በማስመሰል ወጣቱን በማነሳሳት ሰላማዊ ሠልፍ የሚጠሩ አፍራሽ ኃይሎች እንዳሉ ገልጸው፣ እነዚህ ኃይሎች ግን የኦሮሞን ሕዝብ ስለማይወክሉ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰባቸው ተገልጿል፡፡ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በአሁኑ ጊዜ በጀመረው ሥራ ሕዝብ እየደገፈው መሆኑን ገልጸው፣ የሕዝብን ጥቅም ከማይፈልጉ ኃይሎች ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረገ መሆኑን ማስታወቃቸው ተሰምቷል፡፡ በአምቦ ከተማ የነበረው ግጭት ዋነኛ መነሻ የአምቦ ውኃ ፋብሪካ ተነቅሎ ወደ ትግራይ ክልል ሊሄድ

የአፈ ጉባዔው ስንብት

Image
አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ በኢትዮጵያ ባልተለመደ ሁኔታ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ይፋ ከተደረገ በኋላ በርካታ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የውጭ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችና ሌሎችም የስንብት ሰላምታ ሰኞ መስከረም 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በፓርላማ ሲያቀርቡላቸው ተስተውሏል፡፡ አፈ ጉባዔ አባዱላ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ቅዳሜ መስከረም 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ሪፖርተር በድረ ገጹ መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፣ በማግሥቱ እሑድ መስከረም 28 ቀን 2010 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ግን ራሳቸው አፈ ጉባዔው ለአገር ውስጥ ሚዲያዎች ይፋ አድርገዋል፡፡ ‹‹አሁን በደረስኩበት ደረጃ በዚህ ኃላፊነት ለመቀጠል የማያስችሉኝ ሁኔታዎች ስላሉና ፍላጎቱም ስለሌለኝ ለመልቀቅ ድርጅቴንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቄያለሁ፤›› ሲሉ አፈ ጉባዔው ተናግረዋል፡፡ በማግሥቱ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመናቸውን በጋራ ስብሰባ በጀመሩበት ወቅት፣ አፈ ጉባዔ አባዱላ ስብሰባውን በማስጀመር ሲመሩ ነበር፡፡ የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳን ከመድረክ በስተጀርባ የሚሰናበቱ የምክር ቤቱ አባላት፣ ለረጅም ዓመታት ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ ሲያመሠግኗቸው ተሰምቷል፡፡ የአገሪቱ የሃይማኖት አባቶች፣ የውጭ ዲፕሎማቶች፣ እንዲሁም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ማለትም የብአዴን አመራሮችና የክልል ፕሬዚዳንቶች ሲሰናበቷቸው ተስተውሏል፡፡ አፈ ጉባኤው ለመልቀቅ ምክንያት የሆናቸውን ወደፊት እንደሚገልጹ ቢያስታውቁም፣ የተለያዩ መላምቶች እየተወሱ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል የተከሰተው ግጭት ሊሆን ይችላል የሚሉ አሉ፡፡ በሌላ በኩል በቴሌቪዥን

የሃዋሳን ከተማ የመንገድ ላይ ፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የተፈታተነው የሰሞኑ ዝናብ

Image
ከትናንትና ወዲያ ላይ በሃዋሳ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በተለይ በከተማዋ መናህርያ ሰፈር ኣከባቢ ያስከተለው የጎርፍ መጥለጥለቅ የኣከባቢውን የትራፊክ ፍልሰት ለሰዓታት ኣስቸጋሪ ኣድርጎ ነበር። ክስተቱ ለመሰል የጎርፍ ኣደጋዎች ከተማይቱ ምን ያህል ዝግጁ እንደሆነች እንድታስብ ያደረግ ነው። ሁሉም ፎቶዎች ከ ፍሰሃ ቦንጃ ፌስቡክ ገጽ ላይ የተወሰዱ ናቸው

የኢትዮጵያ ካርታ ስራ ኤጀንሲ የሰራውን የሲዳማዋ በንሳን ጨምሮ የአስር ከተሞችን ካርታ አስረከበ

Image
ሀዋሳ መስከረም 29/2010 የኢትየዮጵያ ካርታ ስራ ኤጀንሲ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ክልል ለሚገኙ 10 መካከለኛ ከተሞች ካርታ ሰርቶ አስረከበ፡፡ ኤጀንሲው ካርታውን ያስረከበው ትናንት በሀዋሳ ከተማ ለክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ነው፡፡ ርክክቡ የተካሄደው ለአስሩ ከተሞች  የቅየሳ፣ የጥራት ቁጥጥር፣ የመስመርና ሌሎች ጉዳዮችን ማሳያ በማካተት ካርታ ለመስራት መጋቢት 2008 ዓ.ም ከክልሉ ጋር በተፈጸመው ውል መሰረት መሆኑን በኤጀንሲው የፕላንና ፕሮጀክት ዝግጅትና ግምገማ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ ዋቅቶላ ገልጸዋል፡፡ የካርታው ስራ 179 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሸፈነ ሲሆን ከ14 ሚሊየን በላይ ብር ወጪ ተደርጎበታል ዳይሬክተሩ እንዳመለከቱት፡፡  የክልሉ ከተማና ቤቶች ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይልማ ሱንታ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት ካርታው ለከተሞች   እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ካርታው የተሰራላቸው ከተሞች አለታ ወንዶ፣ ሺንሺቾ፣ ዱራሜ፣ አረካ፣ ለኩ፣ ዳዬ በንሳ፣ ሀደሮ፣ ሳውላ፣ ተርጫና ይርጋጨፌ ናቸው ፡፡ ምንጭ፦ ኢዜኣ

በደቡብ ክልል የእንሰት አጠውልግ በሽታን የመከላከል ሥራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቆመ

ዲላ መስከረም 26/2010 በደቡብ ክልል የእንሰት አጠውልግ በሽታን ትኩረት ሰጥቶ መከላከል ካልተቻለ ሰብሉ ከምርት ውጭ የሚሆንበት ደረጃ ሊከሰት እንደሚችል የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አሳሳበ። ኢንስቲትዩት በተቀናጀ የእንሰት አጠውልግ በሽታ ቁጥጥርና መከላከያ ዘዴዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ትላንት በዲላ ከተማ አካሂዷል፡፡ በኢኒስቲትዩቱ የሰብል ምርምር ዳይሬክተር ዶክተር አግደው በቀለ እንደገለፁት፣ በክልሉ ከደቡብ ኦሞ፣ ቤንች ማጂና ሰገን ሕዝቦች ዞኖች ከሚገኙ የተወሰኑ አካባቢዎች በስተቀር ሁሉም ዞኖች እንሰት አብቃዮች ናቸው ፡፡ ሰብሉ በሚበቅልበት ሁሉም አካባቢዎች የእንሰት አጠውልግ በሽታ ወቅት ጠብቆ እየተቀሰቀሰ በሰብሉ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንን ተናግረዋል። በእዚህም በሽታው ከማሳ ወደ ማሳ እየተስፋፋ መምጣቱንና ክስተቱ በስፋት በሚታይባቸው አካባቢዎች ሰብሉ ሙሉ ለሙሉ ከምርት ውጭ የሆኑባቸው ማሳዎች እየተፈጠሩ መምጣታቸውን ጠቁመዋል ። ይህም የእንሰት ተክል ቀስ በቀስ ከምርት ሂደት እየወጣና የአርሶአደሩም ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ እንዲመጣ ማድረጉን  አስረድተዋል፡፡ ዶክተር አግደው እንዳሉት፣ በበሽታው መንሰኤና መከላከያ ዜዴዎች ላይ ሕብረተሰቡ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ ከመሆኑ ባለፈ ተክሉ ምርታማ እንዲሆን እንደ ሌሎች ሰብሎች ብዙ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት አይደለም። በሽታውን በመከላከል አርሶአደሩ ከእንሰት ማግኘት ያለበትን ጥቅም ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት ከሌሎች ሰብሎች እኩል ለእንሰት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። "ለእዚህም በየደረጃው የሚገኝ አመራርን ጨምሮ ባለድርሻ አካላትና አርሶአደሩን በማንቀሳቀስ የተቀናጀ የመከላከል ሥራ ሊሰራ ይገባል" ብለዋል ። በመድ