የትራፊክ ሥርዓት የማታውቀው ከተማ _ ዳዬ
ምንጭ የትራፊክ ሥርዓት የማታውቀው ከተማ ጠመዝማዛውን መንገድ ጨርሰው የዳዬ ከተማ መግቢያ ላይ ብቅ ሲሉ በርካታ የሞተር ሳይክሎች ይመለከታሉ፡፡ አልፎ አልፎም ባለ ሦስት እግር ባጃጆች ይታያሉ፡፡ ሞተር ሳይክሎቹ ግን ለከተማው ነዋሪዎች ብቸኛ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ መንገዱ ላይ የተኮለኮሉት ሞተረኞች ደንበኛ የተገኘ ሲመስላቸው ተሳፋሪውን ለመውሰድ ይሻማሉ፡፡ ቀልጣፋው የመጣውን ደንበኛ እንደወሰደ ሁሉም ወደ ነበሩበት ይመለሳሉ፡፡ ተራ ጠብቆ መሥራት የሚባል ነገር ያለ አይመስልም፡፡ ይህ ብቻም አይደል በአንድ ሞተር ላይም እስከ ስድስት ተሳፋሪዎችን መጫን የተለመደ ነው፡፡ ጫት፣ ጣውላ፣ ቆርቆሮና ሌሎች ነገሮችም የሚያስጭን ደንበኛ ከተገኘም ዓይናቸውን አያሹም ሞተረኞቹ፡፡ ካሉት የሞተር ሳይክሎች ብዛት አንፃር የከተማው አስፋልት በጣም ጠባብ የሚባል ዓይነት ነው፡፡ ከአቅማቸው በላይ ሰውና የተለያዩ ጭነቶችን የደራረቡ ስምንት የሚሆኑ ሞተሮች በጠባቡ የከተማው አስፋልት ላይ ወዲያና ወዲህ ይከንፋሉ፡፡ አልፎ አልፎ ብቅ ከሚሉት ውጪ ሁሉም የሰሌዳ ቁጥር የላቸውም፡፡ በቁጥሩ ፋንታ ‹ፍቅር›፣ ‹ሁሉ በእርሱ ሆነ› የሚሉ የተለያዩ ጥቅሶች በየሞተሮቹ ጀርባ ላይ ሰፍሯል፡፡ እንዲህ ያሉ ሕገ ወጦችን ለመቆጣጠር የተሠማሩ ትራፊክ ፖሊሶች ሚያሽከረክሩት ተመሳሳይ ሰሌዳ አልባ ሞተሮችን መሆኑ ደግሞ ምንድነው ነገሩ? ያሰኛል፡፡ አካባቢው እንደ ቡና ያሉ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገኙ ምርቶች መገኛ በመሆኑ ነዋሪዎቹ ብዙም የገንዘብ ችግር የለባቸውም ሊባል ይችላል፡፡ ከማሳቸው ያለ ቡና ሲደርስ አንድ ሞተር ለመግዛት የሚሆናቸውን ያህል ገንዘብ አያጡም፡፡ ከኬንያ ወደ ከተማው የሚገቡ የኮንትሮባንድ ሞተሮች ደግሞ