‹‹ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ያልሆነው ማስረጃ ስለሌለ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ
ለመሆኑ የዛሬ 15 ኣመት ከሲዳማ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ የጥይት እሩምታ ምላሽ በመስጠት ለበርካታ ንጽሃን ሲዳማዎች እልቂት ምክንያት የሆኑት የዛሬዎቹ ከፍተኛ ኣመራሮች የማይጠየቁት መረጃ ጠፊቶ ነውን? የኣገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰሞኑን በኣጠቃላይ ወቅታዊ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ከጋዜጠኞች ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ የገዥውን ፓርቲ ከፍተኛ ኣመራሮችን በተመለከተ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል የከፍተኛ ኣመራር ተጠያቂነትን የተመለከቱ ሲሆን፣ '' ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ያልሆነው ማስረጃ ስለሌለ ነው''ብለዋል። ለመሆኑ የዛሬ 15 ኣመት ከሲዳማ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ የጥይት እሩምታ ምላሽ በመስጠት ከበርካታ ንጽሃን ሲዳማዎች እልቂት ምክንያት የሆኑት የዛሬዎቹ ከፍተኛ ኣመራሮች የማይጠየቱት መረጃ ጠፊቶ ነው?ለማንኛውም ዝርዝር ወሬው ከታች ያንቡ፦ ፎቶ ከሪፖሪተር ጋዜጣ ‹‹ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ያልሆነው ማስረጃ ስለሌለ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ - ማስረጃ ከተገኘ የትኛውንም አመራር አንተውም ብለዋል - የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት የሚያጣድፍ ነገር አለመኖሩን ጠቁመዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መደበኛውን ጋዜጣዊ መግለጫ ከሰጡ ሁለት ዓመት ገደማ ሆኖታል፡፡ ባለፈው ሰኞ ጥር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. የግሉን ፕሬስ ጨምሮ ለውጭ ጋዜጠኞች በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኙ ጋዜጠኞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡ ዋና ዋና ከሚባሉት መካከል የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ሥልጣንን ለግል ጥቅም ማዋልና አለመጠየቅ፣ በአጥፊዎች ላይም ዕርምጃ