Posts

የበቆሎ ሾርባ ኣሰራሪን በተመለከተ በሲዳማ ኣፎ የቀረበ ቪድዮ

Image
የበቆሎ ሾርባ ኣሰራርን በሲዳማ ኣፎ በቪዲዮ ያቀረበው CIMMYT መቀመጫውን በመክስኮ ሲቲ በማድረግ፤ በዘመነ ግብርና ድህነትን እና ረሃብን በታዳጊ ኣገራት መከላከል ኣላማ ኣድርጎ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በኣለም ላይ በብዛት በምግብነት ከሚቀርቡ የሰብል ኣይነቶች መካከል ስንዴ እና በቆሎን በኣግባቡ ማምረት እና  ለመመገብ የሚያስችል ምክር በተለያዩ ዘዴዎች ይሰጣል። 

በደቡብ ክልል በዳዬ ከተማ በ650 ሚሊዮን ብር የዩኒቨርሲቲ ግንባታ ተጀመረ

Image
በደቡብ ክልል በዳዬ ከተማ በ650 ሚሊዮን ብር የዩኒቨርሲቲ ግንባታ ተጀመረ በደቡብ ክልላዊ መንግሥት ከሐዋሳ ከተማ በ125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዳዬ ከተማ በ200 ሔክታር ቦታ ላይ፣ በ650 ሚሊዮን ብር ወጪ የዩኒቨርሲቲ ግንባታ ሐምሌ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ተጀመረ፡፡ ዩኒቨርሲቲውን ኃላፊነት ወስዶ የሚያስገነባው የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ መሆኑንና አዲስ የሚገነባው ዩኒቨርሲቲ ስያሜ ‹‹ዳዬ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ›› እንደሚባል፣ ግንባታውን ያስጀመሩት የዳዬ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ ገልጸዋል፡፡ ከዓመት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ማለትም አካባቢውን ማፅዳትና ለነዋሪ አርሶ አደሮች ካሳ በመክፈልና ምትክ ቦታ በመስጠት ቢዘገይም በዚህ ወቅት መጀመሩ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡ በ200 ሔክታር ቦታ ላይ የሚነሱት 488 አርሶ አደሮች ሲሆኑ፣ ለ114 ተነሺዎች ሙሉ በሙሉ የካሳ ክፍያ መፈጸሙንና ለቀሪዎቹ በመክፈል ጎን ለጎን የግንባታ ሥራ እንደሚከናወንም ተናግረዋል፡፡ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በተጨማሪ፣ ለከተማዋ ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከልማቱ ጎን እንዲቆምም ከንቲባው አሳስበዋል፡፡ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ650 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት በመፈራረም ወደ ተግባር ግንባታ የገባው ከተክለብርሃን አምባዬ ኮርፖሬት ግሩፕ ጋር ነው፡፡ ግንባታውን በኃላፊነት ከሚያስፈጽመው ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዮሴፍ ማሞ ጋር በመሆን ያስጀመሩት፣ የኮርፖሬት ግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፉ አምባዬ ናቸው፡፡ በተጠናቀቀው ዓመት የይርጋለም ካምፓስን አጠናቀው ማስረከባቸውን የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው፣ የጀመሩት የዳዬ ዩኒቨርሲቲንም ለ2010 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ለማድረስ ጠንክረው እ

ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል ለሆነው የዝዋይ - አርሲ ነገሌ መንገድ ግንባታ ኮንትራክተሮች እንዲወዳደሩ ጨረታ አወጣ

Image
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል ለሆነው የዝዋይ - አርሲ ነገሌ መንገድ ግንባታ ኮንትራክተሮች እንዲወዳደሩ ጨረታ አወጣ፡፡ ባለሥልጣኑ ጨረታውን ያወጣው ሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ሲሆን፣ በፕሮጀክቱ ላይ ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች እ.ኤ.አ. እስከ ኦክቶበር 25 ቀን 2016 ድረስ ለፕሮጀክቱ ግንባታ የሚያቀርቡትን የገንዘብ ፍላጎት ሰነድ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለመወዳደር የሚፈልጉ ኩባንያዎች የገንዘብ ፍላጎት ሰነዳቸውን በሚያስገቡበት ጊዜ፣ 500 ሺሕ ዶላር የጨረታ ማስረከቢያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 202 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የሞጆ - ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል ሲሆን፣ ከዝዋይ (ባቱ) አርሲ ነገሌ ያለው መንገድ ርዝመት 57.1 ኪሎ ሜትር እንደሆነ ፕሮጀክቱን በገንዘብ ከሚደግፈው የዓለም ባንክ ድረ ገጽ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ ከሞጆ - ሐዋሳ የሚዘረጋው የፍጥነት መንገድ ከሐዋሳ - ሞያሌ በመቀጠልም ከሞያሌ - ናይሮቢ ሞምባሳ ወደብ የሚዘልቅና ኢትዮጵያን በኬንያ በኩል ከወደብ የሚያገናኝ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የዚህ ፕሮጀክት የመጀመርያ ምዕራፍ ከሞጆ - መቂ የሚገነባው 56.8 ኪሎ ሜትር መንገድ ሲሆን፣ የቻይናው ቻይና ሬልዌይ ሰቭንዝ ግሩፕ ውል ተፈራርሟል፡፡ ኩባንያው ፕሮጀክቱን በ3.66 ቢሊዮን ብር እንደሚገነባና በ42 ወራት እንደሚያስረክብ ይጠበቃል፡፡ ሁለተኛው ምዕራፍ ከመቂ - ባቱ የሚገነባው 37 ኪሎ ሜትር መንገድ ሲሆን፣ የኮሪያ መንግሥት ባቀረበው 82 ሚሊዮን ዶላር ብድር የሚገነባ ነው፡፡ ለግንባታውም የተመረጠው ዳዎ ኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ኩባንያ ነው፡፡ የሦስተኛው ምዕራፍ ከባቱ - አርሲ ነገሌ ለሚገነባውና በአሁኑ ወቅት ጨረታው ለወጣው መንገድ ግንባታ የዓለም ባንክ 370 ሚሊዮን ዶላር

Hawassa International Stadium to host Ethiopia’s last AFCON Qualifier

Image
Residents of  Hawassa City  have a reason to smile as they will host  Ethiopia’s Walia Ibex  last  AFCON 2017  qualifier against  Seychelles  in September. The match initially scheduled for the Capital’s  Addis Ababa Stadium , will now be staged at the  Hawassa International Stadium. The newly built stadium was given a clean bill of health by  CAF  inspectors who toured the facility a month a go paving way for it’s first international event. Hawassa hosted eight group A and B matches of the  2015 CECAFA Senior Challenge Cup  that saw the 60,000 capacity masterpiece fill to the rafters. It adds to three the number of approved stadiums in the country after Addis and  Bahir Dar Stadiums . Bahir Dar hosted Walia’s 2-1 win over Lesotho in March; a tie watched by a record 100,000 plus fans. The Group “J” action headed to Addis Stadium for Algeria fixture in the same month that ended in a 3-3 draw. Addis Stadium playing surface has lately become unplayable due to heavy rains, an

ሲዳማን ጨምሮ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች በመጪዎቹ አስር ቀናት ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችል ተጠቆመ

Image
በመጭዎቹ አስርት ቀናት በአንዳንድ የአገርቱ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችል የብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ። ዝናቡ በገደላማ ቦታዎች ላይ የመሬት መንሸራተትና ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግም አሳስቧል። አርሶ አደሮች ውሃ ማሳ ላይ እንዳይተኛ ቦይ ከማውጣትና ከማንጠፈፍ በተጨማሪ የተዘራና ለዘር የተዘጋጀ ማሳ በጎርፍ እንዳይሸረሸር የጎርፍ መከላከል ስራ መስራት እንደሚገባ ኤጀንሲው ገልጿል። ፎቶ ከ ኮሊኢሜጂስ በተለያዩ የአገርቱ ክፍሎች ዝናቡ ቀጣይነት ስለሚኖረው የመኸር አብቃይ አካባቢዎች የመካከለኛ ጊዜ ሰብሎችን ለመዝራት፣በቡቃያ ደረጃ ለሚገኙና የቋሚ ሰብሎችን የውሃ ፍላጎት ለመሟላት አመቺ  ነው ተብሏል። በአፋርና ሰሜን ሶማሌ ለሚገኙ አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች ለመጠጥ ውሃና ለግጦሽ ሳር አቅርቦት የጎላ ጠቀሜታ እንዳለውና አርሶ አደሮች  ግብአቶችን በወቅቱ በመጠቀም  ሰብሎችን በፍጥነት መዝራት ይኖርባቸዋልም ብሏል። እንደ ኤጀንሲው መረጃ ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅና ምዕራብ ወለጋ ፣ጅማ ፣ኢሉ አባቦራ፣ምዕራብና ሰሜን ሸዋ ፣አዲስ አበባ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ  ያገኛሉ። የጋምቤላ ክልል ዞን 1፣2 እና 4 እንዲሁም ከአማራ ክልል ምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም፣ሰሜን ሸዋ ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ባህርዳር ዙሪያ ፣አገው ፣አዊ፣ የሰሜንና የደቡብ ጎንደር ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ  በላይ ዝናብ የሚያገኙ ናቸው። ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ ሁሉም የትግራይ ዞኖች ፣የአፋር ክልል ዞን 3፣4 እና 5 እንዲሁም ከደቡብ ክልል የሃዲያና ጉራጌ ዞኖች ፣የወላይታና የሲዳማ ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ የሚያገኙ ስፍራዎች መሆናቸው ተገልጿል። ምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ ፣የአርሲና ባሌ ዞኖች ፣ከፋና ቤንች ማጂ ፣ከሶ