Posts

ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል ለሆነው የዝዋይ - አርሲ ነገሌ መንገድ ግንባታ ኮንትራክተሮች እንዲወዳደሩ ጨረታ አወጣ

Image
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል ለሆነው የዝዋይ - አርሲ ነገሌ መንገድ ግንባታ ኮንትራክተሮች እንዲወዳደሩ ጨረታ አወጣ፡፡ ባለሥልጣኑ ጨረታውን ያወጣው ሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ሲሆን፣ በፕሮጀክቱ ላይ ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች እ.ኤ.አ. እስከ ኦክቶበር 25 ቀን 2016 ድረስ ለፕሮጀክቱ ግንባታ የሚያቀርቡትን የገንዘብ ፍላጎት ሰነድ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለመወዳደር የሚፈልጉ ኩባንያዎች የገንዘብ ፍላጎት ሰነዳቸውን በሚያስገቡበት ጊዜ፣ 500 ሺሕ ዶላር የጨረታ ማስረከቢያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 202 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የሞጆ - ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል ሲሆን፣ ከዝዋይ (ባቱ) አርሲ ነገሌ ያለው መንገድ ርዝመት 57.1 ኪሎ ሜትር እንደሆነ ፕሮጀክቱን በገንዘብ ከሚደግፈው የዓለም ባንክ ድረ ገጽ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ ከሞጆ - ሐዋሳ የሚዘረጋው የፍጥነት መንገድ ከሐዋሳ - ሞያሌ በመቀጠልም ከሞያሌ - ናይሮቢ ሞምባሳ ወደብ የሚዘልቅና ኢትዮጵያን በኬንያ በኩል ከወደብ የሚያገናኝ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የዚህ ፕሮጀክት የመጀመርያ ምዕራፍ ከሞጆ - መቂ የሚገነባው 56.8 ኪሎ ሜትር መንገድ ሲሆን፣ የቻይናው ቻይና ሬልዌይ ሰቭንዝ ግሩፕ ውል ተፈራርሟል፡፡ ኩባንያው ፕሮጀክቱን በ3.66 ቢሊዮን ብር እንደሚገነባና በ42 ወራት እንደሚያስረክብ ይጠበቃል፡፡ ሁለተኛው ምዕራፍ ከመቂ - ባቱ የሚገነባው 37 ኪሎ ሜትር መንገድ ሲሆን፣ የኮሪያ መንግሥት ባቀረበው 82 ሚሊዮን ዶላር ብድር የሚገነባ ነው፡፡ ለግንባታውም የተመረጠው ዳዎ ኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ኩባንያ ነው፡፡ የሦስተኛው ምዕራፍ ከባቱ - አርሲ ነገሌ ለሚገነባውና በአሁኑ ወቅት ጨረታው ለወጣው መንገድ ግንባታ የዓለም ባንክ 370 ሚሊዮን ዶላር

Hawassa International Stadium to host Ethiopia’s last AFCON Qualifier

Image
Residents of  Hawassa City  have a reason to smile as they will host  Ethiopia’s Walia Ibex  last  AFCON 2017  qualifier against  Seychelles  in September. The match initially scheduled for the Capital’s  Addis Ababa Stadium , will now be staged at the  Hawassa International Stadium. The newly built stadium was given a clean bill of health by  CAF  inspectors who toured the facility a month a go paving way for it’s first international event. Hawassa hosted eight group A and B matches of the  2015 CECAFA Senior Challenge Cup  that saw the 60,000 capacity masterpiece fill to the rafters. It adds to three the number of approved stadiums in the country after Addis and  Bahir Dar Stadiums . Bahir Dar hosted Walia’s 2-1 win over Lesotho in March; a tie watched by a record 100,000 plus fans. The Group “J” action headed to Addis Stadium for Algeria fixture in the same month that ended in a 3-3 draw. Addis Stadium playing surface has lately become unplayable due to heavy rains, an

ሲዳማን ጨምሮ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች በመጪዎቹ አስር ቀናት ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችል ተጠቆመ

Image
በመጭዎቹ አስርት ቀናት በአንዳንድ የአገርቱ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችል የብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ። ዝናቡ በገደላማ ቦታዎች ላይ የመሬት መንሸራተትና ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግም አሳስቧል። አርሶ አደሮች ውሃ ማሳ ላይ እንዳይተኛ ቦይ ከማውጣትና ከማንጠፈፍ በተጨማሪ የተዘራና ለዘር የተዘጋጀ ማሳ በጎርፍ እንዳይሸረሸር የጎርፍ መከላከል ስራ መስራት እንደሚገባ ኤጀንሲው ገልጿል። ፎቶ ከ ኮሊኢሜጂስ በተለያዩ የአገርቱ ክፍሎች ዝናቡ ቀጣይነት ስለሚኖረው የመኸር አብቃይ አካባቢዎች የመካከለኛ ጊዜ ሰብሎችን ለመዝራት፣በቡቃያ ደረጃ ለሚገኙና የቋሚ ሰብሎችን የውሃ ፍላጎት ለመሟላት አመቺ  ነው ተብሏል። በአፋርና ሰሜን ሶማሌ ለሚገኙ አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች ለመጠጥ ውሃና ለግጦሽ ሳር አቅርቦት የጎላ ጠቀሜታ እንዳለውና አርሶ አደሮች  ግብአቶችን በወቅቱ በመጠቀም  ሰብሎችን በፍጥነት መዝራት ይኖርባቸዋልም ብሏል። እንደ ኤጀንሲው መረጃ ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅና ምዕራብ ወለጋ ፣ጅማ ፣ኢሉ አባቦራ፣ምዕራብና ሰሜን ሸዋ ፣አዲስ አበባ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ  ያገኛሉ። የጋምቤላ ክልል ዞን 1፣2 እና 4 እንዲሁም ከአማራ ክልል ምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም፣ሰሜን ሸዋ ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ባህርዳር ዙሪያ ፣አገው ፣አዊ፣ የሰሜንና የደቡብ ጎንደር ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ  በላይ ዝናብ የሚያገኙ ናቸው። ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ ሁሉም የትግራይ ዞኖች ፣የአፋር ክልል ዞን 3፣4 እና 5 እንዲሁም ከደቡብ ክልል የሃዲያና ጉራጌ ዞኖች ፣የወላይታና የሲዳማ ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ የሚያገኙ ስፍራዎች መሆናቸው ተገልጿል። ምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ ፣የአርሲና ባሌ ዞኖች ፣ከፋና ቤንች ማጂ ፣ከሶ

ከጢልቴ ዱሜ ግርጌ

Image
በእንዳለ ደበላ ሀዋሳ ኢዜአ “ተረግዞ ለመወለድ ያለ ተጨማሪ ቀናት ዘጠኝ ድፍን ወራት ብቻ የፈጀበት በርካቶችን ያስደመመ ልጅ  በሀዋሳ ተወልዷል”  አሉኝ አንድ በእድሜ የገፉ አዛውንት፡፡ እንዴ ታዲያ እርግዝና እኮ ዘጠኝ ወር ነው የሚፈጀው በዘጠኝ ወር መወለድ ያስደመመበት ምክንያት አልገባኝም አልኳቸው፡፡ “አይ ልጄ አሉኝ በቅዱስ መጽሀፉ የሰፈረውን እንኳን ብናይ ማርያም እየሱስ ክርስቶስን የወለደችው ከዘጠኝ ወር ከዘጠኝ ቀናት እርግዝና በኋላ ነው” አሉኝ፡፡ “እናቶችን ብትጠይቅ ልጆቻቸውን ለመውለድ ከዘጠኝ ድፍን ወራት ተጨማሪ ቢያንስ ዘጠኝ ቀናት ይኖራል ፡፡ ይህ ልጅ ግን ዘጠኝ ድፍን ወር ብቻ የተረገዘ ነው ፡፡ ያለ ተጨማሪ ቀናት ተወለደ ”፡፡  በቅርቡ ወንድ ልጅ ያስታቀፈችኝ ውዷ ባለቤቴ ልጁን የተገላገለችው አስር ወር ከሰባት ቀን መሆኑን ትውስ አለኝና የአዛውንቱን ወግ ማድመጥ ቀጠልኩ፡፡ አቶ ታደሰ ባላ ከሀዋሳ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኝ የሸበዲኖ ወረዳ ማዕከል በሆነችው ለኩ እንደተወለዱና በተለምዶ እርሻ ጣቢያ እየተባለ በሚጠራው የመንግስት እርሻ ድርጅት ተቀጥረው ሲሰሩ ቆይተው ጡረታ ከወጡ 12 ዓመት እንደሆናቸው አወጉኝ፡፡ “ዛሬ በዘጠኝ ወሩ የተወለደውን ልጅ ለማየት መጣሁ እናም በእድሜዬ እንደዛሬው ተደምሜ አላውቅም” ባይ ናቸው ፡፡ “እንዲህ ፈጥኖ ይሆናል ብዬ በፍጹም አልጠበቅሁም ነበር ፡፡ ግን ሆኖ ሳየው አስደመመኝ ፡፡ በዚች ከተማ ባልወለድባትም የስራን ሀሁ የጀመርኩባት ናት”፡፡ “ከ40 አመት በላይ የኖርኩባት በመሆኑ በዚህ መልክ በአጭር ጊዜ የሆነ ታምር ገጥሞኝ አያውቅም” ብለው ከታሪክ ያወቁትን የሀዋሳን አመሰራረት አጫወቱኝ፡፡ እሳቸው ያወጉኝን በከተማዋ ታሪክ ዙሪያ በዘለቀ ከበደና ሰርካለም አለማየ

U17 ፕሪሚየር ሊግ ፡ ሲዳማ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ተሸጋግረዋል

Image
ፎቶ ከ ሶከር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ሲጠናቀቁ ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል፡፡ 10:00 ላይ በወንጂ ሜዳ ጨዋታቸውን ያደረጉት ሐረር ሲቲ እና ሲዳማ ቡና 1-1 አቻ ተለያይተዋል፡፡ ብሩክ ሰሙ ለሐረር ሲቲ ሲያስቆጥር አንለይ የሲዳማ ቡናን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና ነጥቡን 8 በማድረስ የደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ በመቀመጥ ወደ ግማሸ ፍጻሜው ተቀላቅሏል፡፡ በተመሳሳይ 10:00 አዳማ አበበ ቢቂላ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ከተማን ወንድወሰን ቢራራ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ቢያሸንፍም ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለማለፍ በቂ አልሆነለትም፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀዋሳ ከተማ ጋር እኩል 7 ነጥብ ቢይዝም በግብ ልዩነት ተበልጦ ከምድቡ ተሰናብቷል፡፡ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በመጪው ሀሙስ አዳማ አበበ ቢቂላ ላይ ሲደረጉ 07:00 ላይ ሲዳማ ቡና ከ መከላከያ ፤ 09:00 ላይ አዳማ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ ይጫወታሉ፡፡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች 4 ዮሐንስ ደረጄ (መከላከያ) 3 የኋላሸት ፍቃዱ ( አዳማ ከተማ) 3 እንደልቡ ደሴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) 2 ታዲዮስ አዱኛ (ሐረር ሲቲ) 2 ወንድማገኝ ታደሰ (ሀዋሳ ከተማ) 2 ምንተስኖት ማቲዮስ (ሀዋሳ ከተማ) 2 ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና) 2 ኢሳ ንጉሴ (አዳማ ከተማ) 2 ዳንኤል ጌድዮን (ደደቢት) ምንጭ