Posts

Last Lap for July's Inaguration of Hawassa Industrial Park

From http://allafrica.com/stories/201606290119.html  dos Yoseph Local investors caught off-guard by accommodative measures - some can meet new criteria, some cannot During the last lap meeting with local investors before the scheduled July 3, 2016 inauguration of Hawassa Industrial Park, Arkebe Oqubay, board chairman of the Industrial Parks Development Corporation, cut the size of modalities for entry of local investors. At the meeting held on June 23, 2016, the Ethiopian Investment Commission (EIC) presented a model feasibility study to local investors, followed by a case by case question and answer period with those who bought and submitted the bid document. The investors, who were caught by surprise in what took place at the meeting, called for a consultative meeting on the way forward. "This is inconsiderate of the real price range of products, labour average salary, production area usage, investment and production cost," one of the bidders commented on the model

ፊቼ ጨምበላላ የመላ ኢትዮጵያውያን ኩራትና የአለም ቅርስ በመሆኑ ተገቢው ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል-ፕሬዚዳንት ሙላቱ

Image
( ኤፍ.ቢ.ሲ ) የፊቼ ጨምበላላ የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓል የመላ ኢትዮጵያውያን ኩራትና የአለም ህዝብም ቅርስ በመሆኑ ተገቢው ጥበቃ ሊደረግለት እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ አሳሰቡ። የፊቼ ጨምበላላ ዘመን መለወጫ በዓል ዋዜማ በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ ስነሰርዓቶች እየተከበረ ነው። በዓሉ ከአሮጌ ዓመት ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገርን ለማሳየት የሚከበር ነው። የዘንድሮው በዓል የማይዳሰስ ዓለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ በተመዘገበ ማግስት፥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚከበር መሆኑ የተለየ ያደርገዋል ተብሏል። በዛሬው እለትም የሲዳማ ባህል ፓርክ ግንባታ ማስመጀመሪያ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ ስርዓት በጉዱ ማሌ አደባበይ ተከናውኗል። የመሰረት ድንጋዩን ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በዛሬው ዕለት አስቀምጠዋል። በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት፥ የማእከሉ መገንባት የሲዳማን ባህልና ማንነት ከማስተዋወቅ በላይ የመላ ኢትዮጵያውያን ሀብት እንዲሆን ያስችለዋል። ማእከሉ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅም የሚመለከተው አካል ሁሉ በትኩረት እንዲንቀሳቀስ ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል። ከ1 ቢሊየን በላይ ወጪ የሚደረግበት ማዕከሉ በአራት አመታት ውስጥ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅም ነው የተመለከተው ። ማዕከሉ በውስጡ ሙዚየሞች፣ የተለያዩ ማዕከላት፣ ካፍቴሪያዎች፣ የመዝናኛ ቦታዎች፣ ጥብቅ ደንና ሌሎችም በርካታ ክፍሎችን ያካተተ ነው። በስነስርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የስራ ሃላፊዎች፣ ከዩኒስኮ የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች፣ በ100 ሺህ የሚቆጠሩ የሲዳማና የአካባቢው ህዝቦች ተሳታፊ ሆነዋል።

Major Animal Health Constraints of Market Oriented Livestock Development in Sidama Dale District Southern Region Ethiopia

Image
Photo  Source Abstract  Background: Knowing the status of major problems that constrain livestock development no doubt contributes to initiating projects that can help improve productivity and market success of Ethiopian farmers; aiming at contributing to reduction in poverty of the rural poor through market oriented agricultural development. The objective of this study is to characterize the livestock production system and investigating the major livestock health problems in the area. Methodology: Purposive sampling method was used to select 60 households from four peasant association (PA). A structured questionnaire was prepared and the heads of selected households were interviewed to collect data on production system characteristics and the importance of livestock health problems. Focus group discussion was also made with key respondents from each PA and the participants described the major husbandry problems in their area. Results: The results revealed that mixed crop

በሀዋሳ ከተማ ከ34 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነቡ ነው

Image
የወሬው ምንጭ ኢዜ ኣ ነው በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ማዕከል በሆነው ሀዋሳ ከተማ   ከ34 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንደሚገነቡ የክልሉ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ሰፋፊ ይዞታ ያላቸውና ለኪራይ የሚሆን ቤት ለሚገነቡ ግለሰቦች የብድር አገልግሎት የሚውል ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ መመቻቸቱም ተመልክቷል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አስቻለው ካሳዬ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት በከተማዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል ግንባታው የሚካሄደው ከመጪው ዓመት ጀምሮ ነው፡፡ "የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የገቢ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚገነቡ ሲሆን ከ34 ሺህ ቤቶች ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት በአስር ዘጠና መርሀ ግብር የሚገነቡ ናቸው" ብለዋል፡፡ በአስር ዘጠና መርሀ ግብር ለሚገነቡት  ስቱዲዮ ቤቶች የሚመዘገቡ ቤት ፈላጊዎች በወር 199 ብር ሄሳብ ለሶስት ዓመት መቆጠብ አለባቸው፡፡  " ለባለ አንድ መኝታ ቤት 368 ብር ለባለ ሁለት መኝታ 575 ብር እና ለባለሶሰት መኝታ ቤት ደግሞ  739 ብር በወር ለሰባት ዓመት የቆጠበ የቤት ባለቤት መሆን ይችላል " ሲሉ  ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡  ለግንባታው የቦታ ፣ የገንዘብና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን  ጠቁመው ለቤት ፈላጊዎች ምዝገባው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡ ተመዝጋቢዎች ከተመዘገቡበት ጊዜ ጀምሮ በየወሩ መቆጠብ ያለባቸውን ገንዘብ እየቆጠቡ 10 እና 20 በመቶ የሚሆነውን ቆጥበው እንዳጠናቀቁ ቤቱን በዕጣ እንደሚያገኙና በአንድ ጊዜም መክፈል እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ " የመኖሪያ ቤት እጣው በሚወጣበት ጊዜ መንግስት በሰጠ

‹‹የሲዳማ ዘመን መለወጫ በዓል ከብሔረሰቡ ተወላጅ አልፎ የዓለም በዓል መሆኑ አስደስቶናል››

Image
ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ወ/ሮ ምሕረት ገነነው፣ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ቱሪዝምና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሐዋሳ የቱሪስት መዳረሻና የመዝናኛ ከተማ እየሆነች የመጣች ሙደ ነች፡፡ ይህች ከተማ በአገር ውስጥ ቱሪስትም እየጎበኛት ይገኛል፡፡ በ1991 ዓ.ም. የነበረው ጠቅላላ የአገር ውስጥ ጎብኚ 19.136 ሲሆን፣ በ2008 ዓ.ም. እስከ ግንቦት ወር ደግሞ 150,000 ጎብኝተዋታል፡፡ ጠቅላላው የአገር ውስጥም የውጭ ጎብኚ ደግሞ በ1991 ዓ.ም. 21.668 የነበረ ሲሆን በዘንድሮው ዓመት እስከ ግንቦት 2008 ዓ.ም. 195,000 ሆኗል፡፡ ሌላው የሲዳማ የዘመን መለወጫ የጫምባላላ በዓል በዚህ ዓመት በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡ ይህም ለከተማዋ የቱሪስት መዳረሻነት አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ በዚህና በተያያዥ ጉዳዮች የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ቱሪዝምና የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ወ/ሮ ምሕረት ገነነውን  ታምራት ጌታቸው  አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር ፡- የጨንባላላ በዓል በቅርቡ በዩኔስኮ ተመዝግቧል፡፡ ይህ ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ወ/ሮ ምሕረት ፡-  በመጀመሪያ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ የጫንባላላ በዓል የሲዳማ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን ዘንድሮም በአገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል፡፡ ከሌሎች በዓሎች የሚለይበት የራሱ የሆነ ነገሮች አሉት፡፡ ለምሳሌ ቀኑ የፍቅር የመቻቻል ቀን ነው፡፡ በዛን ቀን ከብት የማይመታበት ሕፃን ልጅን እንኳ የማይቆጣበት ሲሆን፣ ሰዎች ቢያስቀይሙህ እንኳን ምንም ዓይነት ዕርምጃ የማትወስድበት፣ የተጣላ የሚታረቅበት ነው፡፡ በበዓሉም ቀን ጉርሳሜ የሚባል ምግብ ነው የሚቀርበው፡፡ ይህ ከብሔሩ ተወላጅ በተጨማሪ ለመላው ዓለም አስተማሪነቱ ትልቅ ነው በዓሉ ጉድ