Posts

በፕሪሚየር ሊጉ ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

Image
(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል። ሁለቱም ጨዋታዎች በክልል የተደረጉ ሲሆን፥ እነዚህም ሀዋሳ እና ይርጋለም ላይ የተካሄዱት። በዚህም መሰረት ዛሬ በ09፡00 ሰዓት ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ሊጉን በአንደኝነት የሚመራውን ቅዱስ ጊዮርጊስን በሜዳው አስተናግዷል። ጨዋታውንም ሀዋሳ ከተማ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ለሀዋሳ ከተማ የማሸነፊያ ጎሎቹን ፍርደአወቅ ሲሳይ እና አስቻለው ግርማ ከመረብ ያሳረፉ ሲሆን፥ ቅዱስ ጊዮርጊስን በባዶ ከመውጣት የታደገችውን ጎል ደግሞ ደጉ ደበበ ከመረብ አሳርፏል። በተመሳሳይ ዛሬ በ09፡00 ሰዓት ላይ በተደረገ ሌላ ጨዋታ ይርጋለም ላይ ሰዳማ ቡናን እና  ዳሽን ቢራን አገናኝቷል። ጨዋታውም 1ለ1 በሆነ የአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ለሲዳማ ቡና ኤሪክ ሙራንዳ እንዲሁም የተሸ ግዛው ደግሞ ለዳሸን ቢራ የአቻነት ጎሎቹን ከመረብ አሳርፈዋል።  የ13ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች እሁድ እና ማክሰኞ ቀጥሎ የሚደረጉ ሲሆን፥ እሁድ በ09፡00 ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማን እንዲሁም  ሆሳዕና ላይ ሀድያ ሆሳዕና ከደደቢት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። እንዲሁም ማክሰኞ 09፡00 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ ቡናን ቦዲቲ ላይ የሚያስተናግድ ሲሆን፥ በተመሳሳይ መከላከያ  አዳማ ከተማን አዲስ አበባ ስታድየም ያስተናግዳል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኤሌክትሪክ  ደግሞ ጨዋታቸውን  በ11፡30 አዲስ አበባ ስታድየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ትናነት በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ገጥሞ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። በሌላ የፕሪሚየር ሊጉ መርሃ ግብር ኤሌክትሪ

8 Telltale Signs You’re an Expat in a Country that was Never Colonized

Image
Traditional house in Ethiopia. PHOTO: Courtney Danyel Living in a country that was never a colony is actually pretty rare—unless you’re in Europe, of course. As an ex-anthropologist and travel addict, I’ve had the opportunity to visit countries across five continents, but when I moved to Ethiopia in 2014, I quickly realized I was in a unique place. Depending on how you define it, the only countries that were never colonies are Liberia, Ethiopia, Japan, Thailand, Bhutan, Iran, Nepal, Tonga, China, and possibly North Korea, South Korea and Mongolia. Some historians nitpick over this list. Ethiopia, for example, was occupied by the Italians from 1936 to 1941, until they were kicked out. They left behind pizza and pasta (which could never be a bad thing). But if these historians took the time to visit Ethiopia (or the other countries on the list), they would realize how obvious it was that they were never really colonized. From my own experience, here are eight telltale signs that told me

የሐዋሳውን መሬት መንቀጥቀጥ ሽሽት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ 5 ተማሪዎች በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ተቀጠፈ

Image
(ዘ-ሐበሻ) በሐዋሳ ከተማ ዛሬም እንደአዲስ የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰ:: ባለፈው ሳምንት ለ6 ጊዜያት የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በርካቶችን ቤታቸው ገብተው ለማረፍ እንኳ ፍርሃት እንዲደርስባቸው አድርጎ ነበር:: የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የ እረፍት ጊዜ ሰጥቶ ከየቤተሰባቸው ጋር እንዲያሳልፉ ፈቃድ በሰጠው መሰረት በርካታ ተማሪዎች ወደየ ከተማቸው ያመሩ ሲሆን በዚህም መሠረት ዛሬ ከሐዋሳ ተሳፍረው ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ 5 ወጣት ተማሪዎች ሕይወታቸው በመኪና አደጋ ተቀጥፏል:: ተማሪዎቹን ከሐዋሳ ጭና ስትሄድ የነበረችው መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ሃዋሳ ሲጓዝ ከነበረ አይሱዙ መኪና ጋር በመጋጨቷ የ5ቱ ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ የሰጠው መግለጫ ያስረዳል:: የአደጋው መን ስ ኤ ይበልጥ እየተጣራ መሆኑንም ፖሊስ አስታውቋል:: ተሽከርካሪዋ ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ሲጓዝ ከነበረ ኤፍ ኤስ አር አይሱዙ የጭነት መኪና ጋር በመጋጨቷ ነው አደጋው የደረሰው። ይህ አሰቃቂ ዛሬ ጃንዋሪ 29, 2016 7 ሰዓት ላይ የደረሰው በሞጆ እና በመኪ ከተሞች መካከል ላይ በሚገኘው የአዋሽ ወንዝ ድልድይ ላይ መሆኑም ታውቋል:: ይህ የአዋሽ ድልድይ በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ በተቃራኒ መንገድ 2 መኪኖች በአንድ ላይ ለመጓዝ አስቸጋሪ እና አስፈሪ ነው የሚሉት ለዘ-ሐበሻ አስተያየታቸውን የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች የክልሉ የትራፊክ ፖሊስ በድልድዩ ላይ በአንድ ጊዜ አንድ መኪና ብቻ እንዲያልፍ የሚያዝ ህግ ማውጣት ነበረበት እንዲሁም መኪኖችም በፍጥነት እንዳይሄዱ  ማስጠንቀቂያዎችን በአካባቢው መለጠፍ ነበረበት ሲሉ ይናገራሉ:: Source  http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/01/Awash-Bridge-and-hawasa-student

3 ህፃናት ሃዋሣ ዩኒቨርሲቲ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ

Image
በሃዋሣ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የሃዋሣ ዩኒቨርሲቲ ፍሳሽ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ የገቡ 3 ህፃናት ህይወታቸው አለፈ፡፡ ዕድሜያቸው 8‚ 12‚ እና 14 የሚሆናቸው ህፃናት፤ በሽቦ አጥር በተከለለው የዩኒቨርሲቲው የቆሻሻ ፍሳሽ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ በአጥር ተንጠላጥለው በመግባት ለመዋኘት ሲሞክሩ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ወደ ፍሳሽ ማጠራቀሚያው የገቡት አራት ህፃናት ሲሆኑ ከሁለት መንትያ ወንድማማቾች መካከል አንደኛው ወደ ማጠራቀሚያ ውስጥ ሳይገባ በመቅረቱ ህይወቱ የተረፈ ሲሆን፤  የስምንት አመቱ ህፃን መንትያ ወንድሙን ጨምሮ ሁለት ጓደኞቹ በገንዳው ውስጥ ገብተው በመቅረታቸው ሁኔታውን ለሰዎች ነግሮ፣ የህፃናቱ አስከሬን ከገንዳው ውስጥ ሊወጣ ችሏል፡፡ የህፃናቱ የቀብር ስነስርዓት ከትናንት በስቲያ በስላሴ ቤተክርስቲያን የተፈፀመ ሲሆን በህፃናቱ ሞት የአካባቢው ነዋሪዎች በእጅጉ አዝነዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ለፍሳሽ ማጠራቀሚያ ባዘጋጀው ገንዳ ውስጥ የተጠራቀመውን ፍሳሽ እያጣራ መልሶ ለአገልግሎት እንዲውል በሚያስችል ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፤ ማጠራቀሚያው ግን በበቂ ሁኔታ በአጥር ተከልሎና ጥበቃ ተመድቦለት ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባ ነበር ብለዋል፡፡ ስለጉዳዩ እንዲነግሩን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ በሌላ በኩል ከሰሞኑ ርዕደ መሬት ጋር በተያያዘ አዋሣ ዩኒቨርሲቲ ለ15 ቀናት በመዘጋቱ ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው በመኪና ሲጓዙ የነበሩ 5 የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ትናንት ዝዋይ ላይ በተፈጠረ መኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል፡፡ Source  http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50458