Posts

በሃዋሳ የምገኙ የሴካፋ ተሳታፊ ቡድኖች በደቡብ ክልል መንግስት የጻጥታ ኃይል ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑ ተነገረ

Image
በሃዋሳ የምገኙ የሴካፋ ተሳታፊ ቡድኖች በደቡብ ክልል መንግስት የጻጥታ ኃይል ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑ ተነገረ Photo from citizentv የኬኒያውን ስትዚን ዲጅታል ጠቅሶ ወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደዘጋበው በዘንድሮው ኢትዮጵያ በማስተናገድ ላይ ባለችው የሴካፋ ውድድር ተሳታፊ የሆኑ እና ውድድራቸውን ሃዋሳ ላይ በማድረግ ላይ ያሉት ብሄራዊ ብድኖች በክልሉ ጻጥታ ኃይል ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው። ዝርዝር ወሬውን ከታች ያንቡ፤ Tight security as Harambee Stars train ahead of Zanzibar clash   

የሲዳማ ኣዲስ ኣመት በዓል _ፊቼን በኣለም ቅርስነት ለመመዝገብ የምደረገውን የመዝጋቢው ኮሚቴ ውይይት ነገ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ተኩል ጀምሮ ኦንላይን መከታተል ይችላሉ

Image
የቀጥታ ስርጭቱን በዚህ ሊንክ ይከታተሉ: Live

በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል የተባለውና ከሩብ ፍፃሜው እስከ ፍፃሜው ያለው ጨዋታ በሀዋሳ ሊካሄድ እንደሚችል በስፋት እየተነገረ ነው

Image
( ኤፍ.ቢ.ሲ ) በ2015ቱ 38ኛው የምስራቅ አና መካከለኛው የእግር ኳስ ውድድር(ሴካፋ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ሩብ ፍጻሜ መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል። በምድብ አንድ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ አቻዋ ጋር በሀዋሳ ስታዲየም የተጫወተች ሲሆን፥ ውጤቱም 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። በጨዋታው ታንዛኒያ በ51ኛው ደቂቃ ጎል አስቆጥረው ጨዋታውን መምራት ችለው የነበረ ሲሆን፥ ሙሉ የጨዋታው ሰዓት ተጠናቆ የባከነ ሰዓት ላይ የታንዛኒያ ብሄራዊ ቡድን በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠረው ግብ ዋልያዎቹ አቻ በሆነ ውጤት ጨዋታውን አጠናቀው ሊወጡ ችለዋል። በዚህም መሰረት ዋልያዎቹ ከምድብ አንድ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳን ተከትለው በ4 ነጥብ በሶሰተኝነት አጠናቀዋል። ዋልያዎቹ ምርጥ ሶስተኛ በመሆን ወደ ሩብ ፍጻሜ መቀላቀል መቻላቸውንም አረጋግጠዋል። በምድብ ሁለት ኡጋንዳ እና ብሩንዲ በሀዋሳ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያካሄዱ ሲሆን፥ ኡጋንዳ ጨዋታውን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች። የ13 ጊዜያት የሴካፋ አሸናፊዋ ኡጋንዳ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ከምድብ ሶስት ደቡብ ሱዳን በመጀመሪያ ተሳትፎዋ ወደ ሩብ ፍጻሜ ስታልፍ፥ ማላዊም ደቡብ ሱዳንን ተከትላ  ማለፏን አረጋጣለች። በተያያዘ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል የተባለውና ከሩብ ፍፃሜው እስከ ፍፃሜው ያለው ጨዋታ በሀዋሳ ሊካሄድ እንደሚችል በስፋት እየተነገረ ነው። ለዚህም የሴካፋ አወዳዳሪ አካላት፣ የውድድሩ ስፖንሰር እና የቴሌቪዥን አስተላላፊው ዲ.ኤስ.ቲቪ እንዲሁም በሀዋሳ የሚገኙት ቡድኖች በከተማውና መስተንግዶው በመደሰታቸው እና ቀሪ ውድድሮች በሀዋሳ እንዲካሄድ ፍላጎት በማሳየታቸው ነው ተብሏል።

የሲዳማ ኣዲስ ኣመት በዓል - ፊቼ በኣለም የቅርስ መዝገብ ለመመዝገብ ከጫፍ መድረሱ ተሰማ

Image
ፎቶ ከዩኔስኮ ድረገጽ የፊቼ በዓል ከነገ ማለትም እንደፈሬንጆቹ የዘመን ኣቆጣጠር ከኖቨምቤር 29 ጀምሮ ለኣራት ቀናት በናሚቢያዋ ዋና ከተማ ዊንድሆክ በምካሄደው የዩኔስኮ ኣስረኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በኣለም ቅርስነት ለመመዝገብ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ዝርዝር ውስጥ ከገቡት ቅርሶች መካከል መሆኑ ታውቋል። የወራንቻ ኢንፎርሜችን ኔትዎርክ የዩኔስኮን ድረገጻ ጠቅሶ እንደዘገበው የሲዳማን ኣዲስ ኣመታ በኣል ፊቼን ጨምሮ ሌሎች ከ 40 የምበልጡ መሰል ጥበቃ የሚሹ ባህላዊ እሴቶች ከውሳኔ ስጪ ኮሚቴ ፊት ቀርበዋል። ሌሎች በርካታ ቁጥር ያላቸው እና ኣለም ኣቀፍ ጥበቃ እንድደረግላቸው በተለያዩ ኣገራት የቀረቡ ባህላዊ እሴቶች መስፈርቶችን ባለሟሟላታቸው ከውድድር ውጭ መሆናቸው ተዘግቧል። የሲዳማ ኣዲስ ኣመት በኣል ፊቼ ለሲዳማ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኣለም ህዝብ ካለው ከፍተኛ ፋይዳ ኣንጻር በኣለም ቅርስነት ተመዝግቦ ተገብው ጥበቃ እንዲደረግለት ያሻል። ምንጭ

የሎቄ ተጠቂዎች ያለ ምንም ፍትህ 14ኛ ኣመታቸውን ልይዙ ነው

Image
የሰፊውን የሲዳማ ህዝብ መብት እና ኣንድነት ለማስጠበቅ ስሉ ሎቄ በካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ኃይሎች በግፊ የተገደሉት፤ ለተለያዩ ኣካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳቶች የተዳረጉ ሲዳማውያን ያለ ምንም ፍትህ ኣስራ ኣራተኛ ኣመታቸውን ልይዙ መቃረባቸው ታውቋል። ዝርዝሩን ሊንኩን ተጭነው ያንቡ፤   ኣያንቱ