የከተሞችን ዕድገት የሚመዝን አለም አቀፍ መስፈርት በኢትዮጵያ ሊተገበር ነው፤ ከሃዋሳ ምን እንጠብቅ?
የከተሞችን ዕድገት የሚመዝን አለም አቀፍ መስፈርት በኢትዮጵያ ሊተገበር ነው туристический онлайн-справочник Лучшие Андроид планшеты አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2008 (ኤፍ. ቢ. ሲ) የኢትዮጵያን የከተሞች እድገት መመዘን የሚያስችል አለም አቀፍ መስፈርት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አስታወቀ። መስፈርቱም በከተሞች ቀጣይነት ያለው እና ሁሉን አቀፍ እድገት በማስመዝገብ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማደረግ ነዋሪዎቻቸውን የላቀ ተጠቃሚ ያደረጋል ብሏል ሚኒስቴሩ። የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሀይሌ ከፋና ብሮድ ካስቲን ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ መስፈርቱን በ44 ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው ብለዋል። መስፈርቱም ወጥነት የሌለውን የከተሞች እድገት በማሰቀረት የሀገሪቱን ከተሞች በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳደዳሪ የሚያደርጋቸው ነው ሲሉም አቶ መኩሪያ ተናግረዋል። መመዘኛው በዘጠኝ ዋና ዋና መስፈትሮች የተከፈለና ከመቶ በላይ ዝርዝር መመዘኛዎች የሚኖሩት ሲሆን፥ የከተሞች ምርታማነት የሚለው ከመሰፈርቶቹ ቀዳሚ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በዚህም ከከተማው ነዋሪው የሚሰበሰብ ግብርና የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶችን ለነዋሪዎቹ ለማቅረብ የሚያደረገው ወጪ ሲነፃፀር ምን ያህል የተጣጣመ ነው የሚለውም ተካቶበታል። እንዲሁም ከተማው በስሩ አቅፎ ከያዘው የህዝብ ቁጥር ጋር የሚሰጠው ውጤት፣ አንድ በከተማ የሚኖር ግለሰብ በቀን ምን ያህል ሊትር ውሃ ይደረሰዋል፣ በከተማው ከሚመረተው የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ምን ያህሉ በተዘርጋለት ስርዓት ይወገዳል፣ የትምህርት እና ጤና መስረተ ልማት ዝርጋታም በአለም አቀፍ