Posts

IMF worried over growing debts by state enterprises, limited room for the private sector

Image
Little appears to have changed in the views of those at the International Monetary Fund (IMF) about Ethiopia’s macroeconomic performance. Disclosing its latest conclusion, on September 30, 2015, the assessment and recommendations of the IMF executive board for Ethiopia is the “same ol’ same ol’,” despite an unusually brief report with a couple of omissions from its predecessors. The verdict is that growing at 8.7pc, Ethiopia’s economic performance remains “buoyant,” a word with connotations of “light-heartedness”, which executive board members used, changing the tone from “robust,” the term used in their previous assessments, implying vigour in the economy over the years. The size of the economy grew from 877 billion Br in 2013 to 1.2 trillion Br last year, largely due to “prudent fiscal and pro-poor growth” policies the government has been following, according to the IMF. Yet, it warns that the economy faces risks from “rising domestic and external vulnerabilities,” again looking

ሙስና በአዲስ አበባ በኔትወርክ በመያያዙ ከኢሕአዴግ በስተቀር የሚፈታው እንደሌለ ተነገረ

Image
-  ተመዘገበ የተባለው የባለሥልጣናት ሀብት ይፋ እንዲደረግ ተጠየቀ ‹‹በየስብሰባው እየተወዳደሱና በጭብጨባ እየተደጋገፉ መለያየት ይቁም›› የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስና፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር እጦት ከወረዳ እስከ ከተማ አስተዳደሩ ድረስ በኔትወርክ የተያያዙ በመሆናቸው ሊፈታቸውም ሆነ ሊያስቆማቸው የሚችለው ‹‹ድርጅቱ›› ኢሕአዴግ ብቻ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መስከረም 20 ቀን 2008 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ለግማሽ ቀን አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ ላይ ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ የሁሉም ክፍላተ ከተሞች፣ ወረዳዎች ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተው ነበር፡፡ ተሳታፊዎቹ እንደተናገሩት የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ በመጠናቀቅ ላይ ካለው መስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍላተ ከተሞች ሊባል በሚችል ሁኔታ ከግንባታ፣ ከመሬትና ቤቶች ጋር በተገናኘ ነዋሪዎች እያለቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በተለይ በአዲሱ የሥራ ዘመን ከኃላፊነታቸው እንደሚነሱ ያወቁ፣ የጠረጠሩና ሹክሹክታ የሰሙ የክፍላተ ከተሞችና የወረዳዎች ተሿሚዎች ‹‹የሚፈርስ የማይፈርስ፣ መንገድ የሚወጣበት የማይወጣበት፣ ክርክር ያለበት የሌለበት፣ ግንባታ የተፈቀደለት ያልተፈቀደለት…›› በማለት በሥራ ሰዓትና ከሥራ ውጪ የነዋሪዎችን ግድግዳና የውጭ በር ቀለም ሲቀቡ እንደሚውሉ ጠቁመዋል፡፡ ያለምንም ማስጠንቀቂያ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ኅብረተሰቡን ሰላም እየነሳው በመሆኑ፣ የአስተዳደሩና የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች ትኩረት ሰጥተው ሊያስቆሟቸው ወይም ዕርምጃ ሊወስዱባቸው እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ አሳስበዋ

በክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ላይ ባለሥልጣናት ጣልቃ እንደሚገቡ ተጠቆመ

በክልል የመንግሥት ተቋማትና ሕዝብ ላይ የሚፈጸም ሙስናን ለመከላከል የተቋቋሙ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች፣ የክልል ባለሥልጣናት ጣልቃ በመግባት ለሥራቸው እንቅፋት እንደሚሆኑ ተገለጸ፡፡ የአገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት የሁለት በጀት ዓመት (የ2006 እና 2007) የፀረ ሙስና እንቅስቃሴን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በተደረገው ውይይት እንደተገለጸው፣ የክልሎች የሥነ ምግባረና ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ከፌዴራሉ የተለየ የሥራ አፈጻጸም እንዳለቸው ተነግሯል፡፡ የፌደራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን እንደተናገሩት፣ የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሚከታተላቸው ትልልቅና ግዙፍ የሕዝብ ሀብትን የሚያንቀሳቅሱ ድርጅቶችን ነው፡፡ በእነሱ ላይ ችግር ሲያጋጥም ኮሚሽኑ ለሚወስደው ዕርምጃ በትልልቅ ባለሥልጣናት ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡ አፈጻጸሙ ጥሩ ሲሆንም የማበረታታት ሁኔታዎች መኖራቸውን፣ ነገር ግን ክልሎች ተፅዕኖ አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ባለሥልጣናት ጣልቃ እየገቡ የምርመራ ሒደቶችን እንደሚያስቀሩም ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ የጣልቃ ገብነቱን ዓይነትና ዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ በፌዴራል በኩል ባለፉት ሁለት የበጀት ዓመታት በርካታ የሕዝብና የመንግሥት ንብረቶችን ማስመለስ መቻሉን፣ በሙሰኞች ተወስደው የነበሩ ንብረቶች መመለሳቸውንና በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ሙስናን ለመከላከል የሚበተኑ ፖስተሮች፣ በመገናኛ ብዙኃን የሚነገሩና የሚታዩ ፖስተሮችና ድራማዎች ከማስተማር ባለፈ በተቃራኒው መልዕክት ስለማስተላለፋቸው የተነሳውን ጥያቄ ኮሚሽነር ዓሊ አልፈውታል፡፡ በውይይቱ ላይ በቅርቡ በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሆነው የተ

የኢትዮጵያ ቡና ደረጃዎች ከአሥር ወደ ስድስት ዝቅ እንዲሉ ተወሰነ

Image
በአሥር ደረጃዎች ተከፋፍሎ ለገበያ ሲቀርብ የነበረው የኢትዮጵያ ቡና ምርት ወደ ስድስት ደረጃዎች ዝቅ ብሎ ለግብይት እንዲበቃ ተወሰነ፡፡  ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ እስካሁን የአገሪቱ የቡና ምርት በአሥር ደረጃዎች ተከፋፍሎ እንደየደረጃው  ዋጋ እየተሰጠው ሲሸጥ ቆይቷል፡፡ ይህ የደረጃ አሰጣጥ ግን ለአሠራርም ሆነ የአገሪቱ የቡና ምርት ሊያገኝ የሚገባውን ዋጋ እንዳያገኝ በማድረጉ በአዲስ አሠራር እንዲለወጥ ተደርጓል፡፡ በቡና ደረጃዎች አሰጣጥ ላይ የተደረገ ጥናት አዋጭ የሚሆነው አሥር የነበሩትን የቡና ደረጃዎች ዝቅ ማድረግ እንደሚገባ ነው፡፡  በዚህ መሠረት የተደረገውን ጥናት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣንና ንግድ ሚኒስቴር በመቀበላቸው፣ የ2008 ዓ.ም. የቡና ምርት ከሚገባበት ከታኅሳስ ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ ቡና በስድስት ደረጃዎች ተከፋፍሎ ለገበያ እንዲቀርብ መወሰኑን፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ አረጋግጠዋል፡፡ እንደ አቶ ኤርሚያስ ገለጻ፣ በዚህ ውሳኔ መሠረት ለምሳሌ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተብሎ ደረጃ ይሰጣቸው የነበሩትን በአንድ ደረጃ ማጠቃለል ያስችላል፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ የሚሰጣቸው የቡና ዓይነቶች ዋጋ ልዩነት ተቀራራቢ በመሆኑ በአንድ ዋጋ እንዲሸጡ ያስችላል፡፡ የተሻለ ዋጋም ያስገኛል፡፡ በመጋዘን አሠራርም አሥር ቦታዎች ከፋፍሎ ከማስቀመጥ በስድስት ቦታዎች ማስቀመጥ ጊዜና ጉልበትን ይቆጥባል ብለዋል፡፡ በአዲሱ የምርት ዘመን ከታኅሳስ 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ አሠራር፣ በቡና አቅራቢዎችም መደገፉን የምርት ገበያው መረጃ ያመለክታል፡፡ ከአንድ እስከ አምስት ደረጃ የተሰጣቸው ለኤክስፖርት የሚቀርቡ ሲሆን፣ ደረጃ ስድስት የተሰጠው ቡና ደግሞ

Sunshine & Hilton Worldwide Sign Agreement for Hilton Hawassa Resort & Spa

Image
Sunshine Business Plc., sister company of Sunshine Investment Group, and Hilton Worldwide today signed a management agreement for the upscale Hilton Hawassa Resort & Spa, which is expected to begin welcoming guests in 2020. “With a strong legacy of hospitality in Ethiopia, Hilton Hawassa Resort & Spa will join Hilton Addis Abeba in offering world-renowned service, in this rapidly evolving part of the country,” said Patrick Fitzgibbon, senior vice president of development, Europe & Africa for Hilton Worldwide. “With a further 55 million dollars government funding committed to delivering an airport fro Hawassa by 2018, the future is bright for travellers to southern Ethiopia. We are delighted to be making this announcement here where we are also celebrating the milestone of 20,000 Hilton rooms open or under development across Africa,” he added. Samuel Tafese, President of Sunshine Investment Group on the occasion expressed his delight to have finalized the agreement wit