Posts

በክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ላይ ባለሥልጣናት ጣልቃ እንደሚገቡ ተጠቆመ

በክልል የመንግሥት ተቋማትና ሕዝብ ላይ የሚፈጸም ሙስናን ለመከላከል የተቋቋሙ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች፣ የክልል ባለሥልጣናት ጣልቃ በመግባት ለሥራቸው እንቅፋት እንደሚሆኑ ተገለጸ፡፡ የአገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት የሁለት በጀት ዓመት (የ2006 እና 2007) የፀረ ሙስና እንቅስቃሴን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በተደረገው ውይይት እንደተገለጸው፣ የክልሎች የሥነ ምግባረና ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ከፌዴራሉ የተለየ የሥራ አፈጻጸም እንዳለቸው ተነግሯል፡፡ የፌደራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን እንደተናገሩት፣ የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሚከታተላቸው ትልልቅና ግዙፍ የሕዝብ ሀብትን የሚያንቀሳቅሱ ድርጅቶችን ነው፡፡ በእነሱ ላይ ችግር ሲያጋጥም ኮሚሽኑ ለሚወስደው ዕርምጃ በትልልቅ ባለሥልጣናት ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡ አፈጻጸሙ ጥሩ ሲሆንም የማበረታታት ሁኔታዎች መኖራቸውን፣ ነገር ግን ክልሎች ተፅዕኖ አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ባለሥልጣናት ጣልቃ እየገቡ የምርመራ ሒደቶችን እንደሚያስቀሩም ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ የጣልቃ ገብነቱን ዓይነትና ዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ በፌዴራል በኩል ባለፉት ሁለት የበጀት ዓመታት በርካታ የሕዝብና የመንግሥት ንብረቶችን ማስመለስ መቻሉን፣ በሙሰኞች ተወስደው የነበሩ ንብረቶች መመለሳቸውንና በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ሙስናን ለመከላከል የሚበተኑ ፖስተሮች፣ በመገናኛ ብዙኃን የሚነገሩና የሚታዩ ፖስተሮችና ድራማዎች ከማስተማር ባለፈ በተቃራኒው መልዕክት ስለማስተላለፋቸው የተነሳውን ጥያቄ ኮሚሽነር ዓሊ አልፈውታል፡፡ በውይይቱ ላይ በቅርቡ በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሆነው የተ

የኢትዮጵያ ቡና ደረጃዎች ከአሥር ወደ ስድስት ዝቅ እንዲሉ ተወሰነ

Image
በአሥር ደረጃዎች ተከፋፍሎ ለገበያ ሲቀርብ የነበረው የኢትዮጵያ ቡና ምርት ወደ ስድስት ደረጃዎች ዝቅ ብሎ ለግብይት እንዲበቃ ተወሰነ፡፡  ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ እስካሁን የአገሪቱ የቡና ምርት በአሥር ደረጃዎች ተከፋፍሎ እንደየደረጃው  ዋጋ እየተሰጠው ሲሸጥ ቆይቷል፡፡ ይህ የደረጃ አሰጣጥ ግን ለአሠራርም ሆነ የአገሪቱ የቡና ምርት ሊያገኝ የሚገባውን ዋጋ እንዳያገኝ በማድረጉ በአዲስ አሠራር እንዲለወጥ ተደርጓል፡፡ በቡና ደረጃዎች አሰጣጥ ላይ የተደረገ ጥናት አዋጭ የሚሆነው አሥር የነበሩትን የቡና ደረጃዎች ዝቅ ማድረግ እንደሚገባ ነው፡፡  በዚህ መሠረት የተደረገውን ጥናት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣንና ንግድ ሚኒስቴር በመቀበላቸው፣ የ2008 ዓ.ም. የቡና ምርት ከሚገባበት ከታኅሳስ ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ ቡና በስድስት ደረጃዎች ተከፋፍሎ ለገበያ እንዲቀርብ መወሰኑን፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ አረጋግጠዋል፡፡ እንደ አቶ ኤርሚያስ ገለጻ፣ በዚህ ውሳኔ መሠረት ለምሳሌ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተብሎ ደረጃ ይሰጣቸው የነበሩትን በአንድ ደረጃ ማጠቃለል ያስችላል፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ የሚሰጣቸው የቡና ዓይነቶች ዋጋ ልዩነት ተቀራራቢ በመሆኑ በአንድ ዋጋ እንዲሸጡ ያስችላል፡፡ የተሻለ ዋጋም ያስገኛል፡፡ በመጋዘን አሠራርም አሥር ቦታዎች ከፋፍሎ ከማስቀመጥ በስድስት ቦታዎች ማስቀመጥ ጊዜና ጉልበትን ይቆጥባል ብለዋል፡፡ በአዲሱ የምርት ዘመን ከታኅሳስ 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ አሠራር፣ በቡና አቅራቢዎችም መደገፉን የምርት ገበያው መረጃ ያመለክታል፡፡ ከአንድ እስከ አምስት ደረጃ የተሰጣቸው ለኤክስፖርት የሚቀርቡ ሲሆን፣ ደረጃ ስድስት የተሰጠው ቡና ደግሞ

Sunshine & Hilton Worldwide Sign Agreement for Hilton Hawassa Resort & Spa

Image
Sunshine Business Plc., sister company of Sunshine Investment Group, and Hilton Worldwide today signed a management agreement for the upscale Hilton Hawassa Resort & Spa, which is expected to begin welcoming guests in 2020. “With a strong legacy of hospitality in Ethiopia, Hilton Hawassa Resort & Spa will join Hilton Addis Abeba in offering world-renowned service, in this rapidly evolving part of the country,” said Patrick Fitzgibbon, senior vice president of development, Europe & Africa for Hilton Worldwide. “With a further 55 million dollars government funding committed to delivering an airport fro Hawassa by 2018, the future is bright for travellers to southern Ethiopia. We are delighted to be making this announcement here where we are also celebrating the milestone of 20,000 Hilton rooms open or under development across Africa,” he added. Samuel Tafese, President of Sunshine Investment Group on the occasion expressed his delight to have finalized the agreement wit

በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የፍጻሜ ጫዋታ ሀዋሳ ከነማ ድል ኣልቀናውም

Image
በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ጨዋታ ዛሬ 10 ሰአት ላይ መከላከያና ሀዋሳ ከተማ የፍጻሜ ጨዋታቸውን አድርገዋል። በጨዋታውም መከላከያ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል። መከላከያ በመጀመሪያው አጋማሽ ምንይሉህ ወንድሙ እንዲሁም በሁለተኛው ግማሽ ፍሬው ሰለሞን ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች ነው ማሸነፍ የቻለው። በዚህም ክለቡ በሶስት አመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ አሸናፊ ሲሆን፥ በአጠቃላይም ለ12ኛ ጊዜ የጥሎ ማለፉን ዋንጫ ማሸነፍ ችሏል። ይህም የጥሎ ማለፉን ዋንጫ ብዙ ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚ ክለብ ያደርገዋል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ 11 ጊዜ በማሸነፍ ይከተላል። መከላከያ የጨዋታው አሸናፊ በመሆኑ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ ይፎካከራል። በመጭው መስከረም 23 ቀን ከአምናው የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታውን ያደርጋል። ጨዋታውን ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኛነት መርተውታል። - See more at: http://www.fanabc.com/index.php/fbc-sport/item/10525-%E1%88%98%E1%8A%A8%E1%88%8B%E1%8A%A8%E1%8B%AB-%E1%8B%A82007-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8C%A5%E1%88%8E-%E1%88%9B%E1%88%88%E1%8D%8D-%E1%8A%A0%E1%88%B8%E1%8A%93%E1%8D%8A-%E1%88%86%E1%8A%90.html#sthash.PIkEK4LD.dpuf

ሂልተን ሀዋሳ ሪዞርትና ስፓን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

Image
( ኤፍ.ቢ.ሲ ) ሂልተን ሀዋሳ ሪዞርትና ስፓን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ። ስምምነቱን ሂልተን አለም አቀፍ እና ሰንሻይን ቢዝነስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ናቸው ዛሬ የተፈራረሙት። በሃዋሳ ሀይቅ ዳርጃ በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈው ሂልተን ሃዋሳ ሪዞርትና ስፓ፥ ግንባታው በዚህ አመት ነው የሚጀመረው። ለግንባታውም 42 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት እንደተያዘለት ነው የሂልተን አለም አቀፍ የአውሮፓና የአፍሪካ የልማት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ፓትሪክ ሲትዝዲቦን የተናገሩት። የሰንሻይን ቢዝነስ ሀላፊነት የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤትና ፕሬዚዳንት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በበኩላቸው፥ መንግስት በክልሉ የሚያካሂዳቸው ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ሰንሻይንን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችን በተለያዩ የገበያ ዘርፎች እንዲሳተፍ ያግዛል ብለዋል። ሂልተን ሃዋሳ ሪዞርትና ስፓ 169 ክፍሎች እና ቪላዎችን እንዲሁም 6 የስብሰባ አዳራሾችን የሚያካትት ሲሆን፥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020 እንግዶች የመቀበል ስራውን ይጀምራል።