የኢትዮጵያን ቡና አምራቾች የቡና ገበያ የሚያጠናክር ውድድር ሊካሄድ ነው
የኢትዮጵያን ቡና አምራቾች በዓለም የቡና ገበያ ማስተዋወቅ የሚያስችል ውድድር በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው። ውድድሩ በአፍሪካ ሲካሄድ የመጀመሪያው እንደሆነም ተገልጿል። የቡና አምራቾቹን የሚያወዳድረው ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ዩሺማ የተሰኘ የጃፓን የተፈጨ ቡና አከፋፋይ ድርጅት ሲሆን የሲዳማ ቡና አምራቾችን ብቻ ያሳትፋል። የድርጅቱ የአቅርቦት ትስስር ማኔጅመንት ዳይሬክተር ሚስተር ቲቲሱያ ሴኪ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ቡና በከፍተኛ መጠን የምታመረትና እምቅ የቡና ኃብትም ያላት አገር ናት። በመሆኑም ይህ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ውድድር ኢትዮጵያ ውስጥ ይደረጋል። ውድድሩ በሲዳማ ክልል በሚገኙ ቡና አምራቾች መካከል ከጥር እስከ የካቲት 2008 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ከ24 ሺህ በላይ አምራቾች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በቀጣይ ሌሎች ክልሎችን ያሳተፈ ውድድር ለማካሄድ መታቀዱንም ነው የተናገሩት ዳይሬክተሩ። ድርጅቱ በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 6ኛ የሚወጡ አሸናፊዎችን የመጀመሪያ ደረጃ ቡና ከመደበኛው ዋጋ ከ10 እስከ 30 በመቶ በሚደርስ ጭማሪ ይገዛቸዋል ብለዋል። ጥሬው የቡና ፍሬ ወደ ጃፓን ከተላከ በኋላ ጥልቅ በሆነ የጥራት ማረጋገጫ መመዘኛ የተለያዩ ምርመራዎች እንደሚደረግለትም ገልጸዋል። አምራቾቹ በውድድሩ መሳተፋቸው ምርታማነታቸውንና ጥራታቸውን የሚሻሻል በመሆኑ የቡናቸው ዋጋ በዚያው መጠን እንደሚያድግ ተናግረዋል። በጃፖን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ማርቆስ ተክሌ በበኩላቸው ውድድሩ አምራቾች ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው እንዲያመርቱ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠናን ያካተተ ነው። ለቴክኖሎጂ ሽግግር ዕድል የሚፈጥርና የቡና አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪውንም የሚያሻሽል መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሚስተር ካዙሂ