Posts

Ethiopia: 3 days of mourning after confirmation of Islamic State killings

ADDIS ABABA, Ethiopia –   Ethiopia's government has declared three days of mourning after confirming that many Ethiopians held captive in Libya were killed by the Islamic State group, after the group released a video on Sunday of the killings. The government said in a statement Monday that the days of mourning will be observed starting Tuesday and that during this time the national flag will fly at half-mast. The statement said that Ethiopia's lawmakers will meet Tuesday to discuss the killings and consider a response. A 29-minute video believed to be released by the Islamic militants shows at least 35 Ethiopian Christians held captive in Libya being shot or beheaded by extremists. Redwan Hussein, an Ethiopian government spokesman, said on Sunday that he believed the victims were Ethiopian migrants trying to reach Europe. http://www.foxnews.com/world/2015/04/20/ethiopia-3-days-mourning-after-confirmation-islamic-state-killings/

የኣብዘኛዎቹ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ወንድ ተማሪዎች በዘንድሮው ኣገር ኣቀፍ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በመረጭነት ኣለመመዝገባቸው ምስጥር ምንድነው?

Image
የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጠቅሶ እንደዘጋበው በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በዘንድሮው ምርጫ ላይ በመራጭነት ከተመዘጋቡት ተማርዎች መካከል 70 ከመቶ የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች ናቸው። እንደዜና ምንጩ ዘጋባ ከሆነ በዩኒቨርሲቲው በስድስት ካምፓስ በተቋቋመዉ 31 የምርጫ ጣቢያዎች  በመራጭነት ከተመዘገቡት 4 ሺህ 359  ተማሪዎች  መካከል 3 ሺህ 40 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን  የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ሲዳማ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ ተናግረዋል፡፡ ለዝርዝር ወሬውን ከታች ያንቡ፦ ሃዋሳ ሚያዝያ 10/2007 የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን እያካሄዱት ያለው የምረጡኝ ቅስቀሳና የክርክር መድረክ የተሻለ አማራጭ ፖሊሲና ፕሮግራም ያለውን ፓርቲ ለይተው እንዲያውቁ እንዳስቻላቸውን አንዳንድ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አስታወቁ። ከዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መካከልየመስኖና ዉሀ ሃብት አስተዳዳር  የአራተኛ ዓመት ተማሪ ፍሬወይን ኢታይ በሰጠችው አስተያየት በመገናኛ ብዙሃን የሚካሄደው የምረጡኝ ቅስቀሳና የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ማንን መምረጥ እንዳለብኝ ካሁኑ ለመወሰን ረድቶኛል " ብላለች። ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ እያካሄዱት ያለው የምረጡኝ ቅስቀሳ በሀገሪቱ እየተገነባ ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳይ መሆኑንም አስረድታለች፡፡ እንዲሁም በዙሁ ትምህርት ዘርፍ የአምስተኛ ዓመት ተማሪ መዓዛ ገብረ መድህን በበኩሏ ከባርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳና ክርክር በምርጫው ሀገሪቱንና ህዝቦቿን ከድህነትና ኃላቀርነት ለማላቀቅ ብቃት ያለውን ፓርቲ ለይታ ለመምረጥ የሚያስችላትን ዕውቀት እንዳገኘች ገልፀዋለች፡፡ " በተለይ የሴቶችን ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች

ክልል አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

Image
(ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጪው ግንቦት የሚካሄደው 5ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ፣ ፍትሃዊ፣ ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እና ፓርቲዎች እስካሁን የተጓዙበትን መንገድ ቆም ብለው የሚመክሩበት ክልል አቀፍ መድረክ በሀዋሳ ከተማ ዛሬ ተካሂዷል። በመድረኩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ለክልል እና ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሚወዳደሩ ፓርቲዎች ተሳትፈውበታል። የእስካሁኑን የምርጫ ሂደትን ለመፈተሽ ምርጫውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ በስኬት ለማካሄድ የባለድርሻ አካላት ሚና የሚል የመነሻ ፅሁፍም ቀርቦም ውይይት ተካሂዶበታል። መድረኩ ደኢህዴን /ኢህአዴግ በምርጫው የድርጅቱ የእስካሁን እንቅስቃሴ የሚፈተሽበት ምቹ አጋጣሚ መሆኑን በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የድርጅቱ ተወካይ አቶ ሁሴን ኑረዲን ቀደም ብለው ተናግረዋል። መድረኩ ፓርቲው ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተፈቱበትን መንገድ እንዲሁም መጪው ምርጫ የተሳካ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀቱን ለማሳወቅ ጠቃሚ መሁኑን ነው ያነሱት። በደቡብ ክልል የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ለገሰ ላንቃሞ በበኩላቸው ፥ መድረኩ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ መዘጋጀቱ ፓርቲዎች ያሏቸውን አማራጮች ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ይረዳል ብለዋል። በሃዋሳ እየተካሄደ ባለው መድረክ ላይ የተለያዩ ፓርቲዎች ሃላፊዎች እና ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመውበታል። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፅህፈት ቤት በጋራ በመተባባር ነው መድረኩን ያዘጋጁት። በአጠቃላይም በመድረኩ ላይ ሶስት ጥናታዊ ፅሁፎች ለውይይት ቀርበዋል።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ደደቢትን አሸነፈ

Image
ሃዋሳ ሚያዚያ 12/2007 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ግጥሚያ ትናንት በይርጋዓለም ከተማ ሁለገብ ስታዲዮም ቀጥሎ ሲዳማ ቡና ደደቢትን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸነፈ። በጨዋታው የሲዳማ ቡናው አጥቂ ኤርክ ሙራንድ ከእረፍት በፊት በ13ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ግብ አንድ ለዜሮ በመምራት እረፍት ወጥተዋል። ከእረፍት መልስ ሲዳማ ቡና ጫና ፈጥሮ በመጫወት በ56ኛው ደቂቃ አጥቂው ኤርክ ሙራንድ ለክለቡና ለራሱ ሁለተኛ ጎል ማስቆጠር ችሏል። የደደቢት ክለብ ከሽንፈት ያላዳነችውን ብቸኛ ጎል በበረከት ይስሀቅ አማካኝነት በ80ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል። ደደቢት አቻ ለመውጣት እስከ መጨረሻው ያደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ሁለት ለአንድ ሊሸነፍ ችሏል። የሲዳማ ቡና አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው በሜዳችን ሙሉ ሶስት ነጥብ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት በመሳካቱ በቀጣይ የሚኖሩንን ጨዋታዎች በማሸነፍ ዋንጫውን ለማንሳት ትኩረት እንሰጣለን ብለዋል። በፕሪሜዬር ሊጉ 18 ጨዋታ ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ38 ነጥብ ሲመራ ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ ጨዋታ እኩል 38 ነጥብ በመያዝ በጎል ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ፣ ንግድ ባንክ በ32 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። - See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/sport/item/3780-2015-04-20-19-40-19#sthash.p00FzDiz.dpuf