እንግሊዝ በኢትዮጵያ ያለው ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አፈጻጸም ያሰጋኛል አለች
- የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ላልተገባ ዓላማ እየዋለ ነው በሚል ተችታለች የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው የ2014 (እ.ኤ.አ.) የሰብዓዊ መብትና የዴሞክራሲ ሪፖርት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ኢትዮጵያ በምትፈጽማቸው ገደቦች ሥጋት እንደገባው አስታወቀ፡፡ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ላልተገባ ዓላማ እየዋለ ነው በሚልም ተችቷል፡፡ የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችና ሌሎች አካላት ሕጉ ተጠቅሶ የተከሰሱት የመሰብሰብና ሐሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ለመጠቀም ሙከራ ሲያደርጉ እንደሆነ ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡ በዓመቱ የዞን ዘጠኝ አባላት የሆኑ ሰባት ጦማሪያንና አቶ ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ 17 ጋዜጠኞች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉም ሲፒጄን በመጥቀስ ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ይህም ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ ከዓለም በአራተኝነት ደረጃ እንደሚያስቀምጣት አመልክቷል፡፡ 30 ጋዜጠኞች በዓመቱ ከአገር እንደተሰደዱ የገለጸው ሪፖርቱ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የመክሰስ ሐሳብ ስለሌለው ሊመለሱ ይችላሉ ማለቱንም ጠቅሷል፡፡ እንግሊዝ ኢትዮጵያ የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት 20 ጋዜጠኞች የተባረሩት በክልሉ የተከሰተውን የተማሪዎች አመፅ በዘገቡበት ተቺ አቀራረብ የተነሳ እንደሆነም እንደሚታመን ጠቅሷል፡፡ የአምስት መጽሔቶችንና የአንድ ጋዜጣ ኅትመት የተቋረጡትም በመንግሥት ውሳኔ እንደሆነ አመልክቷል፡፡ በአገሪቱ የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ተደራሽነት የተገደበ እንደሆነም ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ የግል አሳታሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋና በአስተማማኝ ሁኔታ የማተሚያ ቤት አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውም እንደ ሳንካ እንደሚቆጠር ገልጿል፡፡ ለጋዜጠኞች