የመድረክ የርእዮተ አለም አሰላለፉ እና የምርጫ ዝግጅቱ ሲቃኝ
የምስረታ ጊዜው 2001 ዓመተ ምህረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንደነት መድረክ/መድረክ በምርጫ 2002 ተሳትፏል። የፓርቲው የወቅቱ ሊቀመነበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስለፓርቲው አመሰራረትና ስሪት ሲገልፁ፥ መድረክ የአራት ፓርቲዎች ጥምረት በአደረጃጀቱም ግንባር መሆኑ ያነሳሉ። የኢትዮጵያ ማህበራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ/ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲ፣ የኦሮሞ ፌድራል ኮንገረንስ፣ አረና ትግራይ እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ናቸው አባላቱ። የኢትዮጵያ ማህበራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ እና የኦሮሞ ፌድራል ኮንገረንስ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ሲሆኑ፥ አረና ትግራይ እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ክልላዊ ፓርቲዎች ናቸው። መድረክ በጠቅላላ ጉባኤ በየአመቱ የሊቀመንበር ምርጫ ያካሂዳል፤ አንድ አባል ጠቅላላ ጉባኤው እስከ መረጠው ድረስ በተከታታይ ሁለት ጊዜ በሊቀ መንበርነት መምራት ይችላል። ከሁለት ጊዜ በላይ ግን መመረጥም፤ መምራትም አይቻልም። የሚከተለው ርእዮተ አለም ፓርቲው የተለያየ ርእዮተ አለም ያላቸው አራት ፓርቲዎች ስብስብ ነው። ስለዚህ የሚከተለው ርእዮተ አለም ምንነት ላይ ጥያቄ የሚያነሱ አሉ። ሊቀመንበሩ ፕሮፈሰር በየነ መድረክን ያስገኙት አባል ፓርቲዎች የየራሳቸው ርእዮተ አለም እንዳላቸው ነው የሚጠቅሱት። አራቱን ፓርቲዎች በአንድ ጥላ ስር መድረክ ብሎ ያሰባሰባቸው የሚከተሉት ርእዮተ ዓለም ሳይሆን ያላቸው መለስተኛ የፖለቲካ ፕሮግራም ነው ይላሉ ሊቀመንበሩ። መድረክ የተለያየ የፖለቲካ መስመርን ይዞ አንድ ፓርቲ መሆን ይቻላል ባይ ነው፤ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ፖለቲካ የርእዮተ አለም ሹክቻ ውስጥ የመግቢያ ደረጃ ላይ ያልደረሰ በመሆኑ የሚል መከራከራም አላቸው። በዚህ የተለያዩ ርእዮተ አለሞችን ይዞ በተመሳሳይ መለስተኛ የፖለቲካ ፕ