Posts

የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን በየዓመቱ በሚያወጣው የአፍሪካ መልካም አስተዳደር ጠቋሚ ኢትዮጵያ ከ52 አገሮች 32ኛ ወጣች

Image
እ.ኤ.አ. የ2014 የሞ ኢብራሂም የመልካም አስተዳደር ጠቋሚ ከ30 ገለልተኛ የአፍሪካና ዓለም አቀፍ ታማኝ ምንጮች የተገኙ ከመቶ በላይ መለኪያዎችን በመገምገም ነው የአገሮች የመልካም አስተዳደር ደረጃን ማውጣቱን የገለጸው፡፡ ዋነኛ መለኪያዎቹ አራት ምሰሶዎች መሆናቸውን የሚገልጸው ሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን፣ እነዚህም ሕዝቦች ከመንግሥታቸው የሚጠብቋቸውና መንግሥትም ማቅረብ የሚጠበቅበት ግዴታዎችን የሚዳስስ ነው፡፡ እነዚህ መሠረታዊ ምሰሶዎች የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ የመናገር ነፃነት፣ የንፅህናና የንብረት ባለቤትነት መብቶች ጥበቃን የሚዳስሱ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት ሞሪሺየስ፣ ኬፕ ቨርዴና ቦትስዋና ከአንድ እስከ ሦስተኛ ወጥተዋል፡፡ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሸልስ፣ ናሚቢያ፣ ጋና፣ ቱኒዚያ፣ ሴኔጋልና ሌሴቶ እስከ አሥረኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከምሥራቅ አፍሪካ አገሮች መካከል ሩዋንዳ በ11ኛ ደረጃ፣ ኬንያ 17ኛ ደረጃ፣ ኡጋንዳ 19ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ ኢትዮጵያ 32ኛ ላይ ትገኛለች፡፡ ሶማሊያ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ስትገኝ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክና ኤርትራ ይከተሏታል፡፡  ይህ በእንዲህ እንዳለ የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን በየዓመቱ ለአፍሪካ መሪዎች የሚሰጠውን ሽልማት የሥልጣን ዘመናቸውን በማጠናቀቅ ላይ ለሚገኙት የናሚቢያው ፕሬዚዳንት አድርጓል፡፡ ይህ ሽልማት ላለፉት አራት ዓመታት ብቁ የሆነ መሪ ባለመገኘቱ ሳይካሄድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡  ሽልማቱ በሥልጣን ላይ እያለ ለአገሩ መልካም አስተዳደር ላሰፈነ፣ የሕዝቦቹን የኑሮ ደረጃ ከፍ ላደረገና በሰላማዊ ሽግግር ከሥልጣን ለወረደ መሪ የሚሰጥ ነው፡፡ ሽልማቱም በአሥር ዓመት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ አምስት ሚሊዮን ዶላርና እስከ ዕድሜ ልክ ደግሞ በየዓመቱ 200 ሺሕ ዶላር ያስገኛል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2004 ጀምሮ ሁለት