Posts

በሐዋሳ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ለግምት የሚያዳግት ንብረት መውደሙ ተጠቆመ

‹‹ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል››  የታቦር ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ‹‹አንድ ሕፃን ልጅ ብቻ ሕይወቱ አልፏል››  የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ምክንያቱ በውል ያልታወቀው የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በሐዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ ታራ ቀበሌ አዲስ ከተማ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ የተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ፣ ለግምት የሚያዳግት ንብረት መውደሙን ተጎጂዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ የወደመው የንብረት ግምት በውል ባይታወቅም፣ ከ800 በላይ ሱቆች በመቃጠላቸው በርካታ ንብረት መውደሙን ግን የክልሉ ፖሊስ አረጋግጧል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችና ጉዳት የደረሰባቸው ባለሱቆች እንደገለጹት፣ ገበያው ከተመሠረተ ሦስት ዓመታት ሆኖታል፡፡ ቀኑ ሞቅ ያለ ገበያ የሚካሄድበት ከመሆኑ አንፃር፣ ከሌሎቹ ቀናት በተለየ ሁኔታ እያንዳንዱ ሱቅ በሸቀጣ ሸቀጦች ተሞልቷል፡፡ ነጋዴዎች ሙሉ ቀን ሲገበያዩ ውለው ሒሳባቸውን የሚሠሩት በነጋታው በዕለተ እሑድ በመሆኑ፣ አብዛኞዎቹ ከሽያጭ የሰበሰቡትን ገንዘብ እንኳን ይዘው አለመሄዳቸውን ተጎጂዎቹ ገልጸዋል፡፡ አደጋው የደረሰበት ሰዓት አብዛኛዎቹ ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን ቆልፈው ወደ ቤታቸው የሚገቡበት በመሆኑና እሳቱ በፍጥነት ሱቆቹን በማዳረሱ፣ የተወሰነ ንብረት እንኳን ማዳን አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡ ሐዋሳ ከተማ በተለይ የቱሪስቶችና የተለያዩ የአገሪቱ ዜጎች መዝናኛ ከተማ ከመሆኗ አንፃር፣ ድንገተኛ አደጋን ለመከላከል ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ በቂ የሆነ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ባለመኖሩ ገበያው ሙሉ ለሙሉ ሊወድም መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በርካታ ሚሊዮን ብሮች የሚገመት ንብረት መውደሙን የሚናገሩት ተጎጂዎቹ፣ የነበራቸውን ሀብት በሰዓታት ልዩነት ማጣ

Human Rights Watch Condemns World Bank Actions in Ethiopia

Image
On 23 February 2015, Human Rights Watch released a statement calling on the World Bank to address human rights issues that were raised by an internal investigation that the bank conducted on its actions in Ethiopia. The report found numerous links between investment projects conducted by the World Bank and a number of Ethiopian government initiatives that are deemed discriminatory and counter to basic principles of human rights. Source:  unpo.org Below is an article published by  Human Rights Watch : The World Bank should fully address serious human rights issues raised by the bank’s internal investigation into a project in Ethiopia, Human Rights Watch said in a letter to the bank’s vice president for Africa. The bank’s response to the investigation findings attempts to distance the bank from the many problems confirmed by the investigation and should be revised. The World Bank board of directors is to consider the investigation report and management’s response, which inclu

ERA Awarded Mojo – Hawassa Expressway for Keangnam

The first lot for Mojo – Hawassa Expressway project, which stretches for 93 kilometers, is awarded to a South Korean construction company, Keangnam Enterprises Limited, by Ethiopian Roads Authority (ERA). Workeneh, Gebehu, Ethiopia’s Minister for Transport, explained the firm won the bid for the first lot of the entire 209 kilometers. Even if Keangnam has won the bid the agreement between ERA and the company is not yet concluded. The project is going to be financed partially from a loan that will be secured from the South Korean Government. The difference will be covered by a state funding and the project is expected to commence in the current fiscal year. Upon completion a toll road is expected to connect the capital city of Ethiopia, Addis Ababa, with the capital of the State of Southern, Nations, Nationalities and Peoples. Samsun Wondimu, Public Relations Head at the Authority, explained Keangnam is going to handle the first phase of the project that stretches from Meki to

በሁለት ክፍለ ከተሞቿ ሲትጋይ ያደረችው ሐዋሳ እና ጥያቄ ውስጥ የገባው የከተማ ኣስተዳደር የእሳት ኣደጋን ለመቆጣጠር ያለው ዝግጅትና ብቃት

Image
ፎቶ ከ ተፈሪ ታደሰ በከተማ ታሪክ ከፍተኛ በተባለው በዚህ የእሳት ኣደጋ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፤ ኣላሙራ ኣዲሱ ገበያ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፤ በተመሳሳይ ምሽት በቱላ ክፍለ ከተማም ሁለት ቤቶች በቃጠሎው ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ታውቋል፤ የከተማዋ ኣስተዳደር መሰል የእሳት ኣደጋዎችን ለመቆጣጠር ያለው ዝግጅትና ብቃት ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፤ በሲዳማዋ መዲና ሐዋሳ ከተማ በሁለት ክፍለ ከተሞቿ በተነሱ የእሳት ኣደጋዎች በሰው፤ በእንስሳት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። የእሳት ኣደጋ የደረሰው በኣላሙራ ኣዲሱ ገበያ እና በቱላ ክፍለ ከተማ ነው። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የኣይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በታቦር ክፍለ ከተማ ፉራ ቀበሌ በሚገኘው በተለምዶ ኣዲሱ ገበያ ተብሎ በምጠራው ስፍራ ላይ ባለፈው ቅዳሜ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ ገበያውን ሙሉ በሙሉ አውድሟል። ባልታወቀ ምክንያት በተከሰተውና ከሰዓታት በቆየው የእሳት ቃጠሎ አንድ የአንድ አመት ከስድስት ወር ህጻን ልጅ ህይወቱ ሲያልፍ በአንድ አዛውንት ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል የመንግስት ዜና ኣውታሮች የዘገቡ ቢሆንም ከተለያዩ ምንጭ የተገኙ መረጃዎች የጉዳት መጠን ከፍተኛ መሆኑን ያመለክታሉ፡፡ የእሳት ቃጠሎውን ለማጥፋት የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ፣ የሀዋሳ ጨርቃ ጨርቅና የሻሸመኔ ከተማ እሳት አደጋ መከላከያና የክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊስ እሳት አደጋ መከላከያ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ የከተማው ኣስተዳደር መሰል ኣደጋዎችን ለመቆጣጠ ያለው ዝግጁነት እና ብቃት ኣነስተኛ መሆኑ ለጉዳቱ መባባስ ምክንያት መሆኑ ታውቋል።

“ቡና ኃይለኛ የቆዳ ካንሰር ሊከላከል ይችላል”

Image
ብሔራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚለው ከሆነ ቡና ሜላኖማን የመከላከል ኃይል አለው፡፡ 447 ሺህ  357  ሰዎችን ያሳተፈውና በአማካይ ለ10 ዓመታት የዘለቀው ይህ ጥናት ቡና በብዛት የሚጠጡ ሰዎች ለበሽታው ያላቸው ተጋላጭነት አነስተኛ መሆኑን አመላክቷል። በመሆኑም በቀን አራት ስኒ ቡና ወይም ከዚያ በላይ የሚጠጡ ሰዎች ለሜላኖማ የመጋለጥ ዕድላቸው ቡና ከማይጠጡ ሰዎች በ20 በመቶ ያነሰ መሆኑን ጠቁሟል። ይሁንና የጥናቱ ውጤት ያንኑ ናሙናው የተወሰደበትን ማህበረሰብ እንጂ ሌሎችን እንደማይወክልና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ ተመራማሪዎቹ አልሸሸጉም። ምንጭ፡-  ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ