Posts

Advocates Petition UN to Intervene on Jailed Ethiopian Bloggers’ Behalf

Image
Last April, nine writers were arrested and imprisoned in association with Ethiopia's Zone 9 blogging collective. Eleven weeks later, they were charged under the nation's Anti-Terrorism Proclamation. Since their arrest, Soleyana Gebremicheal and Endalk Chala, two members of the collective who now live in the United States, have advocated tirelessly for their colleagues’ release. Global Voices is honored to publish this original contribution by Soleyana and her colleague, Patrick Griffith, who are now petitioning the UN Working Group on Arbitrary Detention to intervene on the bloggers’ behalf. By  Soleyana S. Gebremicheal  and  Patrick Griffith  Despite early, high-level condemnation of the arrests of independent journalists and bloggers in Ethiopia nine months ago, international attention has waned as the pre-trial proceedings have dragged-on. The government’s continued detention of three independent journalists and six members of the Zone 9 blogging collective is not only

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሃዋሳ ከነማ ክለብን ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተሰማ

Image
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሃዋሳ ከነማ ክለብን ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተሰማ። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ አዳማ ከነማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ደደቢት ክለቦች አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለሱዳኑ አል አህሊ ሸንዲ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ሰርቷል። አሰልጣኙ ቀደም ሲል ለስድስት ወራት እንዲያሰለጥን ጥያቄ ቀርቦለት የነበር ቢሆንም ባለመስማማቱ፥ ክለቡ በአዲስ መልክ የአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ኮንትራት አቅርቦለት ከስምምነት ላይ መድረሱ ነው የተነገረው። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውጤት እየራቀው የሚገኘውን ሀዋሳ ከነማ ወደ ውጤት ለመመለስ የአሰልጣኙ ወደክለቡ መምጣት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ተጠቁሟል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ በኋላ ኢትዮጵያ ቡና ብቸኛውን የሊጉን  ዋንጫ እንዲያጣጥም በማገዝ ታሪካዊ ስራ መስራቱም አይዘነጋም። ኤፍ.ቢ.ሲ

በጃፓኑ ፈጣን ባቡር ከአሥር ሺሕ በላይ ተጓዦች የኢትዮጵያን የጫካ ቡና ይጠጣሉ

Image
ከይርጋጨፌ፣ ከሐረርና ከሲዳማ ቡናዎች በመቀጠል በዓለም የተመዘገ የኢትዮጵያ የጫካ ቡና የመሆን ዕድል እንዳለው ይነገርለታል፡፡ ይህ የተፈጥሮ የጫካ ቡና በአሁኑ ወቅት ተፈጊነቱ እየጨመረ ሲሆን በተለይ በጃፓን ቡና ጠጭዎች ዘንድ ከምንጊዜው በላይ እየተወደደ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በጅማ ዞን አስተዳደር ውስጥ ከሚገኙ አካባቢዎች ውስጥ በተለይ በለጠና ጌራ የተባሉት በቻካ ቡና ሀብታቸው ይታወቃሉ፡፡ የሰው ንክኪ የሌለው የጫካ ቡና እየለቀሙ የሚተዳደሩ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ቡናቸው በጃፓን ገበያ ተፈላጊነቱ እንዲጨምር ካቻሉት መካከል ሬንፎረስት አሊያንስ የተባለው አሜሪካ ኩባንያ የጫካውን ቡና ተፈጥሯዊ ይዞታ እያረጋገጠ የምሥክር ወረቀት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ ነበር፡፡ ከሰባት ዓመታት በፊት የተጀመረው ማረጋገጫ የመስጠት ተግባር ከወደጃፓን ስመ ወፍራም የሆኑ ኩባንያዎችን ለመሳብ አብቅቷል፡፡ የበለጠ-ጌራ የጫካ ቡናን በመግዛት ላይ የሚገኘው ዩሺማ ኮፊ ኮርፖሬሽን (ዩሲሲ) ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ቡናውን እንዲገዛ መንገዱን ያመቻቸው፣ የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ነው፡፡ በጃይካ በኩል የተመሠረተው የዩሲሲና የበለጠ-ጌራ ቡና አምራቾች ግንኙነት እየዳበረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ቡናቸው የልዩ ጣዕም ቡናነቱ ተመስክሮለት፣ በጃፓኑ ፈጣን ባቡር ለሚሳፈሩ ተጓዦች እየተሸጠ ይገኛል፡፡ በዓለም ላይ ፈጣን ከሚባሉት አንዱ የሆነውና ‹‹ቡሌት ትሬን›› የሚባል መጠሪያን ያተረፈው የባቡር ትራንስፖርት ላይ በየቀኑ ከአሥር ሺሕ በላይ የቡና ስኒዎች እየተሸጡ ሲሆን፣ ዩሲሲ ከዚህ በፊት በዚህ መጠን ለተሳፋሪዎች ቡና  ሸጦ እንደማያውቅ፣ የኩባንያው አማካሪ የሆኑትና በቅርቡ ጅማን ጎብኝተው የተመለሱት ናዖሚ ናካሒራም ሆኑ በጃይካ የግብርና

ነገ በእኔ በል ሲዳማ!

Image
አባይ ጸሐዬ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የዛቱበት ድምጽ ተለቀቀ – “በአ.አ. ማስተር ፕላን ላይ ዳግም ጥያቄ ካነሱ ልክ እናስገባቸዋለን” አሉ

የግል የኅትመት ሚዲያዎች በወገንተኝነት ተወቀሱ

Image
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን የግል የኅትመት ሚዲያዎች ወገንተኞች ናቸው ሲል ወቀሰ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንና ከብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ‹‹ምርጫና የሚዲያ ሚና›› በሚል ርዕስ የካቲት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ባዘጋጁት መድረክ ላይ ነው፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ልዑል ገብሩ ይህንን የተናገሩት፡፡ የግል የኅትመት ሚዲያዎች ዛሬም ቢሆን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን የማጥላላትና ጥላሽት የመቀባት አባዜ ያለባቸውና የብሔር ብሔረሰቦችን ማንነት የሚያንቋሽሹ ወገንተኛ ኅትመቶች ናቸው ብለዋል፡፡ ቢሆንም የተወሰኑት የግል ኅትመቶች ሥራቸውን በአግባቡ እንደሚሠሩ አለመጥቀስ ተገቢ አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን የውይይቱ ዋና ዓላማ በምርጫው ወቅት የሚዲያው ሚና ምን መሆን እንደሚገባው ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ ከ1997 ምርጫ እስከ 2002 ምርጫ ድረስ የሚዲያ ተቋማት ምርጫን የዘገቡበት ሁኔታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ፋኩልቲ መምህር በሆኑት ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ተዳሷል፡፡ ጋዜጠኞች በማንኛውም ፓርቲ ላይ አደጋ ሊያመጡ የሚችሉ ዘገባዎችን በማጣራትና ትክክለኛውን ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አስረድተዋል፡፡ በእሳቸው ዳሰሳ መሠረት የ1997 ምርጫ በሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን በማግኘት እስካሁን ወደር የሌለው ነው፡፡ ነገር ግን ጤናማ ያልሆኑ ፍረጃዎች የበዙበት፣ ከሙያው መርሆዎች ውጪ በርካቶች ዘገባ በመሥራታቸው ሕዝቡ የተጎዳበት እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ሌላው በኢትዮጵያ ምርጫ የሚዲያዎች ዘገባን በተመለከተ ንግግር ያደረጉት የዛሚ ፐብሊክ ኮኔክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ተሾመ፣ የ1997 ዓ.ም. ም