Posts

በጃፓኑ ፈጣን ባቡር ከአሥር ሺሕ በላይ ተጓዦች የኢትዮጵያን የጫካ ቡና ይጠጣሉ

Image
ከይርጋጨፌ፣ ከሐረርና ከሲዳማ ቡናዎች በመቀጠል በዓለም የተመዘገ የኢትዮጵያ የጫካ ቡና የመሆን ዕድል እንዳለው ይነገርለታል፡፡ ይህ የተፈጥሮ የጫካ ቡና በአሁኑ ወቅት ተፈጊነቱ እየጨመረ ሲሆን በተለይ በጃፓን ቡና ጠጭዎች ዘንድ ከምንጊዜው በላይ እየተወደደ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በጅማ ዞን አስተዳደር ውስጥ ከሚገኙ አካባቢዎች ውስጥ በተለይ በለጠና ጌራ የተባሉት በቻካ ቡና ሀብታቸው ይታወቃሉ፡፡ የሰው ንክኪ የሌለው የጫካ ቡና እየለቀሙ የሚተዳደሩ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ቡናቸው በጃፓን ገበያ ተፈላጊነቱ እንዲጨምር ካቻሉት መካከል ሬንፎረስት አሊያንስ የተባለው አሜሪካ ኩባንያ የጫካውን ቡና ተፈጥሯዊ ይዞታ እያረጋገጠ የምሥክር ወረቀት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ ነበር፡፡ ከሰባት ዓመታት በፊት የተጀመረው ማረጋገጫ የመስጠት ተግባር ከወደጃፓን ስመ ወፍራም የሆኑ ኩባንያዎችን ለመሳብ አብቅቷል፡፡ የበለጠ-ጌራ የጫካ ቡናን በመግዛት ላይ የሚገኘው ዩሺማ ኮፊ ኮርፖሬሽን (ዩሲሲ) ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ቡናውን እንዲገዛ መንገዱን ያመቻቸው፣ የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ነው፡፡ በጃይካ በኩል የተመሠረተው የዩሲሲና የበለጠ-ጌራ ቡና አምራቾች ግንኙነት እየዳበረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ቡናቸው የልዩ ጣዕም ቡናነቱ ተመስክሮለት፣ በጃፓኑ ፈጣን ባቡር ለሚሳፈሩ ተጓዦች እየተሸጠ ይገኛል፡፡ በዓለም ላይ ፈጣን ከሚባሉት አንዱ የሆነውና ‹‹ቡሌት ትሬን›› የሚባል መጠሪያን ያተረፈው የባቡር ትራንስፖርት ላይ በየቀኑ ከአሥር ሺሕ በላይ የቡና ስኒዎች እየተሸጡ ሲሆን፣ ዩሲሲ ከዚህ በፊት በዚህ መጠን ለተሳፋሪዎች ቡና  ሸጦ እንደማያውቅ፣ የኩባንያው አማካሪ የሆኑትና በቅርቡ ጅማን ጎብኝተው የተመለሱት ናዖሚ ናካሒራም ሆኑ በጃይካ የግብርና

ነገ በእኔ በል ሲዳማ!

Image
አባይ ጸሐዬ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የዛቱበት ድምጽ ተለቀቀ – “በአ.አ. ማስተር ፕላን ላይ ዳግም ጥያቄ ካነሱ ልክ እናስገባቸዋለን” አሉ

የግል የኅትመት ሚዲያዎች በወገንተኝነት ተወቀሱ

Image
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን የግል የኅትመት ሚዲያዎች ወገንተኞች ናቸው ሲል ወቀሰ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንና ከብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ‹‹ምርጫና የሚዲያ ሚና›› በሚል ርዕስ የካቲት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ባዘጋጁት መድረክ ላይ ነው፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ልዑል ገብሩ ይህንን የተናገሩት፡፡ የግል የኅትመት ሚዲያዎች ዛሬም ቢሆን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን የማጥላላትና ጥላሽት የመቀባት አባዜ ያለባቸውና የብሔር ብሔረሰቦችን ማንነት የሚያንቋሽሹ ወገንተኛ ኅትመቶች ናቸው ብለዋል፡፡ ቢሆንም የተወሰኑት የግል ኅትመቶች ሥራቸውን በአግባቡ እንደሚሠሩ አለመጥቀስ ተገቢ አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን የውይይቱ ዋና ዓላማ በምርጫው ወቅት የሚዲያው ሚና ምን መሆን እንደሚገባው ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ ከ1997 ምርጫ እስከ 2002 ምርጫ ድረስ የሚዲያ ተቋማት ምርጫን የዘገቡበት ሁኔታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ፋኩልቲ መምህር በሆኑት ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ተዳሷል፡፡ ጋዜጠኞች በማንኛውም ፓርቲ ላይ አደጋ ሊያመጡ የሚችሉ ዘገባዎችን በማጣራትና ትክክለኛውን ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አስረድተዋል፡፡ በእሳቸው ዳሰሳ መሠረት የ1997 ምርጫ በሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን በማግኘት እስካሁን ወደር የሌለው ነው፡፡ ነገር ግን ጤናማ ያልሆኑ ፍረጃዎች የበዙበት፣ ከሙያው መርሆዎች ውጪ በርካቶች ዘገባ በመሥራታቸው ሕዝቡ የተጎዳበት እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ሌላው በኢትዮጵያ ምርጫ የሚዲያዎች ዘገባን በተመለከተ ንግግር ያደረጉት የዛሚ ፐብሊክ ኮኔክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ተሾመ፣ የ1997 ዓ.ም. ም

Worancha connecting people & knowledge

የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ግለሰቦችን ያለፍቃዳቸው ከቤት ንብረታቸው ባያፈናቅላቸው ምን ይለዋል?

Image
ገዥው ፓርቲ በሚከተለው የከተሞች ልማት ፖሊስ የተነሳ በኢትዮጵያ በርካታ የከተማ ኣስተዳደሮች በየከተሞች ዙሪያ የምገኙትን ገጠራማ ቀበሌዎችን በመዋጥ ላይ ናቸው። በቅርቡ የኣዲስ ኣበባ ከተማ ኣስተዳደር በኣከባቢው የሚገኙትን ገጠራማ ትናንሽ የኦሮሚያ ከተሞችን በልማት ስም ከስሩ ኣስገብቷል። በርግጥ ትናንሽ ገጠራማ ከተሞችና ቀበሌዎች በትላልቅ ከተሞች ስዋጡ ይህ ለመጀመሪያ ግዜ ኣይደለም። እንዳውም የኣዲስ ኣበባ ከተማ ኣስተዳደር ከእኛዋ ከሃዋሳ ከተማ ልምድ የወሰደ ነው የሚመስለው። ከኣመታት በፊት የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር በዙሪያው በሲዳማ ዞን ስር ይተዳደሩ የነበሩትን 14 ቀበሌያት በቱላ ክፍለ ከተማ ስር ማጠቃለሉ ይታወሳል። በጊዜው የደኢህዴን ካድሬዎች ቀበሌያቱ ከሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ሰር ከተጠቃለሉ ብዙ ጥቅሞች እንደሚያገኙ በመስበክ የየቀበሌያቱን ነዋሪዎች መቆሚያ እና መቀመጫ በማሳጣት እንዲጠቃለሉ እንዳደረጉ ይታወቃል። በርግጥ በርካታ ሰዎች በጉዳዩ ላይ ደሰተኛ ባይሆኑም ለልማት እና ለለውጥ ጉጉ ስለነበሩ ደጋፋቸውን ከመስጠት ኣልተቆጠቡም። እንዳውም የቀበሌያቱን ከሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ስር መሆንን ኣስመልክተው ከብት ኣርደው ደግሰዋል። የሆነ ሆኖ፤ በኣሁኑ ጊዜ የቀበሌያቱ ነዋሪዎች በካድሬዎቹ የተገባላቸው የልማት ስራ ኣለመሰራቱን ይናገራሉ። በርግጥ ኣንዳንድ የልማት ስራዎች እየተሰሩ ያሉ ቢሆኑም እየተሰሩ ያሉት የልማት ስራዎች በሌሎች ክፍለ ከተሞች እየተሰሩ ካሉት ጋር የሚወዳደሩ ኣይደሉም ይላሉ። እንዳውም፤ የቀበሌዎቹ ከከተማ ኣስተዳደር ስር መሆናቸውን ተከትሎ በተለይ ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ በርካታ ችግሮች ኣጋጥሞቸዋል። በየቀበሌያቱ ያለው መሬት ተጠንቶ ፕላን እስኪሰራ ድረስ ቤት መገንባት በመከልከሉ የየቀበሌያቱ ነዋሪ