የደቡብ ክልል የፓርቲዎች የጋራ መድረክ ኢራፓን በአባልነት ሲቀበል፤ ሲአን/መድረክ በሲዳማ ዞን በቡርሳና በቦርቻ ምርጫ ክልል በአባላትና ደጋፊዎቼ ላይ ደረሰ ያለውን ድብደባና ወከባ የዞኑ የጋራ ምክር ቤት እንድያጣራ ወሰነ
በመጪው ምርጫ በደቡብ ክልል የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ /ኢራፓ/ን የጋራ ምክር ቤቱ ስድስተኛ አባል አድርጎ ተቀበለ፡፡ የጋራ መድረኩ ዛሬ ባካሄደው አምስተኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ የሚወዳደሩ ክልላዊ ፓርቲዎች በመሰረቱት የጋራ መድረክ ላይ እንዲሳተፍ በክልሉ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በኩል ቀደም ሲል ጥሪ ተደርጎለት ያልተገኘውንና ዛሬ የአባልነት ጥያቄ ያቀረበውን የኢራፓ ጉዳይና ሌሎች ሶስት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል፡፡ የኢትዮጵያውያን ራዕይ ፓርቲ /ኢራፓ/ ተወካይ አቶ ሺበሺ መኮንን በግል ጉዳይ ምክንያት እስካሁን በመድረኩ ምስረታና ስብሰባ ላይ ሳይገኙ በመቆየታቸው ይቅርታ ጠይቀው የጋራ መድረኩ አባል ለመሆን ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የጋራ መድረኩ በቀረበው ጥያቄ ላይ በመወያየት ኢራፓ አመራሮች በማይኖሩበት ወቅት ተወካይ በመላክ በመድረኩ ምስረታና ስብሰባ ላይ መካፈል ሲችል ይህን አለማድረጉ ተገቢ አለመሆኑ ተገልጾለት ለወደፊቱ አመራሩ በማይገኝበት ወቅት በውክልና ሌላ ሰው ተካፋይ እንዲሆን ማድረግ አንዳለበት ተገልጾለት የጋራ መድረኩ አባል እንዲሆን ያቀረበው ጥያቄ በሙሉ ድምጽ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ሲአን/መድረክ በሲዳማ ዞን በቡርሳና በቦርቻ ምርጫ ክልል በአባላትና ደጋፊዎቼ ላይ ጥር 22 ቀን 2007 ስብሰባ ላይ በፖሊስ ድብደባና ወከባ ደርሶባቸዋል በማለት ጉዳዩን የጋራ መድረኩ አጣርቶ የእርምት አርምጃ አንዲወስድ ባቀረበው አቤቱታ ላይም መድረኩ ውይይት አድርጓል፡፡ የሲአን/መድረክ ተወካይ በቡርሳና ቦርቻ በድርጅቱ አባላትና በደጋፊዎች ላይ ደረሰ ያለውን ድብደባና ወከባ ለጋራ መድረኩ ከማቅረቡ በፊት ችግሩ የተፈጸመው በዞን ስለሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ባለው የጋራ ምክር ቤት በማቅረብ ጉዳዩ እንዲታይ ማ